ወደ አዲስ አገር መፍለስ
ወደ አዲስ አገር መፍለስ
ሰበነ፣ በመጨረሻ ኖርዌይ በመድረሳችን በጣም ደስተኛ ነኝ። እዚህ በጣም ጥሩ ነው፣ እና መጪው ጊዜ አሁን ለእኛ እና ለልጆቻችን ደህንነት የተጠበቀ እንደሆነ ይሰማኛል።
ኣማኒኤል፣ እዚህ መኖር መልካም ነው? እንግዳ በሆነ አገር ውስጥ መሆን በጣም ሰልችቶኛል። ሁሉም ነገር በጣም አስቸጋሪ ነው፡ ሁሉም ነገር ምንም ኣይሰራም። ሥራ የለኝም፡ ቋንቋውን አይገባኝም እና በሁሉም ነገር እርዳታ ያስፈልገኛል። እዚህ ያሉ ሰዎች በጣም የሚገርም ባህሪ አላቸው። እነሱ ከእኔ በተለየ መልኩ ያስባሉ።
ሰበነ፣ ሁሉም ነገር መልካም እንደሆነ አስቤ ነበር።
ኣማኒኤል፣ ከጥቂት ሳምንታት በፊት ነገሮች በጣም የተሻሉ ነበሩ። ያኔ፡ ሕይወት በእርግጥ እንዴት የተለየ እንደሆነ አልገባኝም ነበር። በጣም ብዙ አጥተናል፡ ቤተሰብ፣ ጓደኞች፣ ወጎች እና ቋንቋችን።
ወደ ኣዲስ አገር በሚሄዱ ሰዎች ላይ የሆነ ነገር ይከሰታል። ኣብዛኛውን ጊዜ፡ ሰዎች ባለ ሶስት ደረጃዎች፡ “የአእምሮ የፍልሰት ሂደት” ብለን በምንጠራው ሁኔታ ያልፋሉ። እነዚህ የተለያዩ ደረጃዎች በሰው ላይ የሚቆዩበት ጊዜ ከሰዉ ወደ ሰው የተለያየ ነው።
ደረጃ 1
መጀመሪያ ላይ ደስተኛ እና ብሩህ ተስፋ መሰማቱ የተለመደ ነው። ብዙውን ጊዜ ሥራ የሚበዛበት ወቅት ነው። ብዙ የሚደረግ ነገር አለ፡ ሁሉም ነገር አዲስ በመሆኑ አስደሳች ሊሆንም ይችላል። ስለዚህ፡ ሰዎች ስላገኟቸው አዳዲስ እድሎች የበለጠ ማሰብ ይቀናቸዋል፣ እናም ትተውት ስለመጡና ስላጡት ነገር እምብዛም ላያስቡ ሊሆኑ ይችላሉ።
ደረጃ 2
ከጥቂት ቀናት፣ ሳምንታት ወይም ወራት በኋላ፣ አብዛኛው ሰው በአዲሱ ሀገር ውስጥ ያለው ህይወት ከባድ እንደሆነ ይሰማዋል። መንቀሳቀስ የሚያስከትለውን መዘዝ በድንገት ይገነዘባሉ። በአዲሱ አገር፡ያልለመዱት ነገር በሙሉ ስጋት እንዲሰማቸውው ያደርጋቸዋል። ሰዎች ከዚህ ቀደም የነበሩት ዓይነት መሆን ሲያቅታቸው፡ ተስፋ ይቆርጣሉ፡ እናም ከዚህ በፊት የነበራቸውን ሕይወት መናፈቅ ይጀምራሉ።
ደረጃ 3
ከተወሰነ ጊዜ በኋላ, ለብዙ ሰዎች ህይወት እንደገና ቀላል ይሆናል. ከቋንቋውም ሆነ ከአዲሲቷ አገር ሥርዓት ጋር በተያያዘ የበለጠ ተረድተዋል። መጪው ጊዜ ብሩህ ይመስላል። እርምጃውን ተቀብለዋል። ቀስ በቀስ, በአዲሱ ሀገር ውስጥ የህይወት እና የእሴቶችን አወንታዊ ገጽታዎች መቀበል ይጀምራሉ. ይህ ከትውልድ አገራቸው ይዘውት ከመጡት እሴት እና አስተሳሰብ ጋር ሲጣመር በአዲሱ ማህበረሰብ ውስጥ ቦታቸውን ያገኛሉ።
ኣብራችሁ ተወያዩ
- አማኒኤል እና ሰበኔ እንዴት ናቸው? እነሱ የሚሉት፡ ከተሞክሮኸው የተለየ ሆኖ ይሰማሃል ወይ?
- አማኒኤል ብዙ እንዳጣ ይናገራል። ይህ ለጤንነቱ ምን ማለት ሊሆን ይችላል?
- ኣለ ፈቃዱ ወደ አዲስ አገር የሄደ፡ በፈቃደኝነት ከሄደ ሰው ኣንጻር፡ እነዚህን ደረጃዎችን በተለየ ሁኔታ ሊሞከረው ይችላልን?
- የቤተሰቡ አባላት በተለያዩ ጊዜያት እነዚህን ደረጃዎች የሚያልፉ ከሆነ፡ በቤተሰቡ ውስጥ ምን ዓይነት ሕይወት ሊኖር ይችላል?
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ
በአዕምሮአዊ ስደት ሂደት ስንት ደረጃዎች አሉት ?
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ
የትኛው ደረጃ በ…..ባሕሪይ ይገለጣል
- በአዲሱ አገር ያለው አኗኗር ከባድ ስሜት አለው
- ስፍራን የመቀየርን መዘዝ ከማወቅ የተነሳ
- ቀድሞ የነበረውን ሕይወት ከመናፈቅ አንጻር
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ
እነኚህ የተለያዩት ደረጃዎች በምን ያክል ጊዜ ያበቃሉ?
አረፍተ ነገሩን አሟሉ
በአዲሱ አገር ያለውን የሕይወት እና እሴቶች እውቅና መስጠት ሲጀምሩ፡ እና ቀድሞ ከነበራችሁበት ሃገር ሕይወት እሴቶች እና አስተሳሰብ ጋር በማጣመር….....፡፡
ትክክል ወይም ስህተት የሆነውን ይምረጡ
መግለጫዎቹን ያንብቡ:: ትክክል የትኛው ነው? ስህተት የትኛው ነው?