የኖርዌይ እውነታዎች
ፊልሙን ይመልከቱ
የኖርዌይ እውነታዎች
- ኖርዌይ ንጉሣዊ አስተዳደር ያላት አገር ናት፡፡ የአገሪቱ መሪ፡ ንጉሥ ሃራልድ ይባላል። የንግሥናው መዓርግ ከትውልድ ወደ ትውልድ ይሸጋገራል።
- በኖርዌይ 5.5 ሚሊዮን ሰዎች ይኖራሉ (01.01.2024)፡፡ 75 ከመቶ የሚሆነው ሕዝብ በባሕር ዳርቻዎች የሚኖር ነው። ግማሽ የሚሆነው ሕዝብ ደግሞ በምሥራቃዊው የኖርዌይ ክፍል ይኖራል፡፡
- በኖርዌይ ሁለት ብሔራዊ ቋንቋዎች ያሉ ሲሆን ኞሽክ እና ሳሚ ይባላሉ። በኖርዌይ ቡክሞል እና ኒኖክሽ የተሰኙ የጽሑፍ ቋንቋዎች ኣሉ።
- የኖርዌይ የቆዳ ስፋት 385,178 ስኩዌር ኪሎሜትር ነው። ሕንድ ከኖርዌይ አስር እጥፍ ትበልጣለች ማለት ነው፡፡
- ኖርዌይ፣ ከስዊድን፡ ፊንላንድ እና ራሽያ ጋር ድንበር አላት።
- ዋና ከተማዋ ኦስሎ ትባላለች፡፡ ኦስሎ የኖርዌይ ትልቋ ከተማ ስትሆን በያዝነው ዓመት (በ2021 ዓ.ም.) 700,000 ያህል ነዋሪዎች አሏት (2024)፡፡
- አራቱ ታላላቅ ከተሞቿም ኦስሎ፣ በርገን፣ ትሮንደሄይምና ስታቫንገር ናቸው።
- የኖርዌይ ደቡባዊ የዳርቻ ጫፍ፡ ሊንደስነስ ነው።
- በሰሜን ኬፕ የሚገኘው ክኒቭሼሎደን የኖርዌይ ሰሜናዊ ጫፍ ነው።
- ስቫልባርድ የደሴቶች ስብስብ ሲሆኑ ንብረትነታቸው ደግሞ የኖርዌይ ነው።
- ኖርዌይ በ15 ክልሎች የቆመች ናት።
- በ356 የኣከባቢ ኣስተዳደሮች/ኮሙነ ትከፈላለች።
ምንጭ: www.ssb.no, www.fn.no, www.oslo.kommune.no
መልክአ ምድራዊ አቀማመጥ
ኖርዌይ ብዙ የተራራ ቦታዎች እና ብዙ ደኖች አሏት። ትላልቅ ደኖቹ እና ተራራማ አካባቢዎች ጫካዎች እና ሰው የምይኖርባቸው ናቸው። በአንዳንድ ተራራማ አካባቢዎች በረዶው የማይቀልጥበት የበረዶ ግግር የሸፈናቸው ናቸው።
የኖርዌይ ሰፊ የባህር ዳርቻ 25,148 ኪሎ ሜትር ርዝመት አለው። ይህ ከሰሜን ዋልታ እስከ ደቡብ ዋልታ ድረስ ካለው ርቀት ይረዝማል! በባህር ዳርቻ ላይ ያለው ተፈጥሮ ከደቡብ ወደ ሰሜን ይለያያል። በብዙ ቦታዎች ትላልቅ እና ትናንሽ የባህር ወሽመጥ እና ፊዮርዶች ወደ የመሬት ገጽታ ጠልቀው ይቆርጣሉ። በባህር ዳርቻው ወደ 50,000 የሚጠጉ ደሴቶችም አሉ፡ ነገር ግን ከእነዚህ ደሴቶች ሰዎች የሚኖሩባቸው ጥቂት ናቸው። አንዳንድ ደሴቶች ከዋናው መሬት ጋር በድልድይ ወይም በዋሻ ይገናኛሉ፣ ሌሎቹ ደግሞ፡ በጀልባ አገልግሎቶች ብቻ ይገናኛሉ።
ኖርዌይ ውስጥ ወደ ተለያዩ ስፍራዎች ለመጓዝ ቀላል ነው፡፡ የሕዝብ መጓጓዣ አገልግሎት በጥሩ የተገነባ ነው። ሰዎች፡በቤት መኪና፣ በአውቶብስ፣ በባቡር፣ በጀልባ አሊያም በአውሮፕላን መጓዝ ይችላሉ።
ምንጭ ፡ SSB/ስታትስቲክስ ኖርዌይ
በኖርዌይ ውስጥ ያለውን የመሬት ገጽታ ያስሱ
የአየር ንብረት
ኖርዌይ አራት ወቅቶች አሏት፣ ክረምት፡ ጸደይ፡ በጋ እና መኸር።
ኖርዌይ በሰሜኑ ንፍቀ ክበብ ጥግ ላይ የምትገኝ አገር ናት፡፡ አየሯ ከምታስቡት በላይ ተስማሚ ነው:: ለዚህም ከደቡባዊ ውቅያኖስ የማያቋርጥ የሞቀ ውሃ ወደ ኖርዌይ የባሕረሰላጤ ስለሚያመጣ እናመስግናለን። ይህ ማለት፡ በኖርዌይ ያለው የሙቀት መጠን ከሚጠበቀው በላይ ከፍ ያለ መሆኑን ያመለክታል።
