ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እና ከፍተኛ ትምህርት
ፊልሙን ይመልከቱ
ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት
አብዛኛዎቹ ሙያዎች የሁለተኛ ደረጃ ወይም የከፍተኛ ትምህርት ያስፈልጓቸዋል። ስለዚህ አብዛኛዎቹ ወጣቶች ትምህርታቸውን፡ ከሁለተኛ መለስተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በኋላ ለመቀጠል ይመርጣሉ ።
- ዕድሜያቸው ከ 16 እስከ 25 ዓመት የሆኑ ተማሪዎች በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ቦታ የማግኘት መብት አላቸው።
- የመንግሥት ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ከክፍያ ነፃ ናቸው።
- ተማሪዎች በአጠቃላይ ጥናቶች እና በሙያ ስልጠና መካከል ይመርጣሉ።
- ተማሪዎች ከመጋቢት 1 ቀን በፊት በከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ቦታ ለማግኘት በመስመር ላይ [ኢንተርነት] ማመልከት አለባቸው።
- በ 10ኛ ክፍል ያገኙት ውጤት፡ የትኛውን የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መሄድ እንደሚችሉ ይወስናል።
- አንዳንድ የግል ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች አሉ። ወደ የግል ትምህርት ቤት የሚሄዱ ተማሪዎች ክፍያ መክፈል አለባቸው።
የሙያ ስልጠና ፣ እዚህ መስክ ተማሪዎች ተግባራዊ ትምህርት ይወስዳሉ፡ ትምህርታቸውን ሲያጠናቅቁ ደግሞ የዕደ ጥበብ የምስክር ወረቀት ያገኛሉ። የተግባራዊ ትምህርት ምሳሌዎች ኣናጺነት፣ ፀጉር አስተካካይነት፣ የጤና ሠራተኛ እና የመኪና መካኒክ መርሃ ግብሮችን ያካትታሉ።
አጠቃላይ የጥናት ትምህርት፣ በዚህ መስክ፡ ተማሪዎች የንድፈ ሃሳብ ትምህርት ያገኛሉ። ከአጠቃላይ ጥናቶች ትምህርት የምስክር ወረቀት ያላቸው ተማሪዎች፡ ወደ ዩኒቨርሲቲ ወይም ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ ለመግባት ማመልከት ይችላሉ።
በይነመረብ/ ኢንተርነት
ምንጭ: SSB
ከፍተኛ ትምህርት
የዘመናዊ ደህንነት ማህበረሰብ በከፍተኛ የሥራ ስምሪት ፣ ቴክኖሎጂ ፣ ምርት እና ፈጠራ ላይ የተመሠረተ ነው። ስለዚህ፡ ኖርዌይ በከፍተኛ ደረጃ የተማረ ሕዝብ ያስፈልጋታል። የመንግሥት ዘርፉ፡ ለሁሉም እኩል የትምህርት አቅርቦት በመስጠት ግዳጁን ይወጣል።
35% የኖርዌይ አዋቂዎች የከፍተኛ ትምህርት ደረጃ አላቸው። በተጨማሪ፡ ብዙ ወጣቶች ከፍተኛ ትምህርት እየቀሰሙ ስለሆነ፡ በኖርዌይ የትምህርት ደረጃ እያደገ ነው።በኣሁኒ ጊዜ፡ ሴቶች ከ60% የተማሪዎች ቁጥር ይዘዋል፡ ይኸውም ከኣጠቃላይ የወንዶች ቁጥር ትንሽ ከፍ ያለ ነው። ከጠቅላላው ሕዝብ ጋር ሲነጻጸር፡ ወላጆቻቸው ስደተኛ የሆኑ ሰዎች፡ የበብዛት ወደ ከፍተኛ ትምህርት ይገባሉ።
ከሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የከፍተኛ ትምህርት የመግቢያ ብቃት ያገኘ ሁሉ፡ በዩኒቨርሲቲ ወይም በዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ ቦታ ለማግኘት ማመልከት ይችላል።
