አንደኛው እና ሁለተኛው የዓለም ጦርነት
አንደኛው እና ሁለተኛው የዓለም ጦርነት
ኖርዌይ እንደገና በ1905 ዓ.ም ሉዐላዊት አገር ሆነች። አዲስ ዘመን ተጀመረ። በ1900 ዓ.ም. ጅማሬ የሕዝቡ ቁጥር አደገ፣ ሰዎች ወደ ከተማዎች መፍለስ ጀመሩ፡ ኢንዱስትሪዎችም ተስፋፉ።
ኖርዌይ ብዙ ፏፏቴዎች አሏት፣ ሕዝቡም በ19ኛው ክፍለ ዘመን መገባደጃ ላይ፡ እንዚህን ፏፏቴዎች በውሃ ኋይል ለሚመነጭ ኤሌክትሪክ ኃይል መጠቀም ጀመሩ። ተጨማሪ ፋብሪካዎች ተከፍተዋል፡ ሰራተኞችም በከፍተኛ ደረጃ ይፈለጉ ጀመር። ብዙ ሰዎች ወደ ከተማዎች ይጎርፉ ጀመር። በአንዳንድ ቤቶች ኤሌክትሪክ ተዘርግቷል፣ በከተሞች የመንገድ መብራቶች ተጀመረ፣ በአንዳንዶቹ ደግሞ የኤሌክትሪክ ትራም ኔትወርክ ተዘርግቷል። የናፍጣ ሞተሮች በመርከቦች ውስጥ ተጭነዋል፣ ይህም በበለጠ ፍጥነት እንዲጓዙ አስችሏቸዋል።የመጀመሪያዎቹ መኪናዎች ኖርዌይ ደረሱ።
አንድ ግለሰብ በውሃ ኃይል የሚመነጭ ኤሌትሪክ ማመንጫ መገንባት የሚችልበት ለየት ያለ ሕግ ወጥቷል ሆኖም ግን የኃይል ማመንጫው ንብረትነቱ የሕዝብ ነው፡፡
ለፓርላማው (ስቶርቲንግ) አሁን የሥራ የሚሠራበት ወቅት ነበር።የሠራተኛ ማኅበራት ለሠራተኞች የተሻለ ሁኔታ በመፈለግ ለውጥ ለማምጣት ግፊት አድርገዋል።ስለዚህም፡ስቶርቲንግ ብዙ ሕጎችን አውጥቷል፣ ከእነዚህም መካከል አንድ ሰው ከአስር ሰአት በላይ መሥራት የለበትም የሚለው ሕግ ይገኝበታል። ይህ ሰአት ደግሞ በ1919 ዓ.ም. ወደ ስምንት ሰአት ዝቅ ብሏል። ሁሉም ሰራተኞች በሕመማቸው ጊዜ የሕግ ድጋፍ አላቸው፣ ይህም ማለት ሰራተኞች በሚታመሙበት ጊዜ፡ ከማዕከላዊ መንግሥት የገንዘብ ድጋፍ ይደረግላቸዋል፡፡
እድሜያቸው ከ25 አመት በላይ የሆኑ ወንዶች፡ ከ1898 ዓ.ም. ጀምሮ፡ በአገሪቱ በሚካሄደው አጠቃላይ ምርጫ የመሳተፍ መብት አገኙ። ከ1913 ዓ.ም ጀምሮ ደግሞ እድሜያቸው ከ25 አመት በላይ ለሆናቸው ሴቶች ተመሳሳይ መብት ተሰጣቸው።
አንደኛው የዓለም ጦርነት
በ1914-1918 አንደኛው የዓለም ጦርነት በአውሮፓ ተቀሰቀሰ። በዚሁ ጦርነት ኖርዌይ አልተሳተፈችም፣ ይሁን እንጂ፡ በጦርነቱ የተፈጠረው የምጣኔ ሃብት መዘዝ ገፈት ቀማሽ ሆናለች። በጦርነቱ ምክንያት እንደ ጥራጥሬ፡ ቡና እና ስኳር ባሉ ሸቀጦች እጥረት ስለተፈጠረ፡ ለሕዝቡ በኩፖን እንዲከፋፈል ኣድርጎ ነበር።
በጦርነቶቹ መካከል የነበሩት አመታት
በአንደኛውና በሁለተኛው የዓለም ጦርነቶች መካከል የነበረው ጊዜ፡ በጦርነቶቹ መካከል የነበሩት አመታት በመባል ይታወቃሉ፡፡ በጦርነቶቹ ምክንያት በመላው ዓለም ላይ የተፈጠረው የገንዘብ ቀውስ በኖርዌይ ውስጥም ተፈጥሮ ነበር፡፡ ብዙ ሰዎች ሥራ አጦች ሆነው ነበር፡፡
ሁለተኛው የዓለም ጦርነት
