ማንነት
ፊልሙን ይመልከቱ
ማንነት
እራሳችንን የምናይበትን መንገድ ማንነት ብለን እንጠራዋለን፡፡ ማንነት በባሕሪያችንና ስብእናችንን መሰረት አድርጎ የሚያድግ ነው፡፡ ማሕበራዊ ሁኔታዎች ለምሳሌ የምንኖርበት ስፍራ፣አብረናቸው ጊዜ የምናሳልፋቸው ሰዎች፣ እንዲሁም ፍላጎታችን ሳይቀር የራሱ ሚና አለው፡፡
ወሲባዊ ማንነት
የምናፈቅረው ሰውና ጸታዊ ፍላጎት የምናሳይበት መንገድ ወሲባዊ ማንነታችንን ይወስናሉ፡፡ አንዳንድ ሰዎች፡ ከራሳቸው ጾታ ኣንጻር የሆኑትን የሚመኙ ሲሆኑ ሌሎች ደግሞ ተመሳሳይ ጾታ ካላቸው እንደሚመኙ ራሳቸውን ይገልጻሉ። ኣንድዳንድ ሰዎች ደግሞ፡ የትኛውን ጾታ እንደሚፈቅዱ መግለጽ የማይፈልጉ ኣሉ።
ጾታዊ ማንነት
ጾታ የማንነታችን መግለጫ ኣንዱ አካል ነው። በተለምዶ ስነኣካል (ፊዚዮሎጂ) በባህላዊ መንገድ የእያንዳንዳችን ስንወለድ እንደ ወንድ ወይም ሴት ብሎ ይወስናል። ይህ ግልጽ በሆነ የፆታ ሚና ቅጦች ተጠናክሯል። በኣሁኑ ጊዜ፣ በእነኚህ ምደባዎች ዙሪያ ለሁሉም ሰው እንድማይስማማ በግልጽ እየታየ ነው። ስለሆነም፡ አንዳንድ ሰዎች፡ ራሳቸውን ከተወለዱበት ጾታ ውጭ ወይም በሁለቱ ባህላዊ ጾታዎች መካከል እንደሆኑ እራሳቸውን ይገልጻሉ። በኣለባበሳችን ወይም በሌላ መንገድ ጾታችንን ለመግለጽ የምናደርገው ሁሉ፡ ሥርዓተ-ፆታ ይባላል።
ኣብራችሁ ተወያዩ
- በማንነት እና ብዙህነት መካከል ያለውን ግንኙነት ተወያዩበት።
- ጾታዊ ማንነትን በሁለት ምድቦች መክፈል ምን ጉዳት አለው? ጥቅሞችስ አለውን?
- 'የፆታ አገላለጽ' የሚለውን ቃል ጋር ከምን ታገናኘዋለህ?
- ኣንድ ሰው፡ በሥርዓተ-ፆታ እና ወሲባውነት ያለው ባህላዊ ግንዛቤ ቢጥስ፡ ፈተናዎቹ ምን ናቸው ብለው ያስባሉ?
- LHBTQI' የሚለው ቃል ብዙውን ጊዜ ጾታን እና የጾታ ደንቦችን ስለሚጥሱ ሰዎች ያገለግላል። ፊደሎቹ ምን እንደሆኑ ይወቁ።
አረፍተ ነገሩን አሟሉ
ማንነታችን የሚቀረጸመው በባሕሪያችን እና ………..ላይ ነው፡፡
አረፍተ ነገሩን አሟሉ
በፍቅር የምንወድቅለት እና ጾታዊ መሳሳባችን ……እንድንወስን ይረዳናል፡፡
አረፍተ ነገሩን አሟሉ
ሰዎች በአለባበሳቸው ወይም ለጾታ ያላቸውን ትኩረት …..ብለን እንጠራዋለን፡፡
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ
ስነልቦናዊ ጾታዊ ስርአታችንን የሚያጠናክረው ምንድነው?
ትክክል ወይም ስህተት የሆነውን ይምረጡ
መግለጫዎቹን ያንብቡ:: ትክክል የትኛው ነው? ስህተት የትኛው ነው?