ጤና እና የሕይወት ዘዬ
ፊልሙን ይመልከቱ
ጤና እና የሕይወት ዘዬ
ታሪካዊ እድገት
በአሁኗ ኖርዌይ የኑሮ ደረጃ ከፍተኛ ነው፡፡ ከባድ ለሆኑ ብዙ በሽታዎች መድሃኒት አለ፣የማሕበራዊ ደህንነት ስርዓቱም ሰዎች የሕክምና እርዳታና መድሓኒቶችን ለሁሉም ሰው ይዳረስ ዘንድ የሚያግዝ ስልት አለው። ልጆች ለብዙ በሽታዎች የሚሆኑ ክትባቶችን በነጻ ያገኛሉ። በቀደሙት ጊዜያት፡ በኖርዌይ ብዙ ሰዎች ከድህነት ጋር በተያያዘ እንደ የምግብ እጥረት እና የሳንባ ነቀርሳ ባሉ በሽታዎች ምክንያት ይሞቱ ነበር። ብዙዎችም፡ ሕክምና ሊያገኙ ባለመቻላቸው፡ ይሞቱ ነበር፡፡
የኖርዌይ የህዝብ ጤና ሁኔታ ባለፉት 100 ዓመታት ውስጥ በጣም ተሻሽሏል። ይህ ሊሆን የቻለው፡ በአብዛኛው የማሕበርዊ ደሕንነት ኣገልግሎት ለጥሩ እና ደህንነቱ የተጠበቀ ህይወት ለመኖር ብዙ እና የተሻሉ እድሎችን ስለሚሰጥ ነው። በኖርዌይ የሚኖሩ ሰዎች ከቀድሞው የበለጠ ረጅም ዕድሜ ይኖራሉ። ብዙ አረጋውያንም ከእነርሱ በፊት ከነበሩት አረጋውያን የበለጠ የጤንነት ሕይወት መኖር ጀምሯል። ይሆም፣ ረጅም፡ ጥሩ እና ንቁ ህይወት እንዲመሩ ኣስችሏቸዋል።
ይህ ማለት ኖርዌይ በሽታ የሌለባት ኣገር ናት ማለት አይደለም። ለምሳሌ፡ ብዙ ሰዎች ከጡንቻዎች፡ ጅማቶች፡ ነርቮች፣ የጀርባ ኣጥንትን እንዲሁም የደም ስሮችን በተያያዙ በሽታዎች ይሰቃያሉ። የስኳር በሽታ እና ከመጠን በላይ ውፍረትም እየጨመረ ነው። በዛሬው ግዜ፡ የልብ በሽታና ካንሰር ይተለመዱ የሞት መንስኤዎች ናቸው።
የጤና ችግሮችን ማስቀረት
የጤንነታችን ሁኔታ ብዙ ጊዜ ከአኗኗራችን ጋር የተያያዘ ነው። ይህ ለሁለቱም አካላዊ እና አእምሯዊ ጤንነታችን ይመለከታል። ጤናማ ምግብ ከተመገብን እና የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ካደረግን ረዘም ላለ ጊዜ በጤና የመቆየት እድሉ ሰፊ ነው። የሚያጨሱ ሰዎች ለካንሰር እና ለደም ቧንቧ በሽታዎች የመጋለጥ እድላቸው ከፍተኛ ነው።
ምንም እንኳን የማህበራዊ ደሕንነት ኣገልግሎት መንግስት የህዝቡን ጤና የመጠበቅ ሃላፊነቱን የሚሸከም ቢሆንም፣ በብዙ ሁኔታዎች ህይወቱን እንዴት እንደሚመራ እና ጤናን እንዴት እንደሚንከባከብ የግለሰቡ ጉዳይ ነው።
የአእምሮ ጤና ልክ እንደ አካላዊ ጤንነት አስፈላጊ ነው። ብዙ ሰዎች ከሌሎች ሰዎች ጋር መግባባት ይወዳሉ፣ ይኸውም፡ በቤተሰብ ውስጥ መኖር፣ ጥሩ ጓደኞች በማፍራት ወይም ጥሩ የስራ ባልደረቦች በማግነት ሊሆን ይችላል። ጤናማ አስተሳሰብ መያዝ፣ በውስጣችን መረጋጋት፣ ጥሩ እንቅልፍ መተኛት እና ደስተኛ መሆን ለጤናችንም ጠቃሚ ነው። ጥሩ ሳቅ ረጅም ዕድሜ ለመኖር ይረዳል የሚል የኖርዌይ አባባል አለ።
ስርዓተ ምግብ
- በአመጋገብ እና በጤና መካከል ያለውን ግንኙነት ተወያዩ።
- አመጋገባችሁ ወደ ኖርዌይ ከመምጣታችሁ በፊት እንደ ነበረው አይነት ነውን?
- በአየር ጠባይ እና አመጋገብ መካከል ግንኙነት አለን?
- ጤነኛ ያልሆኑ ምግቦች የትኞቹ እንደሆኑ ታስባላችሁ?
