የአሁኗ ኖርዌይ
የአሁኗ ኖርዌይ
ዛሬ ኖርዌይ ዘመናዊና መድብለ ባሕል ኣገር ናት። የኑሮ ደረጃዋ ከፍተኛ ሲሆን ህብረተሰቡ በዘመናዊ ቴክኖሎጂዎች የሚመራ ነው። በተጨማሪም፡ ኖርዌይ የተባበሩት መንግስታት፣ ኔቶ እና አውሮጳ የቁጠባ ሕብረት በመሳሰሉ ውድቦች በመተባበር ትሰራለች።
ዛሬ በኖርዌይ ማህበረሰብ ውስጥ ጠቃሚ ስለሆኑት እሴቶች፡ በዘፈቀደ ሰውን ብንጠይቅ፡ ምናልባት ከአንዳንድ በጣም አስፈላጊ እሴቶች፡ እኩልነት እና በራሳቸው ህይወት የመወሰን ነፃነት ናቸው ብለው ይመልሱ ይሆናል።
እንደ አብዛኛዎቹ አገራት እና ማሕበረሰብ፡ በኖርዌይ ውስጥም ብዙ ሕጎች አሉ፡፡ ሕጎቹም በአብዛኛው መሰረታቸውን ያደረጉት በሰዎች መካከል ስላለ እኩልነት እና ለሰዎች ብዙ መብት የሚሰጡ መመሪያዎች ናቸው፡፡ ቀጥሎ ዛሬ ያለውን የኖርዌይ ማሕበረሰብ መልክ በኖርዌይ ይኖር ዘንድ አስተዋጽኦ ያደረጉትን ጥቂት ነገሮች እንመለከታለን፡፡ ታላላቅ ፓለቲካዊ እንቅስቃሴዎች ዛሬ ላለው የአሁኗ ኖርዌይ እድገት ለማምጣት እንደመሳሪያ አገልግለዋል፡፡ በተለይ የሰራተኞች እንቅስቃሴና የሴቶች ንቅናቄ ጠቃሚ ነበር፡፡
የሰራተኞች ንቅናቄ
የኖርዌያውያን የሰራተኞች ንቅናቀቄ ከ17ኛው ክፍለ ዘመን የሚጀምር ሲሆን ይበልጥ የተደራጀው ግን በኢንዱስትሪዎች ውስጥ ከተፈጠረው የሥራ ቁጥር እድገት ጋር በተያያዘ ከ1880ዎቹ በኋላ ባለው ጊዜ ነው፡፡ ንቅናቄው ትልቅ ተጽእኖ መፍጠር የጀመረው ከ1900ዎቹ መጀመሪያ ጀምሮ ነው፡፡ የሰራተኞች ንቅናቄ ጥረት የተሻለ የሥራ ሁኔታ፣ አጭር የሥራ ሰአትን ጨምሮ፣ የሥራ ቦታ ደሕንነት፣ የጤና መድኅንና የሥራ እድል ላላገኙ ሰዎች የገንዘብ ድጋፍ የማግኘት መብቶችን አጎናጽፏል፡፡ ዛሬ፡ ግማሽ ያህሉ ተቀጣሪ የሰራተኞች ማሕበር አባል ናቸው፡፡
የሴቶች ንቅናቄ
የሴቶች ንቅናቄ በማሕበረሰቡ ውስጥ ላለው የሴቶች መብት እና ሴቶች ከወንዶች እኩል የሥራ እድል እንዲኖራቸው ለማድረግ ታግሏል፡፡ የሴቶች ንቅናቄ በኖርዌይ ከ1880ዎቹ ጀምሮ በንቃት እየተንቀሳቀሰ ያለ ሲሆን፡ ከ1913 ዓ.ም. ጀምሮ የመምረጥ መብት ተሰጥቶዋቿል።
የሴቶች መብት ትግል እንደገና በ1970ዎቹ ፍጥነት ጨምሯል። የእርግዝና መቋረጥን የሚመለከት ህግ (የፅንስ ማስወረድ ሕግ) በ1978 ጸድቋል። ከሌሎች ነገሮች በተጨማሪ፡ ይህ ሕግ፡ ሴቶች እስከ 13ኛው ሳምንት እርግዝና ድረስ ፅንስ የማስወረድ መብት ይሰጣቸዋል። የመፋታት መብት፣ የወሊድ መቆጣጠሪያ፣ የተመረጠ ፅንስ ማቋረጥ እና ሴቶች በራሳቸው አካል ላይ የመወሰን መብት ለሴቶች እንቅስቃሴ ወሳኝ ጉዳዮች ነበሩ።
ዛሬ፡ ወንዶችና ሴቶች የትምህርትና የሥራ፣ የንብረትና ውርስ፣ የጤና አጠባበቅና የመልካም ጤንነት መብት አላቸው። የአንድ ሰው ጾታ ከአሁን በኋላ ምን መብቶች እና እድሎች እንዳሉ አይገልጽም። ሆኖም አንዳንዶች፡ በተወሰኑ አካባቢዎች ሙሉ እኩልነት ከመምጣቱ በፊት የምንጓዝበት መንገድ አለን ይላሉ።
ነዳጅ
በ1960 ዎቹ ውስጥ፡ በርካታ ኩባንያዎች በኖርዌይ የባህር ዳርቻ ላይ ነዳጅ እና ጋዝ ለመፈለግ ፍላጎት ኣስይተው ነበር። የመጀመሪያው ነዳጅ የተገኘው በ1967 በሰሜን ባህር ሲሆን ኖርዌይ ከዚያን ጊዜ ጀምራ የነዳጅ ኣምራች ሀገር ወደመሆን እያደገች ነው። የነዳጅ ኢንዱስትሪ ለኖርዌይ ኢኮኖሚ በጣም አስፈላጊ ነው። ልክ ከ50 ዓመታት በፊት በውሃ የኤሌክትሪክ ኃይል የሚያመነጩ ተቋማት የሕዝብ ንብረት እንደሆኑ፡ የነዳጅ ዘይት ሃብትም የሕዝብ ንብረት ነው። የግል ኩባንያዎች በነዳጅ ፍለጋ፣ ቁፋሮ እና የማምረት መብቶችን ለተወሰነ ጊዜ የመሳተፍ መብት ኣላቸው። ዛሬ በኖርዌይ ማህበረሰብ ውስጥ በነዳጅ ኢንዱስትሪው ላይ የክርክር እየተካሄደ ነው። በሕዝቡ መካከልም ይህ ኢንዱስትሪ በተፈጥሮ እና በአካባቢው ላይ ስለሚያስከትላቸው መዘዝ ኣለመስማማት ኣለ።
ኣብራችሁ ተወያዩ
- ከ1850 በፊት 15 በመቶው ህዝብ በከተሞች ውስጥ ይኖሩ ነበር። በ1900 አካባቢ 35 በመቶው ህዝብ በከተሞች ይኖር የነበረ ሲሆን፡ ዛሬ 80 በመቶ የሚሆነው የኖርዌይ ህዝብ በከተሞች ነው። እርስዎ በሚያውቁት በሌሎች አገሮች፡ ተመሳሳይ አዝማሚያ አለ?
- ከገጠር ወደ ከተማ ስለሚገቡ ሰዎች አወንታዊ እና አሉታዊ ገጽታዎች ተወያዩ።
- አሁን ላለችው ኖርዌይ እድገት የሰራተኞች ንቅናቄ ያመጣውን ጠቀሜታ ተነጋገሩበት፡፡ እናንተ በምታውቋቸው አገሮች ውስጥ ተመሳሳይ እድገት አለን?
- የሴቶች ንቅናቄ ለአሁኗ ኖርዌይ እድገት ያመጣውን ጠቀሜታ ተነጋገሩበት፡፡ በምታውቋቸው አገራት ውስጥስ ተመሳሳይ እድገት ነበረን?
- አሁን እና ቀድሞ ስለነበረው የሴቶች መብት በኖርዌይ እንዲሁም በሌሎች ቦታዎች ምን እንደሚመስል ተነጋገሩ፡፡
- ኖርዌይ የአውሮጳ ሕብረት አባል አገር አለመሆኗ ለሃገሪቱ ምን ኣገዳስነት ኣለው?
- በ1960ዎቹ መጨረሻ በኖርዌይ ሰሜናዊ የባሕር ክፍል ነዳጅ እና የተፈጥሮ ጋዝ መገኘቱ ኖርዌይን ሃብታም አገር እንድትሆን አድርጓታል፡፡ ይሁን እንጂ የነጻ ትምህርት መብት፣ ነፃ ወይም ድጎማ ያለበት የጤና እንክብካቤ፣ አጭር የሥራ ሰአት፣ የጤና መድኅን ወዘተ..የመሳሰሉት መብቶች ነዳጅ ከመገኘቱ በፊት ተደርጓል። ለእነዚህ መብቶች መረጋገጥ መሰረት ስለሆኑት እሴቶች ተነጋገሩ።
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ
ምን ያህሉ የኖርዌይ ሰራተኞች፡ የሰራተኛ ማህበር አባላት ናቸው?
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ
በሰሜናዊው ባሕር የነዳጅ ዘይት የተገኘው መቼ ነበር?
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ
በ 1978 የወጣው የፅንስ ማስወረድ ህግ ለሴቶች ምን የማድረግ መብት ሰጣቸው?
ትክክል ወይም ስህተት የሆነውን ይምረጡ
መግለጫዎቹን ያንብቡ። ትክክል የትኛው ነው? ስህተት የትኛው ነው?
ትክክል ወይም ስህተት የሆነውን ይምረጡ
መግለጫዎቹን ያንብቡ። ትክክል የትኛው ነው? ስህተት የትኛው ነው?