የሳሚ ሕዝቦች
የሳሚ ሕዝቦች
ሳሚዎች የኖርዌይ ቀደምት ነዋሪዎች ናቸው፡፡ ሳሚዎች በአራት የተለያዩ አገራት ይኖራሉ፡ በኖርዌይ፣ ስዊድን፣ ፊንላንድና፣ ራሺያ፡፡ ሳሚዎች በኖርዌይ ከሚኖሩ ሕዝቦች ሁሉ ቀደምቶቹ ናቸው፣ እንዲሁም የተለያዩ አይነት የሳሚ ቋንቋዎች አሉ። የሳሚዎች ቋንቋ ከኖርዌጃውያን ቋንቋ ፈጽሞ የተለየ ነው። የኖርዌጃውያንን ቋንቋ ብቻ የሚችል ሰው ሳሚዎችን ሊረዳቸው አይችልም። በኖርዌይ የሚኖሩት ሁሉም ሳሚዎች የኖርዌይን ቋንቋ በሚገባ የሚችሉ ናቸው። ብዙዎችም የሳሚን ቋንቋ ይናገራሉ።
የሳሚዎች ብሔራዊ ቀን የካቲት 6 ነው። በዕለቱ፡የሳሚዎች ባንዲራ በመላው ኖርዌይ ይውለበለባል፡፡ ሳሚዎች ኮፍቴ የሚባል ብሔራዊ አልባሳት አላቸው። ሳሚዎች አሁንም ይህንን ልብስ የሚለብሱት እንደ ሰርግ ባሉ ልዩ ዝግጅቶች ላይ ነው። አንዳንድ ሳሚዎቸም ይህንን ልብስ ለዕለት ተዕለት ጉዳዮች ይለብሱታል፡፡
ኖርዌጃውያን ከ150 አመታት በፊት ሳሚዎችን ሙሉ በሙሉ ኖሮውጃውያን ለማድረግ ጥረት አድርገው ነበር፡፡ የሳሚዎች ልጆች ወደ ኖርዌጃውያን ትምህርት ቤቶች እንዲሄዱ ይገደዱ ነበር፣ የሳሚ ቋንቋም እንዲማሩ አይፈቀድላቸውም ነበር። በ1959 ዓ.ም ግን ሳሚዎች በትምህርት ቤቶች ውስጥ የራሳቸውን ቋንቋ እንዲጠቀሙ ፈቃድ አገኙ። በ1902 ዓ.ም የወጣው ሕግ፡ በኖርዌይ ውስጥ መሬት መግዛት የሚችለው የኖርዌይን ቋንቋ የሚናገር፣ የሚያነብና፣ የሚጽፍ ሰው ብቻ ነው የሚል ነበር። ይህ አሰራርም እስከ 1965 ዓ.ም ድረስ ቀጥሎ ነበር። አሁን ያለው ሁኔታ ግን ከዚህ የተለየ ነው። የሳሚዎች ፓርላማ በ1989 ዓ.ም. ተመሰረተ። የሳሚዎች ፓርላማ የሳሚዎችን መብት፡ በተለይ ደግሞ ከባሕልና ከትምህርት አንጻር መሆኑን ያረጋግጣል። ሳሚዎችን የሚወክሉ የፓርላማ አባላት በየአራት አመቱ ይመረጣሉ።
ኣብራችሁ ተወያዩ
- በትውልድ አገራችሁ ቀደምት ነዋሪዎች አሉን? አኗኗራቸውስ ምን ይመስላል?
- እስቲ ስለተለያዩ አናሳ ሕዝቦች ሁኔታ ተነጋገሩ፡፡
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ
ሳሚዎች የሚኖሩባቸው አገራት እነማን ናቸው?
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ
ሳሚዎች በባሕላቸው ለመኖር የሚሰሩት ስራ ምንድነው ?
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ
ከ1902 ጀምሮ የወጣው ሕግ የኖርዌይ ዜጋ የሆነ አና ኖርዌይን ቋንቋ መናገር ፣ማንበብ ፣ እና መጻፍ የሚችሉ የኖርዌይ ዜጎች ብቻ መሬት መግዛት ይችላሉ የሚል ሕግ ወጥቷል ፡፡ ይህ ሕግ በይፋ የታወጀው መቼ ነበር?
ትክክል ወይም ስህተት የሆነውን ይምረጡ
መግለጫዎቹን ያንብቡ። ትክክል የትኛው ነው? ስህተት የትኛው ነው?
ትክክል ወይም ስህተት የሆነውን ይምረጡ
መግለጫዎቹን ያንብቡ፡፡ ትክክል የትኛው ነው? ስህተት የትኛው ነው?