የግል ፋይናንስ

Lærerinnhold

Tips til undervisningen

Snakk sammen

Eksempler på inntekter: lønn, barnetrygd, pensjon
Eksemplerpå utgifter: boutgifter, strøm, transport, mat, fritidsaktiviteter, klær, reparasjoner, møbler, reiser

For å spare kan man f. eks. redusere forbruket eller kjøpe klær, utstyr og møbler brukt. Barna kan arve klær. En kan spare på strømmen (slå av lyset, redusere innetemperatur), sykle eller gå istedenfor å bruke bil, handle på tilbud og handle matvarer planlagt og sjelden.

Tips til undervisninga

Snakk saman

Døme på inntekter: løn, barnetrygd, pensjon
Døme på utgifter: buutgifter, straum, transport, mat, fritidsaktivitetar, klede, reparasjonar, møblar, reiser

For å spare pengar kan ein til dømes redusere forbruket eller kjøpe klede, utstyr og møblar brukt. Barna kan arve klede. Ein kan spare på straumen (slå av lyset, redusere innetemperaturen), sykle eller gå i staden for å bruke bil, handle på tilbod, planleggje matvareinnkjøp og handle matvarer sjeldan.

Læreplan

Grunnleggende ferdigheter

Muntlige ferdigheter
Digitale ferdigheter

Tverrfaglige tema

Folkehelse og livsmestring

Læreplan i samfunnskunnskap for voksne innvandrere etter integreringsloven

samtale om hvordan arbeid, inntekt og forbruk kan påvirke personlig økonomi, levestandard og livskvalitet

Kjerneelement

Individ og fellesskap

Læringsaktivitet

Muntlig aktivitet
Utforsking

የግል ፋይናንስ

Sedler, norske penger. Illustrasjonsfoto.
GettyImages

ገቢ ማንኛውም ወደ ባንክ ሒሳብዎ የሚገባ ገንዘብ፣ (ክፍያ፣ የማህበራዊ ደሕንነት ወይም ከNAV የሚገኝ ማንኛውም ጥቅማ ጥቅሞች፣ የልጅ ድጋፍ፣ የገንዘብ እርዳታ፡ ወዘተ)፡ ነው።

ወጪዎች ማለት ገንዘብ የምታወጡት ሁሉ፣ (ኪራይ፣ ወለድና እና ክፍያዎችን፣ ምግብ፣ ልብስ፣ ትራንስፖርት፣ ኤሌክትሪክ፣ ኢንተርኔት፣ መዝናኛ፣ ወዘተ)፡ ያጠቃልላል።

ጠቅላላ ክፍያ ፡ ግብር ሳይቆረጥ በፊት ያለው ገቢ።
የተጣራ ክፍያ ፡ ግብር ከተቆረጠ በኋላ በእጃችን የሚቀረው ነው።

ገቢና ወጪ

በኖርዌይ ውስጥ ኑሮ ውድ ነው። በአብዛኛዎቹ ቤተሰቦች ውስጥ ያሉት ሁለቱም ወላጆች ከቤት ውጭ፡ ደመወዝ እየተከፈላቸው ስራ ይሰራሉ። አንዳንድ ቤተሰብ፡ ሕጻናት ልጆቻቸው እስኪያድጉ፡ ኣንዳቸው (ኣባት ወም እናት) የተቀነሰ የስራ ሰዓት መስራት ሲችሉ፣ ብዙዎች ኑሮኣቸውን ለሟሟላት፡ “የሙሉ ጊዜ ሥራዎችን” ይፈልጋሉ። በቤተሰብ ውስጥ ሁለቱም አዋቂዎች ለቤተሰቡ ፋይናንስ ተጠያቂ ናቸው።

በኖርዌይ የሚኖሩ አብዛኛዎቹ አዋቂ ሰዎች፡ በወር ኣንድ ግዜ፡ ክፍያ ይቀበላሉ። ይኸውም የማህበራዊ ደህንነት ክፍያ፣ ወይም ጡረታ ሊሆን ይችላል። በቤተሰቡ ውስጥ ከ18 አመት በታች የሆናቸው ልጆች ካሉ፡ ለልጆች ተብሎ የሚሰጠውን ድጎማ ይቀበላሉ። ልጆቻቸው ወደ መዋዕለ ሕጻናት ለማይሄዱ ወላጆች የእንክብካቤ ማድረጊያ ተጠቃሚ በመሆን የገንዘብ እርዳታ ይሰጣቸዋል።

