የቤት ውስጥ ዓመፅ

Lærerinnhold

Læreplan

Grunnleggende ferdigheter

Digitale ferdigheter
Muntlige ferdigheter

Tverrfaglige tema

Folkehelse og livsmestring

Læreplan i samfunnskunnskap for voksne innvandrere etter integreringsloven

samtale om hva negativ sosial kontroll, vold i nære relasjoner, tvangsekteskap og kjønnslemlestelse er, om juridiske og personlige konsekvenser av dette, og om aktuelle hjelpetilbud

Kjerneelement

Individ og fellesskap

Læringsaktivitet

Muntlig aktivitet

የቤት ውስጥ ዓመፅ

GettyImages

ዓመፅ ምንድነው?

  • ዓመፅ ማለት ሌላውን ሰው መተንኮስ ማለት ነው።
  • ትንኮሳ አካላዊ፣ ስነልቦናዊ፣ ጾታዊ ወይንም ቁሳዊ ሊሆን ይችላል።

የቤት ውስጥ ዓመፅ/ ጥቃት ምንድን ነው?

  • በቤተሰብ ውስጥ የሚፈጠር ወይንም በቅርብ ግንኙነት ባላቸው ሰዎች መካከል የሚፈጠር ዓመፅ ነው፡፡
  • ልጆችን የመንከባከብ ኃላፊነትን ለመወጣት በሚደረግ ግንኙነት በልጆችና በአዋቂዎች መካከል የሚፈጠሩ ዓመጾች።

ሁሉም የጥቃት ዓይነቶች በኖርዌይ ውስጥ ሕገወጥ ናቸው። ከቤተሰብ ይሁን ቅርብ ከሆኑ ሰዎች ጋር የሚፈጠር ማንኛውም አይነት ግጭት በማሕበረሰቡ ዘንድ ተቀባይነት የለውም። ይህ ማህበረሰብ፡ በቤተሰብ ውስጥ ወይም በሌሎች የቅርብ ግንኙነቶች ውስጥ ማንኛውንም ዓይነት ዓመፅ ሊቀበል አይችልም።ስለሆነም የቤት ውስጥ ዓመፅ የግል ጉዳይ አይደለም። አሉታዊ ማህበራዊ ቁጥጥር ዓመፅንም ሊያካትት ይችላል።

ልጆች ግጭቶችን ማየት የለባቸውም፡ ይህ በራሱ እንደ ዓመፅ የሚቆጠር ነው። ሴት ከሴት፡ ወንድ ከወንድ ጋር ያላቸው ስበት፣ ጾታቸው ግልጽ ያልሆኑትን፡ እና ሌሎች የ “LGBTIQ+” ማሕበረሰብ ኣባላት ለዓመፅ የተጋለጡ አካላት ሊሆኑ ይችላሉ።

የግዳጅ ጋብቻ እና የሴት ልጅ ግርዛት ዓመፅ ስለሆኑ ፈጽሞ ተቀባይነት የላቸውም። ሕብረተሰቡ ለዓመፅ ተጋላጭ የሆነውን ማንኛውም አካል የመጠበቅ፡ እንዲሁም ማንኛውም ሰው በሰፊው ማሕበረሰብ ውስጥ ተቀላቅሎ እንዲሳተፍ ማድረግ ይገባል።

የቤት ውስጥ ዓመፅ ከባድ ወንጀል ነው፡ ይህ በሠረታዊ ሰብዓዊ መብቶች ጥቃት ሲሆን የህዝብ ጤና ችግርም ነው።

ምንጭ፡ ዓመፅ የሌለው ህይወት፣ በየቤት ውስጥ ዓመፅ የድርጊት መርሃ ግብር፡ (2014 – 2017)፡ ሚኒስትሪ ፍትሕ እና የሕዝብ ደህንነት።

ኢንተርነት

En bekymret og alvorspreget kvinne holder telefonen til øret. Bildet illustrerer en kvinne som oppsøker hjelp etter å ha blitt utsatt for vold i hjemmet. Foto
GettyImages

ኣብራችሁ ተወያዩ

  • በቤት ውስጥ የሚፈጸመው ዓመፅ እና በሌሎች የጥቃት ዓይነቶች መካከል ያለውን ልዩነት ተወያዩበት።
  • አንድ ሰው በሌሎች የቤተሰቡ አባላት ላይ ዓመፅን የሚጠቀምበት ምክንያት ምን ሊሆን ይችላል?
  • አንድ ሰው ዓመፅ ከሚጠቀም የትዳር ጓደኛ ጋር አብሮ የሚኖርበት ምክንያት ምን ሊሆን ይችላል?
  • በዓመፅ ላይ ያለ አመለካከት፡ ከባህል ባህል የተለየ ነውን?
  • ዓመፅ ባለበት ቤት ውስጥ የሚኖሩ የቤተሰብ ኣባላት፡ ደህንነታቸው እንዴት ትገልጸዋለህ?

ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ

ዓመፅን በተመለከተ፡ የኖርዌጅያውያን ሕግ ምን ይላል?

ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ

ምን አይነት ዓመጾች አሉ? ከአንድ በላይ መልሶችን መምረጥ ይቻላል፡፡

አረፍተ ነገሩን አሟሉ፡፡

ማሕበረሰቡ…………ጨምሮ የትኛውንም አይነት ዓመፅ፡ ኣይቀበልም።

አረፍተ ነገሩን አሟሉ፡፡

የቤት ውስጥ ዓመፅ ....

ትክክል ወይም ስሕተት የሆነውን ይምረጡ ፡፡

መግለጫዎቹን ያንብቡ:: ትክክል የትኛው ነው? ስህተት የትኛው ነው?

ልጆች ዓመፅ ሲደርስ ሲመለከቱ ሆነ፡ ወይም በራሳቸው ዓመፅ ቢደርስ፡ እኩል ይጐዳሉ።
የግዳጅ ጋብቻ እና የሴት ልጅ ግርዛት ተቀባይነት የላቸውም።
ዓመፅ ወይን ትንኮሳ ከደረሰባችሁ እርዳታ ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዓመፅ የሚባለው ስነልቦናዊ ሳይሆን አካላዊው ብቻ ነው፡፡
የኖርዌጅያውያን ሕግ የቤት ውስጥ ዓመፅ ኣይቀበልም፡፡