የተፈጥሮ ጥበቃ እና የአካባቢ ጥበቃ
የተፈጥሮ ጥበቃ እና የአካባቢ ጥበቃ
ተፈጥሮን መጠበቅና አካባቢ ጥበቃ የሚሉት ቃላት የተፈጥሮ ጥበቃንና ስነምህዳርን የሚያመለክቱ ቃላት ናቸው፡፡ በተጨማሪም በተፈጥሮ ላይ የሚከሰትን ለውጥ ስለ መገደብ እና ሰዎች በተፈጥሮ ላይ የሚያደርስቱን ጉዳት ማስተካከልንም ነው። የተፈጥሮ ጥበቃና የአካባቢ ጥበቃ አላማ ሰዎች፣ እንሰሳት እና እጸዋት ለወደፊቱም መልካም የሆነ (ባዮቶፕ) ስነህይወታዊ ይዘት እንዲኖራቸው ያደርጋል፡፡
እንደገና መጠቀም እና እንደገና ጥቅም ላይ ማዋል
ዳግም መጠቀም ማለት፡ እኛ በተለያዩ ምክንያቶች የማንጠቀምባቸውን ነገሮች፡ ሌሎች ሰዎች እንዲጠቀሙባቸው ማድረግ ነው። እንደገና ጥቅም ላይ ማዋል ማለት፡ ያገለገሉ ቁሳቁሶች ፈጭቶ በአዲስ መልክ መለወጥ ወይም ቀልጠው አዲስ ምርት ሆነው እንዲወጡ ማድረግ ነው። በቅርብ ዓመታት፡ ዳግም መጠቀም የተለመደ ነገር ሆኗል።ብዙ ሰዎች ስለ ፍጆታቸው እና ስለሚጣሉ ነገሮች የበለጠ እያውቁ በመምጣታቸው፡ ያገለገሉ ልብሶችን፣ የቤት እቃዎችን፡ ወዘተ፡ በመግዛት የመጠቀምን ኣስተሳሰባቸው መለወጥ ይፈልጋሉ።
ቆሻሻን ከምንጩ መለየት
እያንዳንዱ የኖርዌይ ነዋሪ በዓመት ብዙ መቶ ኪሎ ግራም ቆሻሻ ይጥላል። በብዙ ቀበሌዎች ውስጥ የሚኖሩ ሰዎች ከቤታቸው የሚያስወግዱትን ቆሻሻ እዚያው መለየት ጀምረዋል፡፡ ይህ ሂደት ቆሻሻን ከምንጩ መለየት ተብሎ ይታወቃል፡፡ አንዳንድ ቆሻሻዎችን በቤት ውስጥ መለየት እንችላለን፣ እንዲሁም አንዳንዶቹን ወደ ዳግም ማምረቻ አካባቢዎች እራሳችን ወስደን ማስረከብ እንችላለን፡፡ በዳግም ማምረቻ ስፍራዎች የተለያዩ አይነት ቆሻሻዎችን የምናስወግድባቸው ማጠራቀሚያ በርሜሎች አሉ፡፡ ብዙ የኣከባቢ ኣስተዳደሮች የራሳቸው ለውጦ ማምረቻ (የሪሳይክል) ጣቢያዎች አሏቸው። ስለዚህም ልናስወግዳቸው የምንፈልጋቸውን ትልቅ መጠን ያላቸውን የቤት እቃዎች፣ የማጠቢያ ማሽኖችን፣ የአትክልት ስፍራ ውጋጆችን፣ እንዲሁም የቀለም ቆርቆሮዎችን እዚያው ወስደን ማስረከብ እንችላለን፡፡
የምግብ ብክነት
የምግብ ብክነት ማለት ለምግብነት ሊውሉ የሚችሉ ምግቦችን ሰው ለምግብነት እንደማይጠቀማቸው አይነት ነገሮች በመቁጠር መጣል ማለት ነው፡፡ በዓለም ላይ ከሚመረተው ምግብ አንድ ሶስተኛው ሳይበላ ይጣላል። በኖርዌይ በየአመቱ 417,000 ቶን የሚሆን ለምግብነት ሊውል የሚችል ምግብ ይደፋል። ይህም ከየምግብ ማዘጋጃ ፋብሪካዎች፣ ከምግብ መሸጫ ሱቆች፣ ከምግብ ቤቶች፡ ወዘተ…እንዲሁም ከመኖሪያ ቤቶችም የሚወገደውን የሚጨምር ነው። በዓለም አቀፍ ደረጃ በአመት የሚደፋው ምግብ፡ በዓለም ላይ ያሉ የተራቡ ሰዎችን በሙሉ ሊመግብ የሚችል የምግብ መጠን ነው።
