የማህበራዊ ደህንነት ሁኔታ

Lærerinnhold

Tips til undervisningen

Snakk sammen

Start med å snakke om hva mennesker trenger og hva som må være på plass for at vi skal leve gode liv (mat, bolig, helse, familie, jobb, utdanning, penger osv.).

Definer velferd: vel = bra, god og ferd = reise Velferd betyr en god reise gjennom livet.

Hvilke behov blir dekket av velferdsgoder i det norske samfunnet?
Hvordan finansieres velferdsgodene i Norge? Se på sammenhengen mellom skatt, avgifter og velferdsgoder.

Utforsk

Mange av velferdsordningene (sykepenger, dagpenger, sosialhjelp, alderspensjon, uførepensjon, barnetrygd o.a.) blir fovaltet av Nav, som til sammen forvalter en tredjedel av statsbudsjettet.

Lover og regler avgjør hvordan Nav disponerer midlene til de ulike velferdsordningene. Det er ikke slik at hver enkelt saksbehandler tar avgjørelser etter sitt eget hode.

Tips til undervisninga

Snakk saman

Start med å snakke om kva menneske treng og kva som må vere på plass for at vi skal leve gode liv (mat, bustad, helse, familie, jobb, utdanning, pengar osv.).

Definer velferd: vel = bra, god og ferd = reise. Velferd tyder ei god reise gjennom livet.

Kva behov blir dekte av velferdsgode i det norske samfunnet?
Korleis blir dei norske velferdsgoda finansierte? Sjå på samanhengen mellom skatt, avgifter og velferdsgode.

Utforsk

Mange av velferdsordningane (sjukepengar, dagpengar, sosialhjelp, alderspensjon, uførepensjon, barnetrygd o.a.) blir forvalta av Nav, som til saman forvaltar ein tredel av statsbudsjettet.

Lover og reglar avgjer korleis Nav disponerer midlane til dei ulike velferdsordningane. Det er ikkje slik at kvar einskild sakshandsamar tek avgjerder etter sitt eige hovud.

Læreplan

Grunnleggende ferdigheter

Digitale ferdigheter
Muntlige ferdigheter

Tverrfaglige tema

Demokrati og medborgerskap

Læreplan i samfunnskunnskap for voksne innvandrere etter integreringsloven

gi eksempler på hva skattefinansiert velferd innebærer

Kjerneelement

Individ og fellesskap
Demokratiforståelse og deltakelse

Læringsaktivitet

Muntlig aktivitet
Utforsking

የማህበራዊ ደህንነት ሁኔታ

ኖርዌይ፡ ለሁሉም በእኩልነት፡ የሚል በማህበራዊ ደህንነት ላይ የተገነባ፡ ሥርዓት ያላት ኣገር ናት። ይህ ማለት፡ ሁሉም ሰዎች፡ በእኩል አስፈላጊ ስለሆኑ፡ ሁሉም ጥሩ ሕይወት የመኖር ዕድል ሊኖራቸው ይገባል። መንግስትና ኣስተዳድሩም የህዝቡ ደህንነትን የመጠበቅ ግዴታ ኣላቸው። ስለዚህ፡ ኖርዌይ የማህበራዊ ደህንነት መንግስት ነው፡ እንላለን።

የማሕበራዊ ደህንነት ሥርዓት በቀላሉ የመጣ አይደለም። የኖርዌይ የማህበራዊ ደህንነት ሁኔታ፡ በ100 ዓመታት ውስጥ፡ በጥቅም ላይ ጥቅም በመጨመር የተገነባ ሥርዓት ነው። ሁሉም የጥቅማ-ጥቅሞች ዕቅዶች ብዙ ገንዘብ ይፈጃሉ። ፖለቲከኞቹ፡ የትኞቹ የጥቅም መርሃ ግብሮች እንደሚዘጋጁ ይወስናሉ። ስለሆነም፡ ለውጥ ሊመጣ የሚችለው፡ የትኞቹ ፓርቲዎች ስልጣን ላይ ባሉና የሕብረተሰቡ የፋይናንስ ኣቅም ላይ ተመስርቶ ነው።

