ተፈጥሮና የተፈጥሮ ሃብቶች
ፊልሙን ይመልከቱ
ተፈጥሮና የተፈጥሮ ሃብቶች
ኖርዌይ ባለፉት 100 ዓመታት ውስጥ ከዓለማችን እጅግ ሀብታም ከሆኑ አገሮች አንዷ ሆናለች። ይህ ሃብት የተመሰረተው በሀብታሙ የተፈጥሮ ሀብቷ እና በኖርዌይ ውስጥ ያሉ ሰዎች እንዴት እነሱን መጠቀም እንደተማሩ ነው። የኖርዌይ የተፈጥሮ ሀብቶች በዋናነት ዓሳ፡ ደን እና ነዳጅ ናቸው። በተጨማሪም በኖርዌይ ወንዞች እና ፏፏቴዎች ውስጥ ብዙ ውሃ አለ፣ ይህም የኤሌክትሪክ ኃይል ለማምረት ያገለግላል። ከቅርብ ዓመታት ከቅርብ ዓመታት ወዲህ የንፋስ ኃይል ማመንጫዎች የኤሌክትሪክ ኃይል ለማምረት ጥቅም ላይ መዋል ጀምረዋል::
ነዳጅ ለመጀመሪያ ጊዜ የተገኘው በኖርዌይ በሰሜን ባህር በ1960ዎቹ መጨረሻ ላይ ነው። ነዳጅ ለኖርዌይ ኢኮኖሚ በጣም አስፈላጊ ነው።
ኖርዌይ በተፈጥሮ ሃብት ላይ የተመሰረተ ብዙ ምርቶችን ወደ ውጭ ትልካለች። ወደ ውጭ ከሚላኩ ምርቶች በተለይም አሉሚኒየም ነው። የብረታ ብረት ኢንዱስትሪው ከፍተኛ የኤሌክትሪክ ኃይል የሚፈልግ ሲሆን፡ ከውሃ የሚመነጭ ኤለክትሪክ ሃይል ደግሞ ከፍተኛ መጠን ያለው ብረቶችን ለማምረት አስችሏል። በኖርዌይ፡ ዓሳ በጣም ጠቃሚ የተፈጥሮ ሀብት ነው። ዓሦችን ወደ ብዙ አገሮች ይላካል፣ ይህም የውጭ ንግድ ከዓመት ወደ ዓመት እየጨመረ ነው። ኖርዌይ ብዙ ጫካ አላት። በአንዳንድ የደን ውጤቶች ጣውላዎች ይሠራሉ። በተጨማሪ፡ የደን ውጤት ወረቀት እና የግንባታ ቁሳቁሶችን ለመሥራት ያገለግላል። አንዳንድ እንጨቶችም እንዲሁ ወደ ውጭ ይላካሉ።
ተፈጥሮና ከቤት ውጪ ያለ ሕይወት
ተፈጥሮ በራሱ ሀብት ነው። ቱሪስቶች የባህር ዳርቻውን (fjords) እና “የእኩለ ሌሊት ፀሐይን” ለማየት ከመላው አለም ይመጣሉ። ኖርዌይ የሚኖሩ ብዙ ሰዎች ዘና ለማለት እና በተፈጥሮ ውስጥ ኣዲስ ኋይልን ለማግኘት ይወዳሉ። በኖርዌይ ውስጥ ሰዎች በሚኖሩበት ቦታ ሁሉ ከተፈጥሮ ሩቅ አይደሉም፡ ስለዚህም ሁሉም ወደ ፈለጉበት መሄድ ይችላሉ። ይህ "የህዝብ ተደራሽነት መብት" በመባል ይታወቃል። ወጣ ባለ መሬት (በባህር ዳርቻዎች፣ ረግረጋማ ቦታዎች፣ ደኖች እና ተራሮች) በእግር ወይም በበረዶ ስኪዎች (ski) ወደ የትኛውም ቦታ ለመጓዝን እና በፈለግንበት ቦታ እረፍት ማድረግ ይቻላል። ሌሊቱን ከዋክብት ስር ማደር ወይም ድንኳን መትከል ይችላል፡ ነገር ግን በአቅራቢያዎ ካለው ቤት ወይም ካቢኔ ቢያንስ 150 ሜትር ርቀት ላይ መሆን አለብዎ። በኣንድ ቦታ ከሁለት ቀናት በላይ ለማሳለፍ ከፈለጉ ግን፡ የመሬቱን ባለቤት ፈቃድ መጠየቅ አለብዎት።
'የህዝብ ተደራሽነት መብት" ግዴታንም ኣለበት። እንስሳትን መጉዳት ወይም ተፈጥሮን ማበላሸት የለብህም። የተጠቀምንበትን ሁሉ ማጽዳት አለብን፡ የፈለገውን ቆሻሻ ደግሞ መተው የለብንም። በተጨማሪም እሳት ሲያነዱ፡ በጣም ጥንቃቄ ማድረግ አለ። ከ15 ሚያዝያ እስከ መስከረም 15 ባለው ጊዜ ውስጥ፡ በጫካ ውስጥ ወይም በደን አቅራቢያ እሳትን ማብራት የተከለከለ ነው። ለኣንድ ግዜ የሚያገለገል መጥበሻ መጠቀም ቢፈቀድም፡ ቢሆንም በጣም መጠንቀቅ ያሻል።
የዱር ፍሬዎችን(ቤሪዎችን)፣ እንጉዳይዎችንና፣ አበባዎችን በብዙ ቦታዎች መልቀም ትችላላችሁ፡፡ ብዙ ኖርዌጃውያን በእረፍት ጊዜያቸው አሳ ያጠምዳሉ አደን ያድናሉ፡፡ በአጠቃላይ ከወንዞችና ከሐይቆች አሳ ለማጥመድ የአሳ ማጥመጃ ፈቃድ ማውጣት ያስፈልጋል፡ ለዚህም ይከፈልበታል።
ኣብራችሁ ተወያዩ
- በትውልድ ሀገራችሁ፡ ምን ዓይነት የተፈጥሮ ሀብቶች አሉ? እንዴት ጥቅም ላይ ይውላሉ?
- ስለ ነዳጅ ምርት እና የነፋስ ኃይል ጥቅሞች እና ጉዳቶች ተወያዩ።
- ስለ ህዝብ የተደራሽነት መብት ተነጋገሩ። በትውልድ አገራችሁ ተመሳሳይ መብቶች አሉ?
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ
ኖርዌይ በብዛት ወደ ውጪ የምትልከው ምርት ምንድነው?
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ
ወደ መረጣችሁት ተፈጥሮአዊ አካባቢ የመሄድን መብት ምን ብለን እንጠራዋለን?
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ
ተፈጥሮአዊ ስፍራዎች ስትሆዱ የሚጠበቅባችሁ ሃላፊነት ምንድነው?
ትክክል ወይም ስህተት የሆነውን ይምረጡ
መግለጫዎቹን ያንብቡ:: ትክክል የትኛው ነው? ስህተት የትኛው ነው?
ትክክል ወይም ስህተት የሆነውን ይምረጡ
መግለጫዎቹን ያንብቡ፡፡ ትክክል የትኛው ነው? ስህተት የትኛው ነው?
ምስሉን ተጫኑት
በምስሉ ላይ ትክክለኛውን ቦታ ጠቁሙ፡፡ ከሚያዝያ 15 እስከ መስከረም 15 ባለው ጊዜ ውስጥ በደኖች ውስጥ ምን ማድረግ ክልክል ነው?