ሃይማኖት እና የሕይወት አቋም
ሃይማኖት እና የሕይወት አቋም
ኖርዌይ ብዙ ባህል ያላት ዓለማዊ ማህበረሰብ ነች። ዓለማዊ ማህበረሰብ ማለት በሃይማኖት አይገለጽም ማለት ነው። ይህ በግለሰቦች እና ሕጎች ሲነደፍ፡ በሁለቱም ተፈጻሚ ይሆናል። ባለፉት ሁለት ትውልዶች ውስጥ ኖርዌጂያውያን በሃይማኖት ላይ ያላቸው አመለካከት በጣም ተለውጧል። ሃይማኖት የሰዎችን ሕይወት በከፍተኛ ደረጃ ያስተዳድር ነበር። ዛሬ፣ ብዙ ኖርዌጂያውያን ለሀይማኖት የበለጠ ዘና ያለ አቀራረብ አላቸው፣ ምንም እንኳን ብዙ ሰዎች ወደ ቤተ ክርስቲያን የሚሄዱት እንደ ጥምቀት፣ የእምነት ማረጋገጫ፣ ሰርግ እና የቀብር ሥነ ሥርዓቶች ባሉ አስፈላጊ ዝግጅቶች ጋር በተያያዘ ነው።
እስከ 2012 ድረስ ፕሮቴስታንት የኖርዌይ መንግሥታዊ ሃይማኖት ነበር፡ የኖርዌይ ቤተ ክርስቲያን ደግሞ የኖርዌይ መንግሥት ቤተ ክርስቲያን ነበረች። እስከ 1845 ድረስ ኖርዌጂያውያን ከመንግስት ቤተክርስትያን ኣባልነት መውጣት ኣይችሉም ነበር።በኖርዌይ ውስጥ ክርስቲያን ያልሆኑ ሃይማኖታዊ ማህበረሰቦችን ማቋቋም ህጋዊ የሆነው ለመጀመርያ ጊዜ በ1850 አካባቢ ነበር። ስለዚህ ኖርዌይ፡ የመንግስት ቤተክርስቲያን ወይም ኦፊሴላዊ ሃይማኖት የላትም። ሆኖም ኣብዛኛው የኖርዌይ ህዝብ አሁንም የኖርዌይ ቤተክርስትያን አባላት ናቸው። የተቀሩት በሌሎች ሃይማኖት ማህበረሰቦች መካከል ተሰራጭቷ ወይም ከየትኛውም የሃይማኖት ማህበረሰብ ልአባል አይደሉም።
በኖርዌይ ሙሉ የሆነ የሃይማኖት ነጻነት አለ፡፡ ይህ ማለት እምነታችሁን ያለምንም የስደት አሊያም የቅጣት ፍርሃት መተግበር ትችላላችሁ ማለት ነው፡፡ በተጨማሪም ማንም ሰው ሊከተል የሚፈልገውን እምነት በራሱ መወሰንና መምረጥ ይችላል ማለት ነው፡፡ እንዲሁም ማንም ሰው የትኛውንም ሃይማኖት ያለመከተል መብቱም የተጠበቀ ነው፡፡
መደበኛ የሃይማኖት እምነት የሚከተሉ እና የህይወት ኣቋም ኣመለካከታቸው የተለየ የሆኑ ሁሉ፡ ከማዕከላዊ መንግስት እና ከኣከባቢ ኣስተዳደሮች የገንዘብ ድጋፍ ሊያገኙ ይችላሉ። የተመዘገቡ የሃይማኖት እና የህይወት አቋም ማህበረሰቦች፡ ለእያንዳንዱ አባል የኖርዌይ ቤተክርስቲያን እንደምታደርገው ተመሳሳይ የእርዳታ ገንዘብ መጠን ያገኛሉ።
ኣብራችሁ ተወያዩ
- ሃይማኖት በዛሬይቱ ኖርዌይ ላይ ምን አይነት ተጽእኖ አለው? እናንተ በምታውቋቸው ሌሎች አገሮችስ ይህ ሁኔታ ምን ይመስላል?
- አንድ ማህበረሰብ ዓለማዊ ነው የሚለው አዎንታዊ ነው ወይስ አሉታዊ?
- በዛሬው የመድብለ (የብዙሃን) ባህላዊ ኖርዌይ ውስጥ የተለያዩ ሃይማኖቶች እንዴት አብረው ይኖራሉ?
- በተለያዩ የሃይማኖት ቡድኖች መካከል አንዳንድ ጊዜ ቅራኔዎች ነበሩ። በኖርዌይም ሆነ በዓለም አቀፍ ደረጃ ያለው ሁኔታ ዛሬ ምን ይመስላል?
- በአለባበስዎ፣ በጌጣጌጥዎ እና በባህሪዎ ውስጥ ሃይማኖታዊ አቋምዎን ማሳየት አስፈላጊ እና ትክክል ነው?
በምሳው ሰአት በሥራ ስፍራው፡ ኬሪ ከዚያ ቀደም ስለነበረው የጥምቀት ስርዓቱ ይናገራል፡፡ “የመዘምራኑ ቡድን ያቀረቡት ውብ የሆነ ዝማሬ ነበር፤ እንዲሁም አገልጋዩ በጣም ደስ የሚል ስብከት ነበር የሰበከው! በጣም ተነቃቅቼ ነበር፡፡ እያለ ይናገር ነበር፡፡ አንደኛ ጓደኛውም “ሃይማኖተኛ ሰው አትመስለኝም ነበር” አለው፡፡ ኬሪም “አይ በእርግጥ ሃይማኖተኛ ሰው አይደለሁም፡፡ ነገር ግን ድባቡ፣ ባህሉ፣ ክብሩና እርጋታው አሁንም ድረስ በውስጤ አለ፡፡” በማለት መለሰ፡፡
- ዛሬ ለብዙ ኖርዌጂያውያን ሃይማኖት ብዙም አስፈላጊ ባይሆንም፡ ብዙዎች በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ማግባት፣ ልጆቻቸውን እዚያ ማጥመቅ እና የመሳሰሉትን ይመርጣሉ። በሃይማኖት እና በወግ መካከል ያለውን ትስስር ተወያዩበት።
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ
ማሕበረሰቡ ዓለማዊ ነው ሲባል ምን ማለት ነው?
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ
ብዙ ኖርዌጅያውያን፡ ከሃይማኖት ጋር ምን አይነት ግንኙነት አላቸው?
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ
በኖርዌይ በ2012 በኖርዌይ የመንግሥት ሃይማኖት ተብሎ የሚታወቀው ምንድነው ?
ትክክል ወይም ስህተት የሆነውን ይምረጡ
መግለጫዎቹን ያንብቡ። ትክክል የትኛው ነው? ስህተት የትኛው ነው?
ትክክል ወይም ስህተት የሆነውን ይምረጡ
መግለጫዎቹን ያንብቡ፡፡ ትክክለኛው የቱ ነው? ስህተት የሆነው የቱ ነው?