ትምህርት ለኣዋቂዎች
ትምህርት ለኣዋቂዎች
ማሕበረ ሰብ በየጊዜው እየተለወጠ ነው። አዲስ ቴክኖሎጂ በሥራ ዓለም ተጽእኖ አለው። ስለሆነም፡ ሠራተኞቹ ወቅታዊ ሆነው እንዲቆዩ እና አዲስ ክህሎቶችን እንዲማሩ ይጠይቃል። አዋቂዎች አዲሱን የሥራ ሕይወት ፍላጎቶች ለማሟላት ሙሉ በሙሉ አዲስ ትምህርት መውሰድ፣ በነበራቸው ትምህርት ላይ መገንባት ወይም የአንደኛ ደረጃ ትምህርቶችን መውሰድ ይችላሉ። ብዙ አዋቂዎች በሥራ ላይ እንዳሉ በተመሳሳይ ጊዜ ቀጣይ እና ተጨማሪ ትምህርት ይወስዳሉ። ሕይወታችንን ሙሉ መማራችን ቀጣይ በመሆኑ፡ የዕድሜ ልክ ትምህርት ተብሎ ይጠራል።
ለአዋቂዎች የዝግጅት እና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት
አዋቂዎች ከዚህ ቀደም የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርታቸውን ያላጠናቀቁ ከሆነ፡ ለአዋቂዎች (FOV) የመሰናዶ ትምህርት የማግኘት መብት አላቸው። ለአዋቂዎች የዝግጅት ስልጠና ነፃ ነው። ይህንን ስልጠና የመስጠት ሃላፊነት ማዘጋጃ ቤቱ ነው።
ዕድሜያቸው 25 እና ከዚያ በላይ የሆኑ አዋቂዎች፡ ኣስቀድመው የከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ካልወሰዱ፡ ይሀንን የማግኘት መብት አላቸው። የከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት በኖርዌይ ከመጀመርዎ በፊት፡ በኖርዌይ ወይም በሌላ አገር፡ የአንደኛና መለስተኛ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርትዎን ማጠናቀቅ አለብዎት። ለዚሁ ትምህርት ኃላፊነት ያለበት የክልሉ ባለሥልጣን ነው። የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት፡ በሕዝብ ትምህርት ቤት ሥርዓት፡ ለአዋቂዎች ነፃ ነው። በኖርዌይ ብዙ የግል ትምህርት ቤቶችም ኣሉ፣ እኒኚህ ግን፡ ነፃ አይደሉም።
ትምህርት ቤቶች ነፃ ቢሆኑም ፣ አዋቂዎች ለመኖር ገንዘብ ያስፈልጋቸዋል። ብዙዎቹ ወደ ትምህርት ቤት በሚሄዱበት ጊዜ ከኖርዌይ ግዛት የትምህርት ብድር ፈንድ የገንዘብ ድጋፍ/ወይም ብድር ማግኘት ይችላሉ።
ከውጭ አገር ለተወሰደ ትምህርት ዕውቅና መስጠት
የሌሎች አገሮች ብቃቶች ካሉዎት በኖርዌይ ውስጥ እውቅና እንዲሰጣቸው ማመልከት ይችላሉ። ይህ የሚደረገው በኖርዌይ የከፍተኛ ትምህርት እና ክህሎቶች ዳይሬክቶሬት HK-dir በኩል ነው። የጤና ሰራተኞች ከኖርዌይ ጤና ዳይሬክቶሬት ፈቃድ ለማግኘት ማመልከት ይችላሉ።
ስለ አማራጮችዎ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት፡ በትምህርት ቤትዎ ውስጥ ካሉት አማካሪ ወይም ከስደተኛ አማካሪ ጋር ይነጋገሩ።
የቅድመ ትምህርት እና የሥራ ልምድ ግምገማ
በትምህርትም ሆነ በሌላ ልምዶች ብቃት ማግኘት ይቻላል። እንደ አዋቂ ወደ ኖርዌይ የሚመጡ ሰዎች፡ የምስክር ወረቀቶችን በማቅረብ ክህሎቶቻቸውን መመዝገብ አስቸጋሪ ሊሆንባቸው ይችላል። ነገር ግን፡ የትምህርት እና የሥራ ልምዳቸው ሊገመገም ይችላል። ይህ ማለት፡ የግለሰቡ ችሎታዎች በተመደቡበት መስክ ላይ በሚኖሩ መመዘኛዎች ይገመገማሉ ማለት ነው። ግምገማው የጥናት ኮርሶችን ማሳጠር፣ የጥናት መርሃ ግብሮችን መቀበል፣ ከጥናት መርሃ ግብር ክፍሎች ነፃ መሆን፣ እንዲሁም አዲስ ሥራ ወይም ከፍ ያለ ክፍያ ሊያስከትል ይችላል። ግምገማው፡ ከሙያ ትምህርት ጋር በተያያዘ፡ የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት፣ በመለስተኛ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት፡ በሙያ ትምህርትና እና በከፍተኛ የትምህርት ደረጃ፡ ሊሆን ይችላል።
ኣብራችሁ ተወያዩ
- የዕድሜ ልክ ትምህርት የሚለውን ቃል ምን ይመስልዎታል?
- በኅብረተሰብ የተደረጉ እድገቶች፡ የግለሰቡን አዲስ ዕውቀት እና ክህሎቶች ማግኘት ኣስፈላጊነት እንደሚወሰኑ፡ ኣብረው ተነጋገሩ።
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ
አዋቂዎች ነፃ የአንደኛ ደረጃ እና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት የማግኘት መብት ያላቸው መቼ ነው?
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ
የአዋቂዎችን ጨምሮ፡ የአንደኛና የመለስተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርትን የማቅረብ ኃላፊነት ያለው ማነው?
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ
ዕድሜያቸው 25 እና ከዚያ በላይ የሆኑ አዋቂዎች፡ ኣስቀድመው እንዲህ ዓይነቱን ትምህርት ካልወሰዱ፡ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት የማግኘት መብት አላቸው። ይህንን መብት ለማግኘት ምን ዓይነት ትምህርት ቤት ያስፈልግዎታል?
ትክክል ወይም ስህተት የሆነውን ይምረጡ
መግለጫዎቹን ያንብቡ:: ትክክል የትኛው ነው? ስህተት የትኛው ነው?
ትክክል ወይም ስህተት የሆነውን ይምረጡ
መግለጫዎቹን ያንብቡ:: ትክክል የትኛው ነው? ስህተት የትኛው ነው?