የልጆች ጥቅማ-ጥቅም፦ በኖርዌይ ነዋሪ ለሆኑ፡ እድሜያቸው ከ18 አመት በታች ለሆኑ ልጆች፡ የገንዘብ ድጋፍ ይደረጋል። ይህም ልጆች በመኖራቸው ምክንያት የሚወጣውን ተጨማሪ ወጪ ለማገዝ ታሳቢ ያደረገ ነው፡፡


የአንክብካቤ ማድረጊያ ገንዘብ፡ መዋዕለ ሕጻናት ላልገቡ እድሜያቸው አንድና ሁለት አመት ለሆናቸው ልጆች የሚደረግ የገንዘብ ድጋፍ ነው። በግማሽ ፈረቃ መዋዕለ ሕጻናት ለገቡ ልጆች ክፍያው ይቀንሳል፡፡


ስለ ልጅ ጥቅማጥቅም እና ስለ ገንዘብ እንክብካቤ ጥቅማጥቅም መረጃ በNAV ድረ-ገጽ ላይ ማግኘት ይችላሉ።

የባንክ ሒሳብ

በኖርዌይ ውስጥ ያሉ ሁሉም አዋቂዎች የራሳቸው የባንክ ሂሳብ አላቸው። ብዙ ልጆች እና ወጣቶችም የባንክ ሂሳብ ኣላቸው። ደመወዝ፡ ማህበራዊ ዋስትና ወይም ጡረታ ሲቀበሉ ገንዘቡ በቀጥታ ወደ ባንክ ሂሳብዎ ይገባል። የባንክ ሂሳብ ለመክፈት የኖርዌይ የግል መታወቂያ ቁጥር (ዲ-ቁጥር) ያስፈልጋል።

የኢንተርነት ባንክ አገልግሎት

አብዛኛዎቹ አዋቂዎች በኢንተርነት ባንክ ይጠቀማሉ። ይህ የባንክ ሂሳብን እንቅስቃሴ በቀላሉ ለማየት፣ገቢዎችን እና ወጪዎችን ለመከታተል እና ወጪዎችን ለመክፈል ያስችላል። ኢንተርነት ባንክ በኮምፒተር፣ ታብሌት ወይም ስማርትፎን በኩል መግባት ይቻላል። ወደ ኢንተርነት ባንክ ለመግባት ግን የባንክ መለያ ወይም የባንክ ልዩ መለያ ቁጥር (BankID) በሞባይል ስልክዎ ላይ እንዲኖር ያስፈልጋል።

የባንክ ብድር

በኖርዌይ መኪና ወይንም ቤትን የመሳሰሉ ትልልቅ ነገሮችን ለመግዛት ከባንክ መበደር የተለመደ አሰራር ነው፡፡ ስንበደርም ከባንኩ ጋር የምንፈጽመው ስምምነት (ውል) ይኖራል፡፡ ክፍያችንን በየወሩ አሊያም በየሶስት ወሩ እስከ መቼ እና ምንያህል መክፈል እንዳለብን የሚያሳይ የክፍያ የጊዜ ሰሌዳ ይሰጠናል፡፡ በዚሁም፡ ለባንኩ ክፍያ ከነወለዱ እንከፍላለን።

የብድር ክፍያ ፡ ለብድሩ የምንከፍለው ክፍያ ሲሆን፡ ይኸውም በየወቅቱ ልንመልስ የተስማማነው የገንዘብ መጠን ማለት ነው፡፡


ወለድ፡ ለባንክ ወለድ እንከፍላለን፡፡ ወለድ ማለት የተበደርነው ገንዘብ የአገልግሎት ዋጋ ነው፡፡ ወለዱም በተበደርነው የብድር መጠን ልክ የሚሰላ ነው፡፡


ኣብዛኛውን ግዜ፡ በመደበኛነት በየወሩ ወይም በየሩብ ዓመት ክፍያዎችን እና ወለድ እንከፍላለን።

በጀት

በጀት በአንድ በተወሰነ ጊዜ ውስጥ የሚከናወኑ ወጪና ገቢን ያመለክታል፡፡ ድርጅቶችም ሆኑ ግለሰቦች የራሳቸው የበጀት አሰራር አላቸው፡፡ ብዙ ቤተሰቦች የወር በጀት ይይዛሉ፡፡ ይህ ደግሞ ገቢና ወጪያቸውን በቀላሉ መመልከት እንዲችሉ ይረዳቸዋል፡፡ ቤተሰቦች ገንዘባቸውን በምን መንገድ ማውጣት እንዳለባቸው እቅድ ይነድፋሉ፡፡ በጀት ለቁጠባ እና ከእቅድ ውጪ ለሚገጥሙን አንዳንድ ወጪዎች የሚሆነንን ገንዘብ አጠቃሎ ይይዛል፡፡

