የነዋሪዎች መተዳደሪያ ደንቦች
የነዋሪዎች መተዳደሪያ ደንቦች
ስደተኛ ማለት የሌላ አገር ተወላጅ ሆኖ ኑሮውን በኖርዌይ ያደረገ ማለት ነው። በኖርዌይ የሚኖሩ ስደተኞች የተለያዩ የሥራ ፈቃድና የተለያዩ መብቶች አሉዋቸው።
- ከአውሮፓ ሕብረት እና ከአውሮፓ ኢኮኖሚ ሃገራት የመጡ ስደተኞች የመኖሪያ ፈቃድ ማመልከቻ ሳያስገቡ ሥራ መሥራት ይችላሉ፣ሆኖም ግን በፖሊስ ሊመዘገቡ ይገባል፡፡ ምዝገባው በኮምፒውተር የሚከናወን ይሆናል።
- የመልሶ ማቋቋሚያ ስደተኞች ወይም የኮታ ስደተኞች ከ UNHCR (UN) ጋር በመስማማት ወደ ኖርዌይ ይመጣሉ። ወደ ኖርዌይ ሲመጡ ጊዝያዊ የመኖርያ ፈቃድ ይቀበላሉ።
- ከትውልድ ሃገራቸው በዘር፣በሃይማኖት፣በዜግነታቸው፣በጾታዊ አመለካከታቸው በሚገጥማቸው ችግር፣አሊያም በፖለቲካ አቋማቸው ምክንያት ስደት ለሚገጥማቸው ሰዎች ኖርዌይ ጥገኝነት ትሰጣለች። ጥገኝነት ጠያቂዎቹ በራሳቸው ወደ ኖርዌይ በመምጣት የጥገኝነት ጥያቄያቸውን ማቅረብ ይችላሉ። የጥገኝነት ጥያቄያቸውም ጠንካራ የሆነ የሰብአዊ አቅርቦት ሁኔታ ከግምት ውስጥ በማስገባት ተቀባይነት ሊያገኝም ላያገኝም ይችላል።
- በኖርዌይ የመኖሪያ ፈቃድ ያገኘ የቤተሰብ አባል ካለ ለቀሪዎቹ የቤተሰቡ አባላት የመኖሪያ ፈቃድ ጥያቄ በማቅረብ ከቤተሰቦቹ ጋር መቀላቀለ ይችላል።
በጠንካራ ሰብአዊ ጉዳዮች እና የሰፈራ ስደተኞች ምክንያት ጥገኝነት/መኖሪያ የተሰጣቸው ሰዎች ስደተኞች በመባል ይታወቃሉ።
ሰደተኞች በኖርዌይ ውስጥ ለመጀመሪያዎቹ ሶስት ወይም አምስት አመታት ጊዜያዊ የመኖሪያ ፍቃድ ይሰጣቸዋል። ፈቃዱ በአጠቃላይ በየአመቱ መታደስ አለበት። ከሶስት ወይም ከአምስት አመታት በኋላ፡ ለቋሚ የመኖሪያ ፈቃድ ማመልከት ይችላሉ። ከስድስት፡ ሰባት ወይም ስምንት ዓመታት በኋላ ለኖርዌይ ዜግነት ማመልከት ይችላሉ።
ምንጭ፦ www.udi.no
በ UDI ድህረገጽ ላይ መረጃን መሙላት እና የተዘጋጀ መመሪያ ማግኘት ይችላል። አግባብነት ያላቸው ማመልከቻዎች በዚህ ድህረ ገጽ በኩልም ሊቀርቡ ይችላሉ። ድህረገጹ በኖርዌይ ቋንቋን እና በእንግሊዝኛ ይገኛል።
ኢንተርነት
ኣብራችሁ ተወያዩ
- በሃገሪቱ ውስጥ ማን መኖር እንዳለበት ወሳኙ አካል ማነው?
- ወደ ትውልድ አገሩ መመለስ የሚፈልግ ሰው ሁሉ መመለስ ይችላልን?
- በኖርዌይ የመኖሪያ ፈቃድ የጠየቀ ሁሉ የማያገኝበት ምክንያት ምንድነው?
- ሃገሪቱ ስደተኞችን ስትቀበል ምን ኃላፊነት አለባት? ስደተኞችስ ያለባቸው ኃላፊነት ምንድነው?
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ
ስደተኛ የሚለው ቃል ምን ማለት ነው?
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ
ከአውሮፓ ሕብረት /አውሮፓ የኢኮኖሚ ትብብር አገራት የሚመጡ ሰዎች የመኖሪያ ፈቃድ ሳያወጡ የስራ ፈቃድ ማግኘት ይችላሉ፡፡
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ
በመኖሪያ ፈቃድ ጉዳይ የሚሞላ ቅጽ ማግኘት የምትችሉት ከየትኛው ድረ ገጽ ላይ ነው?
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ
በኖርዌይ የመኖርያ ፈቃድ ያለው ቤተሰብ አባል ያላቸው ሰዎች ለምን አይነት ጉዳይ ማመልከት ይችላል?
ትክክል ወይም ስህተት የሆነውን ይምረጡ
መግለጫዎቹን ያንብቡ:: ትክክል የትኛው ነው? ስህተት የትኛው ነው?