- ትምህርት በዩኒቨርሲቲዎች እና ኮሌጆች ነፃ ነው፣ ተማሪዎች ግን ለመጽሐፎቻቸው መክፈል አለባቸው።
- ወደ ኮለጆችና ዩኒቨርሲቲዎች መግባት በማዕከላዊነት የሚያስተዳድረው ኣካል፡ Samordna opptak ይባላል። ስለ ማመልከቻው የጊዜ ገደብ መረጃ በድህረገጹ ይገኛል።
ኢንተርነት
ሎነካሰን (የኖርዋይ መንግስት የትምህርት ፋንድ)
ምንም እንኳን ትምህርት በዩኒቨርሲቲዎች እና ኮሌጆች ነፃ ቢሆኑም፣ ተማሪዎች በሚማሩበት ጊዜ ለሌላ ወጪዎች ገንዘብ ይፈልጋሉ። ስለዚህ ተማሪዎች ለቤት ኪራይ ፣ ምግብ እና ሌሎች አስፈላጊ ነገሮችን ከኖርዌይ መንግስት የትምህርት ፋንድ (ሎንካሰን) ገንዘብ መበደራቸው የተለመደ ነው። ሎነካሰን፡ በኖርዌይ ውስጥ ላሉ ተማሪዎች እና በውጭ ለሚማሩ ተማሪዎች፡ እርዳታ እና ብድር ይሰጣል። ይህም ዕድል፡ ከፍተኛ ትምህርት ለመውሰድ ለሚፈልጉ ሁሉ፣ በፆታ፡ ዕድሜ፡ ማህበራዊ ሁኔታ እና የቤተሰባቸው የገንዘብ ሁኔታ፡ ግምት ውስጥ ሳያስገባ፡ የመማር ዕድላቸውን ያረጋግጣል። አዋቂዎችም፡ ለአንደኛ እና ለመለስተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት፡ ለእርዳታ እና ለብድር ማመልከት ይችላሉ።
ትምህርታቸው ካጠናቀቁ በኋላ፡ የተበደሩት ገንዘብ በወርሃዊ መክፈል ኣለባቸው። ዕርዳታው መከፈል የለበትም፣ ነገር ግን፡ ይህ ብዙውን ጊዜ፡ ተማሪው ትምህርቱን አጠናቅቆ ፈተናውን ካለፈ ብኋላ ብቻ ነው።
ኣብራችሁ ተወያዩ
- ሁሉም ወጣቶች የከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት የማግኘት መብት አላቸው። ይህ ስለ ህብረተሰብ እና ስለ የስራ ገበያው ምን ይነግረናል?
- በኖርዌይ ማህበረሰብ ውስጥ ቁጥራቸው እየጨመረ የመጣ ሰዎች ከፍተኛ ትምህርት እየወሰዱ ነው። ይህ ስለ ሰራተኞች እና የሥራ እድሎች ምን ይነግረናል?
- ሎነካሰን፡ በ 1947 እ.ኤ.አ. ተቋቋመ። ኣላማው ማንኛውም የህብረተሰቡ ኣባል፡ ከፍተኛ ትምህርት እንዲያገኝ ለመርዳት ነው። ሎነካሰን ባንክ እና የበጎ የማህበራዊ ደህንነቱ ስርዓት አስፈላጊ አካል ነው። ስለ መርሃ ግብሩ ምን ያስባሉ?
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ
የሙያ መርሃ ግብር (ፕሮግራም) ምንድነው?
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ
በኖርዌይ፡ የግል ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች አሉ ወይ?
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ
በኖርዌይ ካሉ ኣዋቂዎች፡ ምን ያህሉ ከፍተኛ ትምህርት አላቸው?
ትክክል ወይም ስህተት የሆነውን ይምረጡ
መግለጫዎቹን ያንብቡ:: ትክክል የትኛው ነው? ስህተት የትኛው ነው?
ትክክል ወይም ስህተት የሆነውን ይምረጡ
መግለጫዎቹን ያንብቡ:: ትክክል የትኛው ነው? ስህተት የትኛው ነው?
ትክክለኛውን ምስል ይምረጡ
የትኛው ምስል የንድፈ ሀሳብ ትምህርት ያሳያል?
በምስሉ ላይ ጠቅ ያድርጉ
በየትኛው ዕድሜ፡ ተማሪዎች በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ቦታ የማግኘት መብት አላቸው?