ዲሞክራሲያዊ መብቶች እና ግዴታዎች

Lærerinnhold

Tips til undervisningen

I et demokrati har menneskene både rettigheter og plikter, ansvar og frihet. Alle disse fire faktorene bør være til stede for at demokratiet skal fungere på en god måte.

Hva skjer om ett av beina blir borte?

En demokratisk plikt er å følge de lovene som gjelder i samfunnet. Dette kan være plikt til å gi riktige og sannferdige opplysninger til offentlige etater (Nav, Skatteetaten, folkeregisteret o. l.).

Tips til undervisninga

I eit demokrati har menneske både rettar og plikter, ansvar og fridom. Alle desse fire faktorane bør vere til stades for at demokratiet skal fungere på ein bra måte.

Kva hender om eitt av dei fire «beina» blir borte?

Det er ei demokratisk plikt å følgje lovene som gjeld i samfunnet. Det kan til dømes vere plikta til å gje rette og sanne opplysningar til offentlege etatar (Nav, skatteetaten, folkeregisteret og liknande).

Læreplan

Grunnleggende ferdigheter

Digitale ferdigheter
Muntlige ferdigheter

Tverrfaglige tema

Demokrati og medborgerskap

Læreplan i samfunnskunnskap for voksne innvandrere etter integreringsloven

samtale om menneskerettigheter som ytringsfrihet og vern mot diskriminering
gi eksempler på hvordan demokratiet i Norge fungerer, knyttet til de tre statsmaktene og prinsippet om maktfordeling, politiske partier og valgordningen

Kjerneelement

Demokratiforståelse og deltakelse

Læringsaktivitet

Muntlig aktivitet

ዲሞክራሲያዊ መብቶች እና ግዴታዎች

በዲሞክራሲ የሚኖሩ ሰዎች ነጻነት፣ ሃላፈነቶች፣ መብቶችና፣ ተጠያቂነቶች አሉባቸው። በመጀመሪያ በጣም አስፈላጊ የሆኑትን መብቶች እንመለከታለን።

ሰብአዊ መብቶች

AdobeStock

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብአዊ መብት ድንጋጌ እ.ኤ.አ በ1948 ዓ.ም ነበር የተደነገገው፡፡

እኩልነት

AdobeStock

ማንኛውም ሰው ዕድሜ፣ ዘር፣ የተግባር ችሎታ፣ ጾታ፣ ሃይማኖት እና ጾታዊ ዝንባሌ ሳይለይ ተመሳሳይ መብቶችና እድሎች ሊኖሩት ይገባል።

የመናገር ነጻነት

Kvinne roper inn i en megafon. Hun har høyre hånd hevet og ser engasjert ut. Foto
GettyImages

የመናገር ነፃነት ማለት ስለ ፖለቲካ፣ ሃይማኖት እና ሌሎች ጉዳዮች ያለውን አስተያየት በነፃ መግለጽ፣ ከሌሎች ጋር በነፃነት መወያየት እና ያለ ምንም ቅጣት በነጻነት መፃፍ ማለት ነው። የመናገር ነፃነትን የሚገድቡ አንዳንድ ሕጎች አሉን። ለምሳሌ ሰዎች ዘረኝነትን እና ሌሎች የጥላቻ መግለጫዎችን በቃልም ሆነ በጽሁፍ እንዲናገሩ አይፈቀድላቸውም። የመናገር ነፃነት ለግለሰቦች እና ለሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ጣቢያዎች እና ጋዜጦች ላይም ይሠራል።

የመምረጥ/የማድመጥ/ ነጻነት

En hånd legger en stemmeseddel inn i en stemmeurne. Foto
GettyImages

በዲሞክራሲ ውስጥ ሰዎች በፖለቲካ ምርጫ የመምረጥ መብት አላቸው። በኖርዌይ የመምረጥ እድሜው 18 ዓመት ነው። ምርጫ የሚካሄደው በሚስጥር ድምጽ ነው። ይህ ማለት ግለሰቡ እንዴት ድምጽ እንደሰጠ ሌሎች ሰዎች አያውቁም ማለት ነው። ለጠቅላላ ምርጫ ድምጽ ለመስጠት የኖርዌይ ዜጋ መሆን አለቦት። በአውራጃ እና በኣከባቢ ኣስተዳደር ምርጫዎች ድምጽ ለመስጠት፡ ከምርጫው በፊት ላለፉት ሶስት አመታት በኖርዌይ መኖር አለበዎት።