የማህበራዊ ደህንነት ሥርዓት የሚሠራው፡ በተቻለ መጠን፡ ብዙ የመንግስትን ግብር የሚከፍሉ ሠራተኞች ሲኖሩ ነው። ብዙ ሰዎች ደግሞ፡ እራሳቸውን ችለው ገለልተኛ መሆን ይፈልጋሉ። የማህበራዊ ደህንነት ሥርዓት፡ እገዛ ለሚያስፈልጋቸው የገንዘብ እርዳታ ያደርጋል።

የማህበራዊ ደህንነት መርሃግብሮች ምሳሌዎች፡ -

  • በህመም ግዜ የሚደረግ ክፍያ፡
  • በሥራ አጥነት ግዜ የሚሰጥ እገዛ፡
  • ኣዲስ ለመጣ ሰው (ስደተኛ) የሚደረግ እገዛ፡
  • ነፃ ትምህርት፡
  • ነፃ የሆስፒታል እንክብካቤ፡
  • ለልጆች የሚደረግ የገንዘብ እገዛ፡

የማህበራዊ ደህንነት ሥርዓት አጠቃቀም፡ በአብዛኛው በመተማመን ላይ የተመሠረተ ነው። ማዕከላዊው መንግስት እና ህዝብ እርስ በእርስ ይተማመናሉ። ሕዝቡ፡ ማዕከላዊ መንግሥት አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ እንደሚረዳቸው ያምናሉ፣ ማዕከላዊው መንግሥት ደግሞ፡ ሕዝቡ የደህንነት ሥርዓቱን አላግባብ እንደማይጠቀሙበት ይተማመናል።

የኖርዌይ የሠራተኛ እና የደህንነት አስተዳደር (NAV)

በኖርዌይ እያንዳንዱ ኣስተዳደር የናቭ ጽሕፈት ቤት አለው። ሥራ ለማግኘት ብቃት ይኖረን ዘንድ እርዳታ፣ በሕመም ጊዜ ወይም በሌሎች አስቸጋሪ ጊዜ፡ የገንዘብ ድጋፍ፡ ካስፈለገን የናቭ ጽሕፈት ቤት ሊረዳን ይችላል። ናቭ፡ በኖርዌይ ለሚገኙት የማህበራዊ ደህንነት ተቋማትን ኃላፊነት አለበት። በተጨማሪም፡ ናቭ፡ ማህበራዊ እርዳታን በማካሔድ፡ በሥራ አጥነት ግዜ የሚከፈል ገንዘብ፣ በህመም ግዜ ደመወዝ፣ የጡረታ ክፍያ፣ ለልጆች ዋስትና ተብሎ የተመደበው ሒሳብ እና ለገንዘብ እንክብካቤ መርሃ ግብር ለመሳሰሉት ሌሎች ነገሮች ኃላፊነት አለበት።

ናቭ ከብሔራዊ በጀት በግምት አንድ ሦስተኛ ያክል ያስተዳድራል፡ ወደ 22,000 የሚጠጉ ሠራተኞች አሉት።

የማህበራዊ ደህንነት ማህበረሰብ፡ የሥራ ዕድል ይፈጥራል

የማህበራዊ ደህንነት ሥርዓት፡ ከፍ ያለ የሠራተኞች መጠን ያስፈልጉታል። በኣሁኑ ግዜ፡ በኖርዌይ ከሚሠሩት ሰዎች ሰላሳ በመቶው የሚሆኑ በመንግስት ዘርፍ ውስጥ ይሠራሉ። የኖርዌይ ደህንነት ማህበረሰብ በደንብ እንዲተገበር፡ ብዙ የተለያዩ የሙያ ዘርፍ ያላቸው ሰራተኞች ያስፈልጉታል።

ለምሳሌ፦

  • መምህራን: የቢሮ ሠራተኞች: የፅዳት ሠራተኞች እና ሌሎች የትምህርት ቤት ሠራተኞች፣
  • ዶክተሮች፡ ነርሶች፡ የጤና ባለሙያዎች፡ የቢሮ ሠራተኞች፡ የጽዳት ሠራተኞች እና ሌሎች ሌሎችም በሆስፒታሎች እና በአረጋውያን ቤቶች ውስጥ
  • የጉዳይ ኣስፈጻሚዎች፣ የጽሕፈት ቤት ሠራተኞች እና ሌሎች የናቭ ሠራተኞች።

