የመጀመሪያ ደረጃ መለስተኛ ትምህርት ቤት

Lærerinnhold

Tips til undervisningen

Sammenlikn gjerne de ulike punktene med forholdene i deltakernes hjemland.

Snakk sammen

En ulikhet mellom norsk skole og den skolen mange deltakere kjenner til fra hjemlandet sitt, kan være det at elevene er forventet å argumentere for egne synspunkter i norsk skole. Læreren sitter ikke alltis på fasiten. En annen ting kan være at elevene flyttes opp til neste klassetrinn etter et skoleår uavhengig av innsats. Elevene får heller ikke karakterer i barneskolen.

Bruk gjerne tid på formålsparagrafen. Hva innebærer det at undervisningen bygger på kristne og humanistiske prinsipper? Hvilke prinsipper er dette? Er disse prinsippene problematiske for elever og foreldre med andre religioner og/eller kulturer? Snakk også gjerne sammen om betydningen av begrepene åndsfrihet, nestekjærlighet, tilgivelse, likeverd og solidaritet. Er dette universelle verdier?

Tips til undervisninga

Samanlikn gjerne dei ulike punkta med tilhøva i deltakarane sine heimland.

Snakk saman

Ein ting ved den norske skulen som gjerne er ulikt den skulen mange deltakarar kjenner frå heimlandet sitt, er at det er venta at elevane i den norske skulen skal argumentere for sine eigne synspunkt. Læraren sit ikkje alltid på fasiten. Ein annan ting kan vere at elevane blir flytte opp til neste klassetrinn etter eit skuleår uansett korleis dei har gjort det. Elevane får heller ikkje karakterar i barneskulen.

Bruk gjerne tid på føremålsparagrafen. Kva inneber det at undervisninga byggjer på kristne og humanistiske prinsipp? Kva er desse prinsippa? Er desse prinsippa problematiske for elevar og foreldre med tilknyting til andre religionar og/eller kulturar? Snakk òg gjerne saman om kva omgrepa åndsfridom, nestekjærleik, tilgjeving, likeverd og solidaritet tyder. Er dette universelle verdiar?

Læreplan

Grunnleggende ferdigheter

Muntlige ferdigheter
Digitale ferdigheter

Tverrfaglige tema

Folkehelse og livsmestring

Læreplan i samfunnskunnskap for voksne innvandrere etter integreringsloven

samtale om sentrale verdier som det norske skole- og utdanningssystemet bygger på, og hva som forventes av foreldre i samarbeidet mellom skole og hjem
gi eksempler på barn, unge og voksnes rettigheter, plikter og muligheter i det norske utdanningssystemet, og hvordan utdanning kan finansieres

Kjerneelement

Demokratiforståelse og deltakelse
Individ og fellesskap

Læringsaktivitet

Muntlig aktivitet

የመጀመሪያ ደረጃ መለስተኛ ትምህርት ቤት

Klasserom sett ovenfra med elever ved hver sin pult. Foto.
AdobeStock

በኖርዌይ፡ ስለ ኣንደኛ እና መለስተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የተመለከተ፣

