ዱግናድ
ፊልሙን ይመልከቱ
ዱግናድ
ዱግናድ ክፍያ የሌለው የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ነው፡፡የዱግናድ ማህበረ ሰብ ጥረት ነው፡፡ይህ በክለቦች እና በማሕበራት ውስጥ የተለመደ አይነት ሥራ ነው፡፡ቤቶችን ለመሥራት ትብብር፣ለምሳሌ የአካባቢው ነዋሪዎች ክረምቱ ወጥቶ ጸደይ ሲሆን አካባቢያቸውን በህብረት ለማጽዳት በዱግናድ መንፈስ ተሳትፎ ያደርጋሉ፡፡በብዙ መዋእለ ሕጻናት ውስጥ ብዙ ወላጆች በአመት ለአንድ አሊያም ለብዙ ጊዜያት በዱግናድ መገናኘት የተለመደ ነገር ነው። የቆሸሹ የመዋዕለ ሕጻናቱን አሻንጉሊቶች ያጥባሉ አሊያም ከቤት ውጪ ለተበላሹ ነገሮች ጥገናዎችን ያደርጋሉ፡፡
በኖርዌይ ውስጥ ብዙ ልጆች በተደራጀ የመዝናኛ አንቅስቃሴ ይሳተፋሉ፣ እነዚህ እንቅስቃሴዎችም ወላጆች በበጎ ፈቃድ እንዲከናወን ያደርጋሉ፡፡ ለምሳሌ፡ ወላጆች ያገለገሉ ወይንም የማይፈለጉ ነገሮችን በቅናሽ በመሸጥ አሊያም የተለያዩ የባሕላዊ ዝግጅት መርሃግብሮችን በማዘጋጀት ለማሕበሩ የድጋፍ ማሰባሰብ ያደርጋሉ፡፡
በኖርዌይ ዱግናድ (የበጎፈቃድ አገልግሎት) የቆየ ልማድ ነው። በመላው ዓለም በሚገኙ አብዛኛዎቹ አርሶ አደር ማሕበረሰቦች ዘንድ ተመሳሳይ ልማድ አለ።
በ 2004 ዓ.ም. “ዱግናድ” የሚለው ቃል ኖርዌይ ውስጥ ብሔራዊ ቃል ሆኖ ተመርጧል።
ኣብራችሁ ተወያዩ
- ስለ ዱግናድ ምን ታስባላችሁ? ይህንን ልምድ ከዚህ ቀደም ታውቁታላችሁን?
- በኖርዌይ በዱግናድ ውስጥ እንድትሳተፉ ግብዣ ቀርቦላችሁ ያውቃልን?
- አንዳንድ ክለቦች እና ማህበራት በዱግናድ ውስጥ በአካል ተሳትፎ ማድረግ የማይችሉትን ሰዎች የተወሰነ ክፍያ በመክፈል በገንዘባቸው ተሳትፎ ማድረግ የሚችሉበትን ስርአት ዘርግተው ተግባራዊ አድርገዋል። ስለዚህ ነገር ምን ታስባላችሁ?
ዛሬ ሰኞ ነው፡፡ ሁለት አባቶች ልጆቻቸውን ከመዋዕለ ሕጻናት እየወሰዱ ነው። በሳምንቱ መጨረሻ በመዋዕለ ሕጸናቱ ስለ ነበረው ዱግናድ እየተጫወቱ ነው።
ሄንሪክ፡ በድጋሚ ስለተገናኘን ደስ ብሎኛል! ያከናወነውን ስራ ብዛት በጣም የሚያስገርም ነው፡፡ አዲሱ የመጫወቻ ቤት በጣም ቆንጆ ሆኗል።
አርኔ፡ አዎን፡ እንደዚያ በጋራ መስራት በጣም መልካም ነው፡፡ነገር ግን የትሩልስ ቤተሰቦች በዱግናድ አይሳተፉም።
ሄነሪክ፡ እኔም አለመገኘታቸውን አስተውያለሁ። የበጎ ፈቃድ አገለግሎት ቢሆንም፡ እንዲህ ማድረግ ጥሩ አይመስልም።
አርኔ፡ አዎን በእርግጥ አንዳንድ ጊዜ ሁኔታዎች ላይመች እንደሚችል እረዳለሁ፣ ነገር ግን ሁሉም ቀን የማይመች ………?
ሄነሪክ፡ ሕምም… በእርግጠኝነት ትሩልስ በመጫወቻ ቦታ እንደሌሎቹ ልጆች እኮ ይጫወት ይሆናል።
- እስቲ ከላይ ስላለው ሁኔታ ተነጋገሩ። ሄነሪክ እና አርኔ እንዲህ የተሰማቸው ለምንድነው?
- በዱግናድ ውስጥ ተሳትፎ አለማድረግ ምን አይነት መዘዝ ሊያስከትል ይችላል ብላችሁ ታስባላችሁ?
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ
ዱግናድ ምንድነው ?
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ
በመዋዕለ ሕጻናት ውስጥ ያለው አይነተኛ የዱግናድ ስራ ምንድነው?
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ
በመሰረቱ ዱግናድን የሚያደራጀው ማነው?
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ
ዱግናድ በኖርዌይ ብቻ የሚገኝ ክስተት ነውን?
ትክክል ወይንም ስህተት የሆነውን ይምረጡ
መግለጫዎቹን ያንብቡ:: ትክክል የትኛው ነው? ስህተት የትኛው ነው?
ትክክለኛውን ምስል ይምረጡ
የትኛው ምስል የተለመደውን ዱግናድ ያሳያል፡ ከአንድ በላይ ምስል መምረጥ ይችላሉ፡፡