አሉታዊ ማሕበራዊ ቁጥጥር
አሉታዊ ማሕበራዊ ቁጥጥር
ማህበራዊ ቁጥጥር የግለሰቡን ባህሪ እና የአኗኗር ዘይቤን የሚመለከት ማዕቀፍን ለመግለጽ የሚያገለግል ቃል ነው። ለምሳሌ: ወላጆች ልጆቻቸውን ሲያሳድጉ በሕይወታቸው ዙሪያ ማዕቀፍ ያዘጋጃሉ: እና ማህበረሰቡ ተቀባይነት ያለው ባህሪን በጽሁፍ እና ባልተፃፉ ደንቦች እና ሕጎች ያስቀምጣል።
አንዳንድ ጊዜ ልጆች እና ወጣቶች አልፎ ተርፎም ጎልማሶች የቅርብ ቤተሰቦቻቸው የሚወዷቸው ሕጎች በጣም ጥብቅ ናቸው ብለው ያስባሉ። ደንቦቹ እንደ ምክንያታዊነት ይቆጠራሉ እና ማህበራዊ ቁጥጥር እንደ አሉታዊ ነገር ይታያል። ወላጆች ወይም ሌሎች የቅርብ ዘመዶች ያስቀመጧቸው ማዕቀፎች ከህብረተሰቡ ጋር ግጭት ውስጥ ሊሆኑ ይችላሉ, አለበለዚያ እንደ ተፈጥሯዊ ናቸው። አሉታዊ ማህበራዊ ቁጥጥር የግለሰቡን የግል ነፃነት እና ነጻ ህይወት የመምራት መብትን ሊነፍግ ይችላል። አሉታዊ ማህበራዊ ቁጥጥር ልጆች እና ወጣቶችን በኖርዌይ ማህበረሰብ ውስጥ ተሳታፊ እንዳይሆኑ ያደርጋቸዋል።
ኣብራችሁ ተወያዩ
መርሐት 14 አመቷ ነው። ወደ መለስተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ገብታለች፡፡ በልጅነቷ በነጻነት ነው የኖረችው፡ ወላጆቿም ብዙ ቁጥጥር አያደርጉባትም ነበር፡፡ አሁን ወደ ጉርምስናው እድሜ በመግባቷ ቤተሰቦቿ ጠበቅ እያሉ እንደሆነ ታውቋታል፡፡ወደ ጓደኞቿ ቤት እንደትሄድ አይፈቀድላትም፣ ከትምህርት ቤት መልስ በቀጥታ ደግሞ ወደቤት መምጣት ይኖርባታል። አባቷ አጭር ቁምጣ አድርጋ መጫወቷ ስላላስደሰተው የእጅ ኳስ ጨዋታም መጫወት እንድታቆም አድርጓታል። እናቷም በየምሽቱ ከማን ጋር እንደተደዋወለችና መልእክት እንደተለዋወጠች ለማየት ስልኳን ትፈትሻለች፡፡
ወንድሟ የሁለት አመት ታላቋ ነው። ከእርሱ ላይ ያን ያህል ጠበቅ ያሉ አይደሉም። መርሐት ቤተሰቦቿ በእርሷ ላይ ያላቸው እምነት እንደተሸረሸረ በማሰብ በጣም ተበሳጭታለች። ሁል ጊዜ ካልተቆጣጠሯት የሆነ ስህተት ልትፈጽም እንደምትችል በእርግጥ እያሰቡ ነው?
ስለ መርሐት ሁኔታ ተወያዩ።
- ቤተሰቦቿ ጉዳዩን የሚመለከቱት እንዴት ነው?
- የዚህ አይነቱ ቁጥጥር ምን አይነት መዘዝ ሊያስከትል ይችላል?
- መርሐት እና ወላጆቿ የእለት ተእለት ኑሮአቸውን እንዴት ሊያስተካክሉት ይችላሉ?
ከሁለት አመት በኋላ፡
መርሐት የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ጀምራለች። ሕይወቷም ከቀድሞው የበለጠ አስቸጋሪ ሆኗል። በዕለት ተዕለት ህይወቷ እና በኖርዌይ ትምህርት ቤት ጓደኞቿ መካከል ትልቅ ልዩነት አለ። በክፍሏ ውስጥ ያሉ ሌሎች ልጃገረዶች ብዙውን ጊዜ ከትምህርት በኋላ ተገናኝተው የሚያዝናኑ ነገሮችን በመፍጠር ይጫወታሉ። በሳምንቱ መጨረሻም በጓደኞቻቸው ቤት እርስ በእርሳቸው ቤት ይተኛሉ እና ስለ ፋሽን እና ወንዶች ልጆች ይነጋገራሉ። መርሐትም ከኖርዌጃውያን ማህበረሰብ ቀስ በቀስ እየወጣች እንደሆነች ይሰማታል። ቤተሰቦቿን ትወዳቸዋለች፡ ነገር ግን ቁጥጥር እንደበዛባትና ወጥመድ ውስጥ እንደገባች አስባለች። በትምህርት ቤቷ አናሳ ብሔረሰብ አማካሪ እንዳለ ሰምታለች። ታዲያ፡ ልታናግራት መድፈር አለባት?
- መርሐትን ምን ትመክሯታላችሁ?
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ
ማሕበራዊ ቁጥጥር ምን ማለት ነው?
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ
አሉታዊ ማሕበራዊ ተጽእኖ ምን ማለት ነው?
አረፍተ ነገሩን አሟሉ፡፡
አንድ ሰው የእርሱ በሆኑ የቅርብ ቤተሰቦቹ ያወጡለት ደንብ ጥብቅ እንደሆነ ሲያስብ………….
አረፍተ ነገሩን አሟሉ፡፡
አሉታዊ ማህበራዊ ቁጥጥር ……..ሊሆን ይችላል፡፡
ትክክል ወይም ስሕተት የሆነውን ይምረጡ ፡፡
መግለጫዎቹን ያንብቡ:: ትክክል የትኛው ነው? ስህተት የትኛው ነው?