  • በመላው ኖርዌይ የሚኖሩ ልጆች፡ የ13 ዓመት ትምህርት የማግኘት መብት አላቸው።
  • የኣንደኛ እና መለስተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት፡ ከማንኛውም ክፍያ ነፃ ነው።
  • ልጆች ስድስት ዓመት በሞላቸው ግዜ፡ በነሐሴ ወር ትምህርት ይጀምራሉ።
  • ኣንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት፡ የመጀመርያው ከ 1ኛ እስከ 7ኛ ክፍል ሲሆን፣ መለስተኛ ሁለተና ደረጃ ትምህርት ደግሞ ከ 8ኛ እስከ 10ኛ ክፍል ነው።
  • በመጀመሪያው የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት፡ ልጆች የቃል ወይም የጽሑፍ ፈተና ይሰጣቸዋል፣ ነገር ግን ውጤት አይሰጣቸውም።
  • በመለስተኛ ደረጃ ለሚገኙ ተማሪዎቹ ግን ውጤት ይሰጣቸዋል። የሚሰጣቸው ውጤት ደግሞ ከ1 እስከ 6 ሲሆን፡ 6 ከፍተኛውን ነጥብ ደረጃ ነው።
  • መለስተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የሚገኙ ተማሪዎች፡ የሥነ ስርዓት እና የሥነ-ምግባር ውጤት ይሰጣቸዋል። የሚሰጡ የነጥብ ደረጃዎች ሦስት ደረጃ ያካተቱ ሲሆን፡ እነርሱም፣ ጥሩ፡ መካከለኛ እና ዝቅተኛ ናቸው።
  • ሁሉም የአንደኛና እና መለስተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች፡ ከበጋ ዕረፍት በኋላ፡ ወደሚቀጥለው ክፍል ይዛወራሉ። ማንኛውም ተማሪ በነበረበት ይክፍል ደረጃ ተመልሶ ወይም ደግሞ ኣይማርም።
  • ተማሪዎች የትምህርት ቤት የደንብ ልብስ አይለብሱም።
  • በኖርዌይ፡ በቤት ይሁን በትምህርት ቤት፡ አካላዊ ቅጣት መስጠት የተከለከለ ነው።
  • አንዳንድ ትምህርት፡ ከትምህርት ቤት ውጭ ይካሔዳል። ለምሳሌ፣ የእግር ጉዞ፡ የትምህርት ቤት ካምፕ፡ የመዋኛ ትምህርቶችን እና የሙዚየሞችን ጉብኝት።
  • በኖርዌይ፡ አብዛኛዎቹ ልጆች በመንግስት ትምህርት ቤቶች ይማራሉ፡ ከአምስት በመቶ በታች የሚሆኑት ወደ የግል ትምህርት ቤቶች ይሄዳሉ። ወላጆች፡ ለዚህ የተጠቃሚ ክፍያ ይከፍላሉ።
  • በአንደኛና መለስተኛ ደረጃ ትምህርት የሚሰጡት ትምህርቶች፡ ሂሳብ፡ የኖርዋይ ቋንቋ፡ እንግሊዝኛ፡ የውጭ ኣገር ቋንቋዎች፡ ሳይንስ፡ ማህበራዊ ጥናቶች፡ አካላዊ እንቅስቃሴ፡ የክርስትና እውቀት፡ ሃይማኖት፡ የሕይወት ፍልስፍናዎች እና ሥነ ምግባር (KRLE)፣ ሥነ ጥበብ እና የእጅ ሥራዎች፡ ሙዚቃ፡ ምግብና ጤናን እንዲሁም ተማሪው ከዚህ ተጨማሪ የመረጠው የትምህርት ዓይነትን ያጠቃልላል።
AdobeStock

የአንደኛ እና መለስተኛ ደረጃ ት / ቤቶች፡ በተመሳሳይ መልክ፡ በመላ ሀገሪቱ ስለ ተደራጁ፡ ሁሉም ተማሪዎች በአንድ ሥርዓተ ትምህርት መሠረት ይማራሉ። በኖርወይ ፓርላማ (ስቶርቲንግ) ውስጥ ያሉ ፖለቲከኞች እነዚህን ሥርዓተ ትምህርቶች ይጸድቃሉ። በዚህ መንገድ ፣ ተማሪዎቹ በሚኖሩበት በማንኛውም ኣስተዳደር ፡ ተመሳሳይ ትምህርትን ያገኛሉ።

ለመዋዕለ ሕጻናት ት/ቤቶች፣ የኖርዌይ ትምህርት ቤቶች ኣንቀጽ፡ በክርስትና: ሰብአዊ ቅርስ፡ ወግ፡ እንደ ሰብአዊ ክብር እና ተፈጥሮ ማክበር ባሉ መሰረታዊ እሴቶች ላይ መገንባት እንዳለባቸው ይገልጻል። እንዲሁም፡ በአዕምሯዊ ነፃነት ፣ በጎ አድራጎት፣ ይቅርታ፣ እኩልነት እና አብሮነት ላይ ይገነባሉ።

በኖርዌይ በሚገኙ ትምህርት ቤቶች ያሉ ተማሪዎች ብዙ ግዜ፡ በቡድን ይሠራሉ ፣ እንዲሁም በፕሮጀክቶች ውስጥ ይሳተፋሉ። ስለዚህ ልጆች ከሌሎች ጋር አብረው መስራት እና ለሌሎች አሳቢነትን ይማራሉ።

በኖርዌይ የኣንደኛና መለሰተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