ሥራ ፍለጋ
ፊልሙን ይመልከቱ
ሥራ ፍለጋ
ማመልከቻ እና ሲቪ (የሥራ ልምድ ታሪክ)
በኖርዌይ፣ ሥራ አጥነት ዝቅተኛ ቢሆንም፡ ክፍት የሥራ ቦታ ለምግኘት ግን ጠንካራ ውድድር ሊኖር ይችላል። ማንም መሥራት የሚፈልግ፡ ሥራ በንቃት መፈለግ አለበት። እውቂያዎችህን እና አውታረ መረብህ( network)ን መጠቀም እና ለመሥራት ፍላጎት እንዳለህ ማሳየት አስፈላጊ ነው። ልታመለክትበት የምትፈልገውን ሥራ ስታገኝ፡ ወዲያውኑ የጽሑፍ ማመልከቻ እና ሲቪ ማስገባት ይኖርብሃል።
ማመልከቻው፡ ስለ ራስህና ያለህን ክህሎቶች የምትገልጽበት ደብዳቤ ነው። ሲቪው፡ ያለህን የትምህርት ደረጃ እና የሥራ ልምድን በአጭሩ የምትገልጽበት ሰነድ ነው። ማመልከቻው እና ሲቪው በትክክለኛ የኖርዌይ ቋንቋ መፃፍ አለባቸው። የቀረበው መረጃ ሁሉ፡ ትክክል መሆን አለበት። ሰነዶቹን በቀላሉ ለመከታተል የሚቻሉ መሆን ኣለበት።
አዲስ ሠራተኛ መቅጠር የሚፈልግ አሠሪ፡ ግለሰቡ በሥራው በጣም ተስማሚ መሆኑን ማረጋገጥ ኣለበት። በእርግጥ ሰውዬው (እሱ ወይም እሷ)፡ ትክክለኛ ትምህርት ወይም ብቃት ያለው መሆኑን ከግምት ያስገባል፣ ነገር ግን፡ ተጨማሪ ሌሎች ነገሮችም ከግምት ያስገባል።
የሚቀጠረው ሰው ማሟላት ካለበት ነገሮች፡-
- የሥራ ልምድ፡
- ጥሩ ማጣቀሻዎች፡
- የሥራ አካባቢን የሚስማማ ስብዕና፡
- ከሥራው ጋር የሚጣጣሙ ብቃቶች፡
ቃለ መጠይቅ
አሠሪው ሥራውን ማን እንደሚያገኝ ከመወሰኑ በፊት፡ አንድ ወይም ብዙ ቃለ መጠይቆችን ማሰባሰብ፡ የተለመደ ነው። በቃለ መጠይቁ፡ የሥራ አመልካቹ እራሱን እና ችሎታውን የማቅረብ ዕድል ያገኛል፣ በዚሁም በሚቀጥረው ሰው ላይ ስሜት ያሳድራል። ሁለቱም ጥያቄዎችን ማቅረብ ይችላሉ።
ለቃለ መጠይቅ ምክሮች:
- ቃለመጠይቁ የት እንደሚደረግ እና እንዴት እዚያ መድረስ እንደምትችል ኣስቀድመህ እወቅ።
- ስለምትለብሰው ልብስ እና ምን ዓይነት ስሜት መፍጠር እንደምትፈልግ ኣስብበት።
- በጥሩ ሰዓት ድረስ።
- ጠንካራ የእጅ መጨባበጥ እና የዓይን ግንኙነት አስፈላጊ ናቸው።
- አዎንታዊ ሁን ፣ ፈገግ በል እና ከቃለ መጠይቆች ኣቅራቢዎች ጋር መግባባት ለመፍጠር ሞክር።
ኣብራችሁ ተወያዩ
- በሀገርዎ ውስጥ የተፃፉ ማመልከቻዎች አስፈላጊ ናቸውን?
- በጽሑፍ ማመልከቻ ውስጥ፡ ምን መጨመር እንዳለብዎ ይወያዩ፡
- በቃለ መጠይቅ ግዜ ሊጠይቋቸው የሚገቡ፡ ጥሩ ነገሮች ምንድን ናቸው፣ እና ከመጠየቅ መቆጠብ ያለብዎት ነገር ምንድን ነው?
- በቃለ መጠይቅ ግዜ ምን እንደሚለብሱ ይወያዩ።
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ
የሥራ ማመልከቻ ምንድነው?
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ
ሲቪ ምንድን ነው?
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ
የሥራ ቃለ መጠይቅ፡ ማን ጥያቄዎችን መጠየቅ ይችላል?
ትክክል ወይም ስህተት የሆነውን ይምረጡ፣
መግለጫዎቹን ያንብቡ:: ትክክል የትኛው ነው? ስህተት የትኛው ነው?
ትክክል ወይም ስህተት የሆነውን ይምረጡ
መግለጫዎቹን ያንብቡ:: ትክክል የትኛው ነው? ስህተት የትኛው ነው?