መካከለኛው ዘመንና ውህደቶች
መካከለኛው ዘመንና ውህደቶች
ክርስትና ወደ ኖርዌይ መጣ
ክርስትና ወደ ኖርዌይ ከመምጣቱ ከረጅም ጊዜ በፊት በደቡብ አውሮፓ ውስጥ ዋነኛው ሃይማኖት ነበር። በ1030 ኦላቭ ሃራልድሰን በስቲክልስታድ ጦርነት ሲገደል ልጁ አባቱን ቅዱስ ለማድረግ የቤተ ክርስቲያንን እርዳታ ጠየቀ። ኃያላን ገበሬዎችና አለቆች እየበዙ ክርስትናን ቀስ በቀስ ተቀብለዋል። በስልጣን ላይ ያሉት ወደ አዲሱ እምነት ሲሸጋገሩ፣ ብዙ ተራ ሰዎች ይህንን ተከተሉ። ቤተ ክርስቲያኒቱ ብዙም ሳይቆይ ትልቅ ኃይል ኣገኘት።ሰዎች ለቤተክርስቲያን ግብር መክፈል ጀመሩ፡ ብዙዎቹም መሬታቸውን ለቤተ ክርስትያን ሰጡ። ሃይማኖት በተራ ሰዎች ሕይወት ውስጥ ትልቅ ስፍራ ያዘ።
"ጥቁር ሞት"
ምንም እንኳን ሞት እና በሽታ ቢስፋፋም፡እ.ኤ.አ ከ1000 እስከ 1300 ዓ.ም. ባለው ጊዜ ውስጥ፡ የኖርዌይ ህዝብ ቁጥር ከ150,000 ወደ 400,000 አካባቢ አድጓል።ከሚወለዱት ግማሽ ያህሉ ህፃናት የመጀመሪያ ልደታቸው ሳያከብሩ ሞተዋል። እንዲሁም፡ ብዙ ሴቶች በወሊድ ምክንያት ሞተዋል።
በ14 ኛው ክፍለ ዘመን አጋማሽ ላይ ወረርሽኝ ተከስቶ ነበር። ይህ ወረርሽኝ “ጥቁር ሞት” ተብሎ የሚጠራው በሽታው የተያዙ ሰዎች በአካላቸው ላይ ትላልቅ ሰማያዊና ጥቁር እባጮች ይወጣ ስለነበረ ነው። በዚህ በሽታ የተያዙ አብዛኛዎቹ ሰዎች በጥቂት ቀናት ውስጥ ይሞቱ ነበር። በመላው ዓለም፡ ከ75 እስከ 200 ሚሊዮን ሰዎች በተከሰተው ወረርሽኝ፡ እንደሞቱ ይታመናል። ከአውሮፓ ህዝብ ግማሽ ያህል ሕዝብ በዚህ በሽታ ምክንያት ኣልቀዋል። ከኖርዌይ ሕዝብ፡ አንድ ሶስተኛው በበሽታው ሞተዋል።
ሥልጣን በቤተ ክርስቲያን፣ በንጉሡና በመኳንንት እጅ።
በመካከለኛው ክፍለ ዘመን አብዛኛው ሰው የሚተዳደረው በግብርና ሥራ ነበር፡፡ በቫይኪንጎች ዘመን አብዛኛዎቹ ገበሬዎች እርሻቸውን እና መሬታቸውን የራሳቸው ነበሩት፣ አሁን ግን፡ ሰዎች ለቤተ ክርሰቲያን፣ ለንጉሡ እንዲሁም ለባለ ርስቶች ግብር መክፈል ነበረባቸው። ግብር መክፈል ያልቻለ ማንኛውም ሰው ደግሞ መሬቱን ማስረከብ ነበረበት። ስለሆነም፣ ቤተ ክርስቲያን፡ ንጉሡና መኳንንቶቹ እየበለጸጉ ሲሔዱ፣ ተራው ሕዝብ እየደኸየ መጣ።
በኖርዌይ ውስጥ የመጀመሪያዎቹ ከተሞች የተመሰረቱት በዚህ ወቅት ነው። ትላልቆቹ ከተሞች፣ በርገን (ብዮርግቪን)፡ ትሮንደሄም (ኒዳሮስ)፡ ኦስሎ፡ ስታቫንገር እና ቶንስበርግ ነበሩ።
ውሕደት
በ14ኛው ክፍለዘመን የዳኒሾች ተጽእኖ በኖርዌይ ላይ እያየለ መጥቶ የነበረ ሲሆን ኖርዌይ እ.ኤ.አ ከ1397 ዓ.ም ጀምሮ ከዴንማርክና ከስዊድን ጋር ውሕደት ፈጥራ ነበር፡፡ ይህ ውሕደት በአንድ ንጉሥ ስር የሚተዳደር ነበር፡፡ ስዊድን ከውህደቱ ቆየት ብላ የወጣች ሲሆን ዴንማርክና ኖርዌይ ግን እስከ 1814 ዓ.ም ድረስ አብረው ዘልቀዋል፡፡ ውሕደቱ ይመራ የነበረው ከዴንማርክ ነበር። የዴንማርክ ዋና ከተማ የሆነችው ኮፐንሃገን የውህደቱ የባሕል ማዕከል የነበረች፣ ስለሆነም ኖርዌጃኖች የዴንማርክ ቋንቋ ኣንበበው ይጽፉ ነበር። የኖርዌይ ገበሬዎች በኮፐንሃገን ለሚገኘው ንጉሥ ግብር ይከፍሉ ስለነበር፡ ኖርዌጃኖች ትምህርታቸውን ለመከታተል ወደዚያ ይሄዱ ነበር።
የፕሮቴስታንት እምነት
በ1517 ዓ.ም ሃይማኖታዊ አመፅ ተካሄዶ ነበር።ጀርመናዊው መነኩሴ ማርቲን ሉተር የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያንን ስልጣንን ተገዳደረ። ማርቲን ሉተርም የሚደግፉ ሰዎች ቁጥራቸው እየተበራከተ ነበር። ፕሮቴስታንት የሚለውን ስያሜ የያዙት ተቃውመው በመውጣታቸው ነበር። በሰሜን አውሮፓ የነበሩ በርካታ ነገሥታትም ማርቲን ሉተርን ደግፈዋል። የዴንማርክ ንጉስ ወደ ፕሮቴስታንት እምነት ኣዞረ። ፕሮቴስታንታዊነት፡ በኖርዌይ ውስጥ፡ የመንግስት ቤተ ክርስትያን መሆኑ እስካቆመበት፡እስከ 2012 ድረስ የመንግስት ሃይማኖት ነበር።
ኣብራችሁ ተወያዩ
- ይህ የታሪክ ወቅት በአገራችሁ ምን ይመስል ነበር?
- በትውልድ አገራችሁ "ጥቁር ሞት" ተከስቶ ነበርን?
- በኣሁኑ ጊዜ ከዚህ ጋር የሚመሳሰል ሁኔታ ገጥሟችሁ ያውቅ ይሆን?
- ሃይማኖት በሰዎች ሕይወት ውስጥ ትልቅ ቦታ ነበረው። ቤተ ክርስቲያን ብዙ ኃይል ነበራት። ይህ በሰዎች ላይ ምን ተጽዕኖ ያሳደረ ይመስልሃል? ዛሬ ያለው ሁኔታ ምን ይመስላል?
- ከዴንማርክ ጋር የነበረው ውሕደት የኖርዌይን ሕዝብና የሃገሪቱን ማሕበረሰብ እድገት በምን መልኩ እንደነካው ታስባላችሁ?
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ
በጥቁር ሞት ዘመን፡ በሞት የተነጠቀው ምን ያክሉ የኖርዌይ ሕዝብ ነበር ?
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ
በየትኛው ዘመን ነበር ኖርዌይ ከስዊድን እና ዴንማርክ ጋር ተዋሕዳ የነበረችው?
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ
በ1500 ዎቹ መጀመሪያ ላይ ጀመርናዊው መነኩሴ ማርቲን ሉተር ምን ነበር የተቃወመው?
ትክክል ወይም ስህተት ይምረጡ
መግለጫዎቹን ያንብቡ። ትክክል የትኛው ነው? ስህተት የትኛው ነው?
ትክክል ወይም ስህተት የሆነውን ይምረጡ
መግለጫዎቹን ያንብቡ። ትክክል የትኛው ነው? ስህተት የትኛው ነው?