የሙቀት አማቂ ጋዝ ልቀቶች
በኖርዌይ ውስጥ የሙቀት አማቂ ጋዝ ልቀቶች ቀስ በቀስ እየቀነሱ ነው። ትልቁ የልቀት መጠን ነዳጅ እና ጋዝ ከማውጣት፣ ከኢንዱስትሪ እና ከማዕድን እንዲሁም ከመንገድ ትራፊክ የሚመጡ ናቸው።
በ2024፣ ለመጀመሪያ ጊዜ በኖርዌይ ውስጥ ከተመዘገቡት የነዳጅ መኪናዎች የበለጠ የኤሌክትሪክ መኪኖች ነበሩ። ግቡ ከሞላ ጎደል ሁሉም አዲስ መኪኖች ዜሮ ልቀት ያላቸው ተሽከርካሪዎች እንዲሆኑ ነው። ዜሮ ልቀት ያለው ተሽከርካሪ የሙቀት አማቂ ጋዞችን አያመነጭም። ሌላው ዓላማ ደግሞ በትልልቅ ከተሞች ውስጥ የተሳፋሪ ትራንስፖርት መጨመር በሕዝብ ማመላለሻ፣ በብስክሌት ወይም በእግር ጉዞ መጨመር መከተል አለበት። ስለዚህ የህዝብ ቁጥር ቢጨምርም የመኪና ትራፊክ በተመሳሳይ መንገድ መጨመር የለበትም።
ኣብራችሁ ተወያዩ
- ተፈጥሮንና አካባቢን ከመጠበቅ አንጻር እንደግለሰብ ምን በማድረግ የድርሻችንን መወጣት እንችላለን?
- ዳግም በመጠቀምና ለውጦ በማምረት ጉዳይ ላይ ተነጋገሩ፡፡
- ያገለገለ ማንኛውም ነገር ገዝታችሁ ተጠቅማችሁ ታውቃላቹ? ተጠቅማችሁ የምታዉቁ ከሆነ ለምን? ተጠቅማችሁ የማታውቁ ከሆነስ ለምን?
- ቆሻሻን ከምንጩ በመለየት ጉዳይ ተነጋገሩ፡፡ ለምንድነው ቆሻሻን ከምንጩ የምንለየው? ቆሻሻን ከምንጩ ባንለይ ምን ሊፈጠር ይችላል?
- ስለ ምግብ ብክነት ተነጋገሩ፡፡ ይህን የሚያህል ብዙ ምግብ የምንጥለው ለምን ይሆን? ሊበላ የሚችል ምግብ ደፍታችሁ ታውቃላችሁ? ደፍታችሁ ከሆነ ለምን? አልደፋችሁም ከሆነ ለምን?
- የግል መኪናንን በመጠቀምና የሕዝብ መጓጓዣዎችን በመጠቀም መካከል ያለውን ልዩነት ተነጋገሩበት፡፡ በኖርዌይ ሁሉም ሰው የሕዝብ መጓጓዣ የመጠቀም አጋጣሚ ይኖረዋል? አዎ ከሆነ ለምን? አይ ከሆንስ ለምን?
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ
ዳግም መጠቀም ምን ማለት ነው?
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ
በኖርዌይ ውስጥ እያንዳንዱ ሰው በአመት ምን ያክል መጠን ያለው ቆሻሻ ያስወግዳል?
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ
በኖርዌይ ከፍተኛውን የሙቀት አማቂ ጋዞች ልቀትን የሚያመጣው ምንድን ነው?
ትክክል ወይም ስህተት የሆነውን ይምረጡ
መግለጫዎቹን ያንብቡ፡፡ ትክክል የትኛው ነው? ስህተት የትናው ነው?
ትክክል ወይም ስህተት የሆነውን ይምረጡ
መግለጫዎቹን ያንብቡ፡፡ ትክክል የትኛው ነው? ስህተት የትናው ነው?
ትክክለኛውን ምስል ይምረጡ
በእለት ተእለት ሕይወታችን አካባቢያችንን በማይበክል መንገድ መኖር እንደምንችል የሚያሳየው የትኛው ምሥል ነው?