- ምን አይነት ምግቦች ጤናማ ናቸው ብለው ያስባሉ?
ከስደተኞች ጋር ግንኙነት ያላቸው የጤና ባለሙያዎች፡ ስለ የስደተኞች ጤንነት ይጨነቃሉ። ከኖርዌጂያን የበለጠ” ስደተኞች የሚከተሉትን ችግሮች እንዳጋጠማቸው በማየታቸው ያሳስባቸዋል።
- የስኳር በሽታ
- ከልክ ያለፈ ውፍረት
- ደካማ የጥርስ ጤንነት
- የተመጣጠነ ምግብ እጥረት፣በተለይ የብረት ንጥረ-ነገር እና የቫይታሚን ዲ እጥረት፡፡
- ድብርት
ኣብራችሁ ተወያዩ
የስኳር በሽታ - ካንሰር - ኣስም - ከልክ በላይ ውፍረት --
ኣለርጂ - የልብና የደም ቧንቧ በሽታዎች
- በአኗኗር ዘዬ እና በእነዚህ በሽታዎች መካከል ያለውን ግንኙነት ተወያዩ።
- እናንተ ትኖሩበት በነበረው አገር ውስጥ እነዚህ በሽታዎች የተለመዱ ነበሩን?
- ስደተኞች ወደ ኖርዌይ ከመምጣታቸው በፊት ካጋጠሟቸው የጤና እክሎች ይልቅ ሌሎች የጤና ችግሮች ሊያጋጥሟቸው የሚችሉባቸውን ምክንያቶች ተወያዩ።
- እርስዎ በሚያውቋቸው አገሮች እነዚህ በሽታዎች የታወቁ ናቸው?
በጋ ነው። ሶስቱ የሃንሰን ቤተሰብ ልጆች (የሰባት፣ ዘጠኝ እና አስራ ኣመት)፡ ከትምህርት ቤት እረፍት ላይ ናቸው። ቀኖቹን ረዥም እና አሰልቺ እየሆኑባቸው ነው። አብዛኛዎቹ የልጆቹ ጓደኞች ራቅ ብለው በመሄድ ወይም ሌሎች ነገሮችን በመስራት ተጠመዷል።እናት እና አባት ከስራ በኋላ ደክመው ወደ ቤት ስለሚመጡ፡ ከስራ ውጭ እቤታቸው ዘና ለማለት ይፈልጋሉ። ስለዚህ ቤተሰቡ በአፓርታማው ውስጥ ብዙ ጊዜ ያሳልፋል።
- ስለ ቤተሰቡ ሁኔታ ምን ታስባላችሁ?
- እነዚህ ወላጆች ስለ ምን ነገር ማሰብ አለባቸው ብለህ ታስባለህ?
- ይህ ሁኔታ የልጆቹንም ሆነ የወላጆቻቸውን ጤና ሊጎዳ ይችላልን?
- ሁኔታው በልጆች ላይ ሌላ ነገር ሊነካ ይችላል?
መሕመት የስድስተኛ ክፍል ተማሪ ነው። በክፍሉ ውስጥም ብዙ ጥሩ ጓደኞች አሉት። በእረፍት ሰአት በብዛት እግር ኳስ ይጫወታሉ። አብዛኞቹ ጓደኞቹ፡ በአካባቢው የእግር ኳስ ቡድን ውስጥም ይጫወታሉ። በሳምንት ሁለት ቀን፡ ከሰአት በኋላ ላይ ልምምድ ያደርጋሉ። መሕመት ለቡድኑ መጫወት ይፈልጋል፡ ወላጆቹ ግን ሀሳቡን አልወደዱትም። ይህን ለማድረግ፡ ገንዘብ ያስከፍላል፡ ቤተሰቡ ደግሞ የገንዘብ ኣቅም የላቸውም።
- ይህ ሁኔታ የመሕመትን ጤና በምን መንገድ ሊጎዳው ይችላል?
- ስለ ቤተሰቦቹ ሁኔታስ ምን ታስባላችሁ?
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ
ዛሬ በኖርዌይ ያለው የኑሮ ደረጃ ምን ይመስላል?
አረፍተ ነገሩን አሟሉ
……..ካደረግን ጤናኛ ለረጅም ጊዜ ለመቆየት የተሻለ እድል ይኖረናል፡፡
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ
ትክክል የትኛው ነው?
ትክክል ወይም ስህተት የሆነውን ይምረጡ
መግለጫዎቹን ያንብቡ:: ትክክል የትኛው ነው? ስህተት የትኛው ነው?
ትክክል ወይም ስህተት የሆነውን ይምረጡ
መግለጫዎቹን ያንብቡ:: ትክክል የትኛው ነው? ስህተት የትኛው ነው?
ትክክለኛውን ምስል ይምረጡ
የትኛው ስዕል ጤናማ የሕይወት ዘዬን ይገልጻል? ከአንድ በላይ ስዕሎችን መምረጥ ይቻላል።