የአየር ንብረት ከስፍራ ስፍራ ይለያያል። በባሕር ዳርቻዎች ያለውና በየብሱ ላይ ያለው የአየር ሁኔታም በእጅጉ ይለያያል፡፡ በሰሜናዊ ኖርዌይ ክረምቱ ረጅም፣ ቀዝቃዛና ጨለማ ነው፡፡ በጋው ደግሞ አጭር፣ ነገር ግን በእኩለ ሌሊት እንኳ ደማቅና አስደሳች የጸሐይ ብርሃን የሚታይበት ነው፡፡ በደቡባዊ ኖርዌይ በየብሱ ላይ ብዙ የበረዶ ክምር ሲኖር በባሕር ዳርቻዎቹ ያለው ጥቂት የበረዶ ክምር ነው፡፡ ደቡባዊውና ምሥራቃዊው ኖርዌይ በአጠቃላይ አስደሳች የሆነ ሞቃት በጋ አላቸው። በምዕራባዊው ኖርዌይ የጸደይ ወር የሚመጣው ቀደም ብሎ ነው፡፡ ከምሥራቃዊው ኖርዌይ ይልቅ በምዕራባዊው ክፍል ብዙ ዝናብ ይጥላል፡፡ በመከር ወር ከምዕራባዊው ኖርዌይ ዳርቻ ጀምሮ ባሉት የባሕር ዳርቻዎች ሁሉ ማዕበሎች ይከሰታሉ፡፡
በኖርዌይ የሙቀት መለኪያው (ቴርሞሜትሩ) 25 ዲግሪ ሴንቲ ግሬድ ቢደርስ፡ ሞቃት ነው እንላለን:: በኖርዌይ፡ እስካሁን የተመዘገበው ከፍተኛው የሙቀት መጠን 35.6 ዲግሪ ሴልሲየስ ነው። ይህም የተመዘግበው፡ ሰኔ 20 ቀን 1970፡ በምሥራቅ ኖርዌይ በምትገኝ በኔስቢን ነው። በኖርዌይ የተመዘገበው ዝቅተኛው የሙቀት መጠን ደግሞ፡ ከዜሮ በታች 51.4 ዲግሪ ሆኖ፡ ይኸውም ጥር 1 ቀን 1886 በስሜን ኖርዌይ፡ ብካራስጆክ በተባለው ስፍራ ተመዝግበዋል።
ኣብራችሁ ተወያዩ
- በደንብ የምታውቀውን አገር ግለጽ፣ የአየር ሁኔታ ምን ይመስላል? ሕዝቡ እንዴት ይኖራል? ተፈጥሮና የአየር ሁኔታ በዚያ የሚኖሩ ሰዎች ሕይወት ምን ትርጉም አለው?
- የአገሪቱ የአየር ሁኔታ በሥራ ኑሮ ላይ እና በማሕበራዊ እድገት ላይ የሚያሳድረው ተፅዕኖ እንዳለው ተወያዩ።
- በኖርዌይ በምትኖሩበት አካባቢ ያለው የአየር ሁኔታና የሙቀት መጠኑ ምን ይመስላል?
- በኖርዌይ የአየር ሁኔታው በሕይወት ላይ ምን ምቹ ሁኔታዎችና ገደቦች ይፈጥራል?
ሴት አያት፣ ይኸው አሁን ለቀናት እየዘነበ ነው፡፡ ለምን ያህል ጊዜ የሚቆይ ይመስልሻል?
እናት፡ እንዲህ ነው ብሎ ለመናገር አስቸጋሪ ነው፡፡ ነገር ግን በሬዲዮ የሚተላለፈው የአየር ትንበያ በሳምንቱ መጨረሻ ላይ የአየሩ ሁኔታ እንደሚሻሻል ተናግሯል፡፡
ሴት ልጅ፡ ሁል ጊዜ ስለ አየሩ ሁኔታ ብቻ ነው የምትነጋገሩት!
እናት፡ ኖርዌጅያውያን ስለ አየር ሁኔታ ማውራት ለምን ይወዳሉ፡፡
ለምንድነው ኖርዌጅያውያን ስለ አየር ሁኔታ ማውራት ለምን ይወዳሉ?
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ
በኖርዌይ ውስጥ፡ በብሔራዊ ደረጃ፡ ስንት ቋንቋዎች አሉ?
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ
በኖርወይ ውስጥ ያለው ረዥሙ ወንዝ ማን ይባላል?
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ
በኖርዌይ ውስጥ የተመዘገበው ዝቅተኛው የቅዝቃዜ መጠን ስንት ነው
ትክክል ወይም ስህተት የሆነውን ይምረጡ
መግለጫዎቹን ያንብቡ:: ትክክል የትኛው ነው? ስህተት የትኛው ነው?
ትክክል ወይም ስህተት የሆነውን ይምረጡ
መግለጫዎቹን ያንብቡ:: ትክክል የትኛው ነው? ስህተት የትኛው ነው?
ትክክለኛውን ምስል ይምረጡ፡፡
የትኛው ምስል ነው የመከርን ወቅት የሚያሳየው?