የመግቢያ መርሃ ግብር እና የውህደት ሕግ
የመግቢያ መርሃ ግብር እና የውህደት ሕግ
የመግቢያ ፕሮግራሙ ዓላማ፦
- ለተሳታፊዎቹ መሰረታዊ የሆነ የኖሮዌያውያንን ቋንቋ ችሎታ እንዲኖራቸው ማስተማር፡፡
- ለተሳታፊዎቹ ስለ ኖርዌጅያውያን ማሕብረሰብ መሰረታዊ ግንዛቤ መስጠት።
- ተሳታፊዎችን ለሥራ ቅጥር ወይንም ለትምህርት ማዘጋጀት።
በኖርዌይ ያሉ ባለስልጣናት ሰዎች ወደ አዲስ ሀገር ሲመጡ ሥራ ማግኘት እና እራሳቸውን ማስተዳደር አስቸጋሪ እንደሆነ ይገነዘባሉ። ስለሆነም፡ የኖርዌይ ፓርላማ፣ (ስቶርቲንግ) የውህደት ህግ በመባል የሚታወቀውን ህግ ኣወጣ። የኖርዌይ የኣከባቢ ኣስተዳደሮች የመግቢያ ፕሮግራሙን ለስደተኞች የማቅረብ ተግባርን ያከናውናሉ።
ከሌሎች ነገሮች በተጨማሪ፣ የኖርዌይ የኣከባቢ ኣስተድደሮች፡ የመግቢያ ፕሮግራሙን የመስጠት ተግባር ያከናውናሉ። በዚህ ፕሮግራም ተሳታፊዎቹ የኖርዌይ ቋንቋን ይማራሉ፣ ስለ ኖርዌይ ማህበረሰብ፡ እና በኖርዌይ የስራ ገበያ እውቀትና ስልጠና ያገኛሉ። የፕሮግራሙ ዓላማ ተሳታፊዎች ፕሮግራሙን ሲያጠናቅቁ ወደ ሥራ ገበያ ወይም ትምህርት እንዲገቡ ነው። መርሃግብሩ፡ እንደ ሰውየው የቀድሞ ትምህርት እና ልምድ፡ ከሶስት ወር እስከ ሶስት አመት ሊወስድ ይችላል። ቢሆንም፡ በፕሮግራሙ የሚሳተፉ ሰዎች የገንዘብ ድጋፍ ያገኛሉ።
የመግቢያ መርሃ ግብር ማካተት አለበት
- የኖርዌይ ቋንቋ (ኖሽክ) ትምህርት
- በአዲሷ አገር ሕይወትን በአግባቡ መኖር ይችሉ ዘንድ መርዳት፡
- ለወላጆች መመሪያ መስጠት (ከ18 አመት በታች የሆኑ ልጆች ላሏቸው ወላጆች)፡
- ከሥራ ወይንም ከትምህርት ጋር የተገናኙ ይዘቶች፡
ምንጭ፦ IMDi
ኣብራችሁ ተወያዩ
- ስደተኞች የመግቢያ ፕሮግራም እንዲወስዱ ለምን እድል ይሰጣቸዋል?
- ለምንድነው ሁሉም ስደተኞች የመግቢያ ፕሮግራም እንዲወስዱ እድል ያልተሰጣቸው?
- በመግቢያ ፕሮግራሙ ውስጥ ተሳታፊዎች ምን ዓይነት መስፈርቶች መሟላት አለባቸው?
- በፕሮግራሙ ላይ የሚሳተፉት ምን የሚጠብቁ ይመስላችኋል? ህብረተሰቡ በፕሮግራሙ ውስጥ ከሚሳተፉት ምን ይጠብቃል?
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ
የመግቢያ መርሃ ግብሩ ዓላማ ምንድን ነው?
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ
የመተዋወቂያ መርሃግብሩ ለምን ያህል ጊዜ የሚቆይ ነው?
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ
የማቀናጀቱን ስራ የሚሰራው የትኛው አካል ነው?
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ
የትውውቁን መርሃግብር የሚያዘጋጀው ማነው?
ትክክል ወይም ስህተት የሆነውን ይምረጡ
መግለጫዎቹን ያንብቡ:: ትክክል የትኛው ነው? ስህተት የትኛው ነው?