ሁለተኛው የዓለም ጦርነት በመስከረም ወር 939 በጀርመን በፖላንድ ላይ ወረራ በመፈጸሟ ነበር። ኖርዌይ ሚያዝያ 9 ቀን 1940 በጀርመን ጦር ተያዘች። በኖርዌይ ውስጥ ያለው ጦርነት ኖርዌይ ከመያዟ በፊት ለጥቂት ሳምንታት ብቻ ቆየ። ንጉሱ እና የመንግስት ኣካላቱ ወደ እንግሊዝ ኣገር በመሸሽ፡ ኖርዌይን ከዚያ ነፃ ለማውጣት ትግሉን ቀጠሉ። ስለሆነም፡ኖርዌይ መንግስት የምትመራው፡ የጀርመን ደጋፊ በነበረው፡ በዲሞክራሲያዊ መንገድ ባልተመረጠው፡ የቪድኩን ኩይስሊንግ ነበር።
በኖርዌጂያን ምድር ብዙም ተጨባጭ ውጊያ ባይካሄድም፡ በርካታ ተቃዋሚ ቡድኖች፡ በጀርመን ወረራ ሃይሎች ላይ ኣመጽ ኣክሂደዋል፡ ሕገ ወጥ ጋዜጦችን በማሳተም ዘርግቷል፡ ህዝባዊ እምቢተኝነትን እና ህዝባዊ ተቃውሞ የሚያደርጉ ቡድኖች ኣደራጅቷል። በተቃውሞ እንቅስቃሴ ውስጥ ንቁ የነበሩ ብዙ ሰዎች ከሀገር መሰደድ ነበረባቸው። በጦርነቱ ወቅት ወደ 50,000 የሚጠጉ ኖርዌጂያውያን ወደ ስዊድን ተሰደዋል። ብዙዎቹም ሌሎችን ለመርዳት አደጋ ላይ ወድቀዋል።
በሰሜን ኖርዌይ ብዙ ሰዎች ተገድለዋል፣ የጀርመን ወታደሮች እነዚህን አካባቢዎች ለቀው ሲወጡ፡ አብዛኛው የፊንማርክ እና የትሮምስ ኣከባቢ ክፍል ከጥቅም ውጭ ሆኗል። በሂትለር ትእዛዝ፡ አብዛኛዎቹ ህንፃዎች እና መሰረተ ልማቶች ተቃጥለዋል።
በመጨረሻም፡ ጀርመኖች በብዙ ግንባሮች ጦርነቱን እየተሸነፉ በመሄድ እ.ኤ.አ በ1945 ዓ.ም በጦርነቱ ተሸንፈው እጅ ሰጡ። በጦርነት ምክንያት ከ10,000 በላይ ኖርዌጂያውያን ሕይወታቸውን አጥቷል።
ከጦርነቱ በፊት በኖርዌይ 2,100 የሚሆኑ የአይሁድ ሕዝቦች ይኖሩ ነበር፡፡ ከእነርሱም መካከል 773 ያሕሉ ወደ ማጎሪያ ካምፕ የተወሰዱ ሲሆን፡ ከመካከላቸውም 38 ያህሉ ብቻ ተርፈው ከጦርነቱ በኋላ ወደ ኖርዌይ ተመልሰዋል።
ኣብራችሁ ተወያዩ
- ስቶርቲንግ ለሠራተኞች ኑሮን ቀላል የሚያደርግ ሕጎችን ያጸደቀው ለምን ይመስላቹሃል?
- በትውልድ ሀገርዎ አንደኛው የዓለም ጦርነት እና ሁለተኛው የዓለም ጦርነት ምን ይመስል ነበር?
- ጦርነት በአንድ ማህበረሰብ እና በዚያ የሚኖሩ ሰዎችን እንዴት እንደሚነካ አብራችሁ ተነጋገሩ። በጦርነት ጊዜ ሰብአዊ መብቶች እንዴት ይስተናገዳሉ?
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ
በኖርዌይ ውስጥ ሴቶች ድምጽ የመስጠት መብት ያገኙት መቼ ነበር?
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ
የእርስ በእርሱ ጦርነት መቼ ነበር የተካሄደው?
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ
የጀርመን ጦር መቼ ነበር ኖርዌይን ተቆጣጥሮ የነበረው?
ትክክል ወይም ስህተት የሆነውን ይምረጡ
መግለጫዎቹን ያንብቡ። ትክክል የትኛው ነው? ስህተት የትኛው ነው?
ትክክል ወይም ስህተት የሆነውን ይምረጡ
መግለጫዎቹን ያንብቡ። ትክክል የትኛው ነው? ስህተት የትኛው ነው?
ምስሉን ተጫኑት
በዘመን ቅደም ተከተሉ መሰረት፡ ትክክለኛውን ምስል ይጫኑ፡፡ ሁለኛው የዓለም ጦርነት የተካሄደው መቼ ነበር?