ኣብራችሁ ተወያዩ

  • እኩልነት ምንድን ነው? ደህንነት ምንድነው? ጥሩ ሕይወት ምንድን ነው?
  • በኖርዌይ ኅብረተሰብ ያለውን ማህበራዊ ደህንነት ሥርዓት ተወያዩ።
  • በኖርዌይ የማህበራዊ ደህንነት ሥርዓት፡ የናቭ (NAV) አስፈላጊነት ተወያዩ።
  • ናቭ፡ የኖርዌይ ብሔራዊ በጀት አንድ ሦስተኛ ያስተዳድራል። ይህ ስለ ማህበርዊ ደህንነት ሥርዓት ምን ያመለክታል? እንዲሁም ገንዘቡ ከየት ይመጣል?
Lege sjekker blodtrykk. Foto.
AdobeStock
Illustrasjon, fire personer sitter på stabler av mynter.
AdobeStock

ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ

ለኖርዌይ ሕዝብ የማህበራዊ ደህንነት ጥቅማ ጥቅሞችን የማቅረብ ዋና ኃላፊነት ያለበት ማነው?

ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ

የማህበራዊ ደህንነት ጥቅሞች ምሳሌዎች ምንድናቸው? ከአንድ በላይ መልስ መምረጥ ይቻላል።

ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ

የ NAV ሥራዎች ምንድናቸው? ከአንድ በላይ መልስ መምረጥ ይቻላል።

ትክክል ወይም ስህተት የሆነውን ይምረጡ

መግለጫዎቹን ያንብቡ:: ትክክል የትኛው ነው? ስህተት የትኛው ነው?

ናቭ፡ በኖርዌይ ለሚገኙት ሁሉም የጥቅም መርሃግብሮች፡ ኃላፊነት አለበት።
በኖርዌይ፡ ሦስት የናቭ ቢሮዎች አሉ። በኦስሎ፣ በትሮንድሃይም እንዲሁም በበርገን ይገኛሉ።
በኖርዌይ ከሚገኙት ሰራተኞች መካከል፡ ግማሽ ያህሉ በመንግስት መስርያ ቤቶች ይሰራሉ።
የማህበራዊ ደህንነት ጥቅማ ጥቅሞችን ኣጠቃቀም፡ በአብዛኛው በመተማመን ላይ የተመሠረተ ነው።
የማህበራዊ ደህንነት ሥርዓት፡ ብዙ ሰዎች በማሰራትና ግብር በመክፈል ላይ የተመሠረተ ነው።

ትክክል ወይም ስህተት የሆነውን ይምረጡ

መግለጫዎቹን ያንብቡ። ትክክል ምንድን ነው? ስህተት ምንድን ነው

የማህበራዊ ደህንነት ሥርዓት ተጠቃሚ የሆኑ ሰዎች፡ ነፃ ምግብ እና መጠለያ ያገኛሉ።
ሥራ ለማግኘት ብቁ ለመሆን እርዳታ ካስፈለገን፡ የናቭ ጽ/ ቤት ሊረዳን ይችላል።
የትኞቹ የጥቅም መርሃ ግብሮች ተግባራዊ እንደሚሆኑ የሚወስኑ፡ ፖለቲከኞቹ፡ ናቸው።
በኖርዌይ ያለው የማህበራዊ ደህንነት ሥርዓት መርሃግብሮች፡ ሕገ -መንግስቱን ሳይለወጥ፡ ሊለውጡ ይችላሉ።
የማህበራዊ ደህንነት መንግስት፡ እርዳታ ለሚያፈልጋቸው፡ የገንዘብ ድጋፍ ሊሰጥ ይችላል።

ትክክለኛውን ምስል ይምረጡ

በመንግሥት ዘርፍ ውስጥ የትኞቹ ሙያዎች የተለመዱ ናቸው? ከአንድ በላይ ምስል መምረጥ ይችላሉ።