ሕጎች እና ደንቦች፡ በሥራ ዓለም
ሕጎች እና ደንቦች፡ በሥራ ዓለም
በሥራ ዓለም፡ በአሠሪዎች እና በሠራተኞች መከበር ያለባቸው ሕጎች እና ስምምነቶች አሉ። በስቱርቲንግ (ፓርላማ) ያሉ ፖለቲከኞች ሕጎችን ያፀድቃሉ፡ አሠሪዎች እና ሠራተኞች ደግሞ በየድርጅቶቻቸው በኩል ስምምነቶችን ያደርጋሉ። ሕጎቹ ለሁሉም አሠሪዎች እና ሠራተኞች ይመለከታሉ፣ የጋራ ስምምነቶች ግን ስምምነቶችን በነደፉት ኢንዱስትሪዎች ላይ ብቻ ተፈጻሚነት ይኖራቸዋል።
የሥራ አካባቢ ሕግ
ሁሉም አሠሪዎች እና ሠራተኞች የሥራ አካባቢ ሕግን ማክበር አለባቸው። ከሥራ አካባቢ ሕግ ከሚሸፍናቸው መካከል፡
- ሠራተኛ መቅጠር እና ኮንትራቶች፡
- የሥራ ሰዓታት፡
- ከሥራ መቅረት፡
- በጤና፡ ደህንነት እና በአከባቢ (HMS) ላይ መሳተፍ፡
በሥራ ቦታው፡ አሠሪው የሥራ አካባቢ ዋና ኃላፊነት ሲኖርበት፡ ሠራተኛው የሚከተሉትን ግዴታዎች አሉበት፡-
- ጥሩ የሥራ ሁኔታ እንዲፈጠር መርዳት፡
- የሥራ አካባቢን ለማሻሻል የተወሰዱ ውሳኔዎችን ለመተግበር እገዛ ማድረግ/ማበርከት፡
- በድርጅቱ ውስጥ በተደራጀው የደህንነት እና የአካባቢ ሥራ ውስጥ መሳተፍ፡
የዕረፍት ቀናትን የሚመለከት ሕግ፡
ሕጉ ከሚሸፍናቸው መካከል፡ -
- ምን ያህል የዕረፍት ቀናት መብት አለዎት፡
- የበዓላት ዕረፍት የሚወሰዱበት ግዜ፡
- ሥራ ሊቋረጥ ሲል የሚሰጥ የዕረፍት ግዜ ፡
- ህመም በዕረፍት ወቅት፡
- የዕረፍት ቀናት ክፍያ፡
- በኖርዌይ የሚገኙ ሠራተኞች፡ በየዓመቱ ለአራት ሳምንታት እና የአንድ ቀን ዕረፍት የማግኘት መብት አላቸው፣ ሆኖም ብዙ ሰዎች የአምስት ሳምንት ዕረፍት አላቸው።
- በበዓላት ወቅት ደመወዝ ሳይሆን፡ "የዕረፍት ወቅት ክፍያ" ይከፈላል።
- 'የዕረፍት ወቅት ክፍያ" መጠን የሚወሰነው፡ ሠራተኛው ባለፈው ዓመት ባገኘው ገቢ ነው።
ኣብራችሁ ተወያዩ
- በኖርዌይ ውስጥ የሥራ ሕይወትን የሚመሩ ሕጎችን የጻፈው ማን ነው?
- እነዚህን ደንቦች እንዴት ተቀረጹ?
- አሠሪዎችም ሆኑ ሠራተኞች፡ ሕጎቹንና ደንቦቹን በደንብ ማወቅ፡ ኣስፈላጊነቱ ለምንድ ነው?
- ሕጎቹ እና ደንቦቹ የሚሰጡት ነፃነት ነው ወይስ ገደቦች?
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ
የሥራ አካባቢ ሕግን ማክበር ያለበት ማነው?
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ
በኖርዌይ፡ በኣንድ ዓመት ውስጥ፡ ስንት የእረፍት ቀናት የማግኘት መብት አለዎት?
ኣረፍተ ነገሮችን ኣሟሉ፡
የሚናገኘው የእረፍት ጊዜ ደመወዝ የሚወሰነው በ ....
ትክክል ወይም ስህተት የሆነውን ይምረጡ
መግለጫዎቹን ያንብቡ:: ትክክል የትኛው ነው? ስህተት የትኛው ነው?
ትክክል ወይም ስህተት የሆነውን ይምረጡ
መግለጫዎቹን ያንብቡ:: ትክክል የትኛው ነው? ስህተት የትኛው ነው?