ዲሞክራሲ በኖርዌይ
ፊልሙን ይመልከቱ
ዲሞክራሲ በኖርዌይ
ማዕከላዊው መንግሥት፣ የክልል ባለስልጣናትና የኣከባቢ መስተዳደሮች
- በኖርዌይ 15 ክልሎች እና 356 የኣከባቢዎች ኣስተዳደሮች (ኮሙነዎች) አሉ(1.1.2024)፡፡
- ክልሎች እና የኣከባቢዎች ኣስተዳደሮች የተለየ በመልክአምድራዊ አካባቢዎችና መስተዳደሮች ቢኖርዋቸውም፣ በኣንድ የፖቲካዊ ተጠሪነት ስር ናቸው፡፡
- አብዛኛውን ነገር የሚወስነው ማዕከላዊው መንግሥት ቢሆንም፡ የክልሉን እና የኣከባቢዎች ኣስተዳደሮች በተወሰኑ ጉዳዮች ዙሪያ የራሳቸው አስተዳደር አላቸው፡፡
- ማዕከላዊው መንግሥት የክልሉን እና የኣከባቢዎች ኣስተዳደሮች ማዕቀፍ ያዘጋጃል፡፡
- ማዕከላዊው መንግሥት አገሪቱን በሙሉ ያስተዳድራል፣ የክልሉን እና የኣከባቢዎች ኣስተዳደሮች ግን የአካባቢ ጉዳዮችን ብቻ ይወስናሉ።
ከማእከላዊ መንግሥት ሃላፊነቶች ጥቂቶቹ፡
- የውጪ ፖሊሲ፣
- ሆስፒታሎችን፣
ሕግ ማውጣት፣ - ሥርዓተ ትምህርት፣
ከክልሉ ኃላፊነቶች ጥቂቶቹ ፡
- የከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት
- የክልሉ መንገዶች
የኣከባቢ መስተዳድሮች ሃላፊነቶች ጥቂቶቹ
- አንደኛና መለስተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች፡
- መዋዕለ ሕጻናት፣
- የአዛውንቶች ክብካቤ ማድረግ፡
- ቆሻሻዎችን መሰብሰብ፣ የውሃና ፍሳሽ አገልግሎት፡
- የኣከባቢው መንገዶች፡
ፖለቲካዊና አስተዳደራዊ ኣመራር
ማዕከላዊው መንግሥት፣ የክልል እና የኣከባቢ ኣስተዳደሮች፡ በሕዝብ በተመረጡ ፖለቲከኞች ይመራሉ። ይህ ማለት፡ ፖለቲከኞች በተለያዩ የፓሊሲዎች ጉዳዮች ላይ በመወያየት ይወስናሉ። ይሁን እንጂ ፖሊሲዎችን የሚተገብሩት፡ የመንግስት ሰራተኞች እና በክልሎች የኣከባቢ ኣስተዳደር ውስጥ ያሉ ሰራተኞች ናቸው።
ምሳሌዎች፡
- ፖለቲከኞች የትምህርት ቤት ሥርዓተ-ትምህርት ያጸድቃሉ። መምህራን በነዚህ ስሥርዓተ ትምህርቶች መሰረት ያስተምራሉ።
ፖለቲከኞች ለማሕበራዊ ደኅንነት ኣገልግሎት በመወሰን መመርያ ይቀርጻሉ። የናቭ ሰራተኖች ደግሞ በእነዚህ ሕጎች መሰረት ስራቸውን ያከናውናሉ።
የኖርዌይ ፓርላማ
የኖርዌይ ፓርላማ ስቶርቲንግ ይባላል። ለአራት ዓመታት በሕዝብ የተመረጡ 169 አባላት አሉት። አባላቱ የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎችን ይወክላሉ። ስቶርቲንግ በኖርዌይ ውስጥ የበላይ የመንግስት አካል ነው።
የስቶርቲንግ ዋና ዋና ጠቃሚ አገልግሎቶች
- አዳዲስ ህጎችን ማፅደቅ እና የቆዩትን ማሻሻል፣
- የሀገሪቱን በጀት መወሰን፣
- ለመንግስት እና የማዕከላዊ መንግስት አስተዳደርን መቆጣጠር፣
- በፖለቲካ ጉዳዮች እና በዋና ፕሮጀክቶች ላይ ክርክር ማድረግ፣
ኖርዌይ ክፍት ዲሞክራሲ አላት። ማንም ፍላጎት ያለው ሰው፡ ፖለቲከኞች በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ሲከራከሩ ማዳመጥ ይችላል። ይሁን እንጂ፡ ህዝቡ በስቶርቲንግ ውስጥ ባሉ ጉዳዮች ላይ የመናገርም ሆነ መግለጫ የመስጠት መብት የለውም። ብዙ ጉዳዮች በስቶቲንግ ለምክር ይሰራጫሉ። ይህ ባለሙያዎች እና ተራ ሰዎች አስተያየት እንዲሰጡበት እድል ይፈጥራል።