En mann og en kvinne sitter ved et bord. På bordet er det papirer og en kalkulator og en PC. De ser konsentrerte ut. De lager et budsjett.  Foto
GettyImages

ኣብራችሁ ተወያዩ

  • በኖርዌይ የሚኖር መደበኛ ቤተሰብ ምን ገቢና ወጪዎች ኣሉት?
  • ምን አይነት ያልታሰቡ ወጪዎች ሊኖሩ ይችላሉ?
  • ብዙ ገንዘብ የምታወጣው በምን ላይ ነው?
  • ትንሽ ገንዘብ ለማውጣት ምን ማድረግ ትችላለህ?

የበርግ ቤተሰቦች በመኖሪያ ቤታቸው አንድ ክፍል ውስጥ ሰብሰብ ብለው ተቀምጠዋል፡፡ እናት እና አባትም የወሩን ገቢና ወጪ በጀት እየሰሩ ነበር። አስፈላጊ የሆኑ ክፍያዎች በሙሉ ተከፍለው አሁን እጃቸው ላይ 4,000 ክሮነር የሚሆን ተርፏል። እናም አሁን ይህንን ገንዘብ በምን ላይ ማዋል እንዳለባቸው እየተነጋገሩ ነው፡፡

  • እናት አዲስ የክረምት ኮት ትፈልጋለች። ታደርገው የነበረው ኮት ጊዜው ያለፈበትና ያረጀ ነው።
  • አባት ደግሞ ገንዘቡ ባንክ እንዲቀመጥ ይፈልጋል፡፡ ያልታሰበ ወጪ ሊከሰት ይችላል?
  • ልጃቸው ደግሞ ከጓደኞቹ ጋር የእግር ኳስ ልምምድ ለማድረግ መሄድ ይፈልጋል፡፡ ለዚሁም አዲስ የእግር ኳስ ጫማ ያስፈልገዋል።
  • ሴት ልጃቸው ደግሞ የትምህርት ቤት ቦርሳ ያስፈልጋታል። እሷም አድጋለች እና አዲስ ልብስ ትፈልጋለች።

ቤተሰቡ ገንዘቡን ለማውጣት ለምን ቅድሚያ መስጠት እንዳለበት አብራችሁ ተነጋገሩ።

Kvinne sitter i stua med nettbrett og papir. Budsjett. Foto
GettyImages

ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ

ገቢ ምን ማለት ነው?

ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ

ጥቅል ክፍያ ምን ማለት ነው?

ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ

በጀት ምን ማለት ይነው?

ትክክል ወይም ስህተት የሆነውን ይምረጡ፡፡

መግለጫዎቹን ያንብቡ:: ትክክል የትኛው ነው? ስህተቱ የትኛው ነው?

የልጆች ድጋፍ ማለት እድሜያቸው ከ18 አመት በታች የሆኑ ልጆች የሚያገኙት የገንዘብ ድጋፍ ነው፡፡
ኖርዌይ ውስጥ ኑሮ ርካሽ ነው፡፡
አብዛኛዎቹ ኖርዌጅያውያን ሁለቱም ወላጆች ከቤት ውጪ ስራ ተቀጥረው የሚሰሩ ናቸው፡፡
የኢንተርነት የባንክ አገልግሎት በኖርዌይ ውስጥ የተለመደ አይደለም፡፡
ካባንክ ብር ስትበደሩ ወርሃዊ የብድር ክፍያችሁን እና ወለድ ለባንኩ ትከፍላላችሁ፡፡

ትክክል ወይም ስህተት የሆነውን ይምረጡ፡፡

መግለጫዎቹን ያንብቡ:: ትክክለኛው የቱ ነው? ስህተቱ ምንድነው ?

የኦንላይን የባንክ አገልግሎት አካውንታችሁን ከፍቶ ለመግባት የባንክ መታወቂያ ያስፈልጋችኋል ፡፡
ወለድ ማለት የተበደራችሁት ገንዘበ ዋጋ ማለት ነው፡
ወለድ ከወሰዳችሁት ብድር ላይ በመቶኛ የሚሰላ ገንዘብ ነው፡፡
በጀት በድርጅቶች ብቻ የሚሰራ ነገር ነው፡፡
ለኖርዌጅያውን የራሳቸው የሆነ የባንክ አካውንት መክፈት የተለመደ ነገር አይደለም፡፡