የፍርድ ሒደት ዋስትና

Det norske flagget, klubbe og justicia-vekten. Foto.
GettyImages

የፍርድ ሒደት ዋስትና ማለት ማንም ሰው ያለፍርድ በእስራት ሊቀጣ ኣይችልም ማለት ነው። በዲሞክራሲያዊት ሀገር ፍርድ ማለት ነፃ የሆነ ዳኛ፡ ተከሳሹ ጥፋተኛ ነው ወይስ አይደለም የሚለውን የሚወስን ሲሆን፡ ነፃ ዳኛ ደግሞ ተከሳሹ ጥፋተኛ ሆኖ ከተገኘ ቅጣቱን ይወስናል ማለት ነው። ሁሉም ተከሳሾች የመከላከል መብት አላቸው።

የእምነትና የሀይማኖት ነጻነት

Religiøse symboler. Islam, jødisk, kristen. Foto.
GettyImages

የሃይማኖት እና የእምነት ነፃነት ማለት፡ ሰዎች የትኛውን ሃይማኖት ወይም እምነት መምረጥ እና ሃይማኖታቸውን ወይም እምነታቸውን መተግበር ነጻ ናቸው ማለት ነው። በሌላ አነጋገር፡ ማንም ሰው ከሃይማኖት ቡድን ወይም እምነት ማህበረሰብ እንዲቀላቀሉ ወይም እንዲለቁ የማስገደድ መብት የለውም። ማንም ሰው በሃይማኖቱ ምክንያት አይሰደድም ወይም አይቀጣም። ከ15 ዓመት እድሜ ጀምሮ፡ ማንኛውም ሰው፡በራሱ ተነሳሽነት የሃይማኖት ወይም የእምነት ቡድን የመቀላቀል ወይም የመልቀቅ መብት አለው።

የመሰብሰብ ነፃነት

የመሰብሰብ ነጻነት ማለት ብዙ ነገሮችን ማለት ነው፡፡ ከታች የተዘረዘሩት በጣም አስፈላጊ ከሆኑት መካከል ናቸው፡-

  • ሰዎች ለስደት እና ለቅጣት ሳይጋለጡ የፖለቲካ ፓርቲ ወይም የጥቅም ድርጅት አባል የመሆን መብት አላቸው
  • ሰዎች ስደትና ቅጣት ሳይደርስባቸው የሠራተኛ ማኅበር አባል የመሆን መብት አላቸው። በአንዳንድ ሁኔታዎች ሰዎች የስራ ማቆም አድማ የማድረግ መብትም አላቸው።
  • ሰዎች ሃሳባቸውን በህጋዊ ሰልፎች የመግለጽ መብት አላቸው።

መብቶችና ግዴታዎች

እንደምንመለከተው በዲሞክራሲ ስር የሚኖሩ ሰዎች ብዙ መብቶች አሏቸው፡፡ እነዚህ ነጻነቶችና መብቶች ደግሞ ከሃላፊነትና ግዴታ ጋር አብረው የሚሄዱ ናቸው፡፡ በአብላጫው ውሳኔ ለተደነገገ ሕግና ስርአት መገዛት ይገባል፡፡ በማሕበረሰቡ ውስጥ ያልወደድነውን ነገር ለመለወጥ የመሞከር መብት አለን፣ ይሁን እንጂ ይህንን ማድረግ የምንችለው በዲሞክራሲ ሕግ ተገዢ ሆነን ነው፡፡ የኖርዌጃውያን ማሕበረሰብ፡በታላቁ ሁኔታ፡ በጋራ መተማመን ላይ የተመሰረተ ነው፡፡ ይህ ማለት፡ ባለስልጣናቱ ሕዝቡ ትክክለኛውን መረጃ እንደሚሰጥና ለሕግና ደንብ ተገዢ እንደሆነ ያምናሉ፡ ሕዝቡም ከባለስልጣናቱ፡ ለምሳሌ ከፖሊስና ከልጆች አገልግሎት ጽሕፈት ቤቶች፡ ተገቢ እክብካቤ እንደሚያገኝ እምነት አለው፡፡

ዲሞክራሲን ምን አደጋ ላይ ሊጥል ይችላል?

የሚከተሉት አካላት ለዲሞክራሲ ስጋቶችን ሊወክሉ ይችላሉ።

ዝቅተኛ የምርጫ ተሳትፎ።
በፖለቲከኞች ላይ ያለው እምነት መቀንስ።
በህብረተሰቡ ውስጥ ግልጽ ክርክርን የሚያቆሙ የውሸት ዜናዎች እና የጥላቻ ንግግሮች።
የዲሞክራሲ ሂደቶች እንዲታለፉ የሚያደርጉ ዋና ዋና ሀገራዊ ቀውሶች።
ከአንድ ሀገር በዲሞክራሲያዊ መንገድ ከፀደቁ ህጎች ቅድሚያ በመስጠት ለብዙ ሀገራት ተፈጻሚ የሚሆኑ ህጎች እና መመሪያዎች።

ኣብራችሁ ተወያዩ

  • በዲሞክራሲያዊት ሀገር ውስጥ መኖር ምን ይመስላል?
  • ዲሞክራሲ በሌለበት ሀገር ውስጥ መኖር ምን ይመስላል?
  • በዲሞክራሲ ውስጥ ካሉ መብቶች ጋር አብረው ስለሚሄዱ ግዴታዎች ተነጋገሩ።
  • ምን ዓይነት ዲሞክራሲያዊ መብቶች እና ግዴታዎችን ያውቃሉ?
  • በምርጫው ዝቅተኛ ተሳትፎ እና በፖለቲከኞች ላይ ያለው እምነት መቀነስ ለዴሞክራሲ ጠንቅ የሆኑት ለምን እንደሆነ ተወያዩበት።
  • እምነት በኖርዌይ ማህበረሰብ ጠቃሚ ባህሪ የሆነው በምን መንገድ ነው? ይህ እንዴት እንደሚገለጥ ምሳሌዎችን መስጠት ይችላሉ?
LØvebakken. Stortinget. Foto.
GettyImages

ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ

በኖርዌይ ፍጹም የሆነ የንግግር ነጻነት አለን?

ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ

በኖርዌይ ውስጥ ለመምረጥ የሚፈቀደው በስንት እድሜ ነው?

ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ

በወንጀል ከተከሰሱ መከላከያ የማግኘት መብት ያለው ማነው?

ትክክል ወይም ስህተት የሆነውን ይምረጡ

መግለጫዎቹን ያንብቡ። ትክክል የትኛው ነው? ስህተት የትኛው ነው?

በዲሞክራሲ ውስጥ የሚኖሩ ሰዎች ነጻነት፣ ሃላፊነት፣ መብት ፣እና ግዴታ አላቸው፡፡
የመናገር ነጻነት ሁሉንም አይነት ንግግሮች የሚመለከት ነው፡፡
በዲሞክራሲ ውስጥ የሚኖሩ ሰዎች በፖለቲካዊ ምርጫ ጊዜ ድምጽ የመስጠት መብት አላቸው፡፡
በኖርዌይ ውስጥ የሚኖር ማንኛውም ሰው በጠቅላላ ምርጫ መምረጥ ይችላል።
በኖርዌይ ውስጥ በአካባቢ እንዲሁም በቀበሌ ምርጫ ላይ ለመሳተፍ በሃገሪቱ ውስጥ ቢያንስ ለሶስት አመት መኖርን ይጠይቃል፡፡

ትክክል ወይም ስህተት የሆነውን ይምረጡ

መግለጫዎቹን ያንብቡ። ትክክል የትኛው ነው? ስህተት የትኛው ነው?

ከባድ ወንጅል የፈጸሙ ከሆነ፡ ያለ ፍርድ እስራት ሊቀጡ ይቻላል።
ሁሉም ተከሳሾች መከላከያ የማግኘት መብት አላቸው።
ማንም ሰው ሌላውን ሰው አንድን ሃይማኖት ወይንም ማህበረሰብ እንዲከተል አሊያም እንዲተው የማድረግ መብት የለውም፡፡
አንድ ሰው ከ15 አመቱ ጀምሮ የትኛውን ሃይማኖት ወይንም ማሕበረሰብ መያዝ እና መልቀቅ እንዳለበት በራሱ ተነሳሽነት የመወሰን መብት አለው፡፡
በኖርዌይ ፈቃድ ያለው ብቸኛው እምነት ክርስትና ነው