መንግሥት
ከጠቅላላ ምርጫ በኋላ አንድ ወይም ብዙ ፓርቲዎች በህብረት አዲስ መንግስት ያቋቁማሉ። መንግሥቱም በሚኒስትሮችን (የእያንዳንዱ ሚኒስቴር የፖለቲካ ኃላፊ) እና ጠቅላይ ሚኒስትሩን የቆመ ነው። ከመንግስት ተግባራት ውስጥ አንዱ አዳዲስ ህጎችን እና ባሉት ህጎች የማሻሻል ሃሳብ ማቅረብ ሲሆን፣ ስቶርቲንግ ህጎቹን እና የህግ ማሻሻያዎችን ያጸድቃል። መንግሥትም፡ የስቶርቲንግ ውሣኔዎቹ እንዲተገበሩ የማድረግ ኃላፊነት ኣለበት። መንግሥት በየዓመቱ ብሔራዊ የበጀት እቅድ እያዘጋጀ ለስቶርቲንግ ያቀርባል።
የመንግሥት ምክርቤት
መንግሥት በየሳምንቱ አርብ ቀን፡ ከንጉሱ ጋር ስብሰባ ያደርጋል። በእነዚህ ስብሰባዎች ላይ ሚኒስትሮቹ ስለ ተለያዩ የፖለቲካ ጉዳዮች ለንጉሱ መረጃ ያቀርባሉ። ይህ ስብሰባ የመንግሥት ምክር ቤት ይባላል። ንጉሱ ብዙ የፖለቲካ ስልጣን የላቸውም፣ ነገር ግን እነዚህ ስብሰባዎች አስፈላጊ ናቸው።
የስልጣን መለያየት መርህ
የስልጣን ክፍፍል፡ የመንግሥት ሃላፊነት በሶስት እኩል ስልጣን ያላቸው አካላት መከፋፈል ማለት ነው።
- ህግ አውጭ አካል - ስቶርቲንግ - ህጎችን የሚያጸድቅ፣
- አስፈፃሚ አካል - የመንግሥት- የሕጎችን ረቂቅ የሚያቀርበው እና ከጸድቁ በኋላ ተግባራዊ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ፣
- የፍትህ ኣካል- ስቶርቲንግ ባፀደቀው ሕግ መሰረት፡ ፍርድን በትክክል መተግበሩን የሚያረጋግጥ፣.
ለእነዚህ ሶስት የመንግስት አካላት ስልጣን ሲከፋፈል፡ ከሶስቱ የትኛውን የሚበልጠውን አንዳቸውም ስልጣን ሊይዝ ኣይችልም። ይህም ዴሞክራሲን ያረጋግጣል።
ኣብራችሁ ተወያዩ
- በትውልድ ሃገራችሁ ስላሉ የመንግስት አካላት ተነጋገሩ፡፡
- በኖርዌይ ስላለው የስልጣን ክፍፍል ተወያዩ።
- በማሕበራዊ ደህንነት ኣገልግሎት ስርዓት፡ የመንግሥት፣ የክልልና የኣከባቢ ኣስተዳደሮች ተግባሮች ተወያዩ፡፡
- በምትኖሩበት ማሕበረሰብ ላይ እንዴት ተጽእኖ ማሳደር ትችላላችሁ?
- ከአገራዊ ጉዳዮች ይልቅ በአካባቢያዊ ጉዳዮች ላይ ተጽእኖን መፍጠር ቀላል እንደሆነ ታስባላችሁን? ኣዎን ከሆነ፡ ለምን? ኣይ ከሆነ፡ ለምን?
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ
የማእከላዊው መንግሥት ሃላፊነት የሆኑት ጉዳዮች የትኞቹ ናቸው?
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ
የኖርዌይ ፓርላማ ምን በማባል ይጠራል?
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ
የሃገሪቱ መማክርት ምንድነው ?
ትክክል ወይም ስህተት የሆነውን ይምረጡ
መግለጫዎቹን ያንብቡ፡፡ ትክክል የትኛው ነው? ስህተት የትኛው ነው?
ትክክል ወይም ስህተት የሆነውን ይምረጡ
መግለጫዎቹን ያንብቡ። ትክክል የትናው ነው? ስህተት የትናው ነው?