የቤተሰብ ምጣኔ, እርግዝና እና የልጆች ክትትል
የቤተሰብ ምጣኔ
የቤተሰብ ምጣኔ
በኖርዌይ ፖለቲከኞች ጥንዶች ብዙ ልጆች እንዲወልዱ እንዴት ማበረታታት እንደሚችሉ ይወያያሉ። በአንዳንድ አገሮች፣ ሴቶች ምን ያህል ልጆች መውለድ እንደሚፈቀድላቸው ባለሥልጣናቱ ጥብቅ ገደብ ሊያደርጉ ይችላሉ። በሌሎች አገሮች የኣንድ ሴት አማካይ የወሊድ መጠን አምስት ልጆች ነው።
የቤተሰብ ምጣኔ ማለት ጥንዶች፡ ሴትየዋ መቼ ማርገዝ እንዳለባት መወሰን እና ምን ያክል ልጆች ሊኖሯቸው እንደሚገባ ማቀድ ማለት ነው። ተግባራዊው የቤተሰብ ምጣኔ ማለት ደግሞ አላስፈላጊ እርግዝናን መከላከል ማለት ነው። ለዚህም የተለያዩ የወሊድ መቆጣጠሪያ ዓይነቶች ጥቅም ላይ ይውላሉ፡፡
አንዳንድ የተለመዱ የእርግዝና መከላከያ ዓይነቶች፡-
- የወሊድ መከላከያ ክኒኖች ኢስትሮጅን እና ጌስታጅን/ፕሮጄስትሮን ሆርሞኖችን ያካተቱ እንክብሎች ናቸው። እነዚህ እንክብሎች የእንቁላልን መመረት ያስቆማሉ፡፡
ከቆዳ በታች የሚቀበሩ የወሊድ መቆጣጠሪያዎች የሚባሉት ደግሞ ትንንሽ የፕላስቲክ ዘንጎች ሲሆኑ ከቆዳ በታች የሚቀበሩ ሲሆኑ፡ መጠኑ አነስተኛ የሆነ ጌስተጄን ሆርሞን በየቀኑ ይለቃሉ። ይህ ሆርሞን እንቁላል እንዳይመረት ያደርጋል፡፣ ይህ የወሊድ መከላከያ፡ በዶክተር መግባት እና መውጣት አለበት። - ጥቅል (Coil) የሚባለው ደግሞ በሴቶች ማሕጸን ውስጥ በዶክተሮች የሚቀመጥ ነው፡፡ ይህ ጥቅል ደግሞ የወንዱ የዘር ፈሳሽ እንዳይንቀሳቀስ የሚያደርግ ሲሆን እንቁላሉ ዳብሮ በማሕጸን ግድግዳ ላይ እንዳይጣበቅ የሚያደርግ ሲሆን ይህም እርግዝና እንዳይፈጠር ያደርጋል፡፡.
- ኮንዶም በግብረ ሥጋ ግንኙነት ከሚተላለፉ በሽታዎች የሚከላከለው ብቸኛው የእርግዝና መከላከያ ነው። በተጨማሪም፡ በወንዶች ጥቅም ላይ የሚውለው ብቸኛው የወሊድ መከላከያ ነው። ካልተፈለገ እርግዝና አደጋን ለመቀነስ ስፐርሚሳይድ ከኮንዶም ጋር አብሮ መጠቀም ይመከራል። ስፐርሚሳይድ በራሱ ግን በቂ አይደለም።
የቅድመ ወሊድ ምርመራ እና ልጅ መውለድ
ኖርዌይ ውስጥ ነፍሰጡር ሴቶች የወሊድ ክትትላቸውን በነጻ የማድረግ መብት አላቸው። የወሊድ ክትትላቸውን በጤና ማዕከላት አሊያም ደግሞ በሴቶች የግል ዶክተር አማካኝነት ማድረግ ይችላሉ። ክትትሉ የሚደረገው በፈቃደኝነት ሲሆን የእናቲቱንና የልጁን ጤንነት ቅድመ ወሊድ ጊዜ፣ በወሊድ ጊዜና በድህረ ወሊድ ጊዜ ያለውን የጤና ሁኔታ የተጠበቀ ያደርገዋል። በኖርዌይ አንዲ ሴት ከ8-12 ጊዜ ክትትል እንድታደርግ ይመከራል። ብዙ ሴቶች ከክፍያ ነጻ፡ በሆስፒታል ውስጥ ይወልዳሉ፡፡
የጤና ምርመራዎችና ክትባቶች
በኖርዌይ የሚኖሩ ልጆች እና ወጣቶች መደበኛ የሆነ የጤና ምርመራ አቅርቦት አላቸው። ይህ የጤና ምርመራ ልጆች ተወልደው ትምህርት እኪጀምሩ ድረስ በጤና ማዕከላት ይሰጣል፡፡ለትምህርት ለደረሱ ልጆች የጤና ምርመራ ሃለፊነቱን የሚወስደው የትምህርት ቤቱ የጤና አገልግሎት ይሆናል። አብዛኛዎቹ የኣከባቢ ኣስተዳደሮች የራሳቸው የሆነ የወጣቶች የጤና ማዕከል አላቸው። በተጨማሪም በኖርዌይ የሚኖሩ ልጆችና ወጣቶች በከባድ በሽታዎች እንዳይያዙ ለመከላከል ክትባት ይሰጣቸዋል። ክትባቱም ቀላል ፣ውጤታማ እና ደህንነቱ በተረጋገጠ ሁኔታ በሽታዎችን የሚከላከል ነው። የጤና ማዕከሉም ሆነ የትምህርትቤቱ የጤና አገለግሎት ከክፍያ ነጻ ናቸው።
የልጆች መደበኛ ዶክተር፡ ልጆች በሚታመሙበት ጊዜ ምርመራ ያደርጋል።
ፅንስ ማስወረድ
በኖርዌይ: ያለው እርግዝናን ስለማቋረጥ ሕግ (የፅንስ ማስወረድ ህግ): ኣንዲት ሴት በመጀመሪያዎቹ 12 ሳምንታት ውስጥ፡ እርግዝናውን ለማቋረጥ መወሰን እንደሚትችል ይደነግጋል። ሴትየዋ ፅንስ ማስወረድ እንደምትፈልግ እና ስለ ፅንስ ማስወረድ የህክምና ጉዳዮች እና ስለ ፅንስ ማስወረድ አማራጮች ተጨማሪ መረጃ የማግኘት እድል እንዳገኘች የሚያረጋግጥ ቅጽ ሞልታ ማቅረብ አለባት። የፅንስ ማስወረድ ሕጉ፡ አንዲት ሴት ከአስራ ሁለተኛው ሳምንት በኋላ ፅንስ ማስወረድ ከፈልገች፣ ምን ሊያጋጥም እንደሚችል መመርያ ያወጣል።
ኣብራችሁ ተወያዩ
- በምታውቃቸው አገሮች ስለ ቤተሰብ ምጣኔ ሰዎች ምን ያስባሉ? የወሊድ መከላከያዎችን መጠቀም የተለመደ ነው?
- ለምንድነው የቅድመ ወሊድ ምርመራዎች ከክፍያ ነጻ እንዲሆኑ በጣም አስፈላጊ ተብለው የሚታሰቡት?
- ለምንድነው ወላጆች በጤና ጣቢያዎች ለሚሰጡትን አገልግሎት መጠቀም አስፈለጊ የሚሆነው?
- በኖርዌይ ውስጥ ያሉ አብዛኛዎቹ ሕጻናት ከተለያዩ በሽታዎች ለመከላከል መከተባቸው ምን ያስባሉ?
- የክትባት ፕሮግራሙ ከክፍያ ነፃ የሆነውለምንድነው ለምንድነው ?
ቀጥሎ ባለው ጉዳይ ላይ ተወያዩ፡
- የፅንስ ማስወረድ ሕግ፡ በሴቶች ራስን በራስ የመወሰን መብት እና በፅንሱ ሕጋዊ ጥበቃ መካከል ያለውን ስምምነት ግምት ውስጥ ያደረገ ነው።
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ
ኖርዌጅያውያን ሴቶች በአማካይ ምን ያክል ልጆች ይኖሯቸዋል?
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ
የቤተሰብ ምጣኔ ምን ማለት ነው? ከአንድ በላይ መልስ መምረጥ ትችላላችሁ
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ
የጤና ማዕከላት ሚና ምንድነው?
ትክክል ወይም ስህተት የሆነውን ይምረጡ
መግለጫዎቹን ያንብቡ:: ትክክል የትኛው ነው፣ ስህተት የትኛው ነው?
ትክክል ወይም ስህተት የሆነውን ይምረጡ
መግለጫዎቹን ያንብቡ:: ትክክል የትኛው ነው? ስህተት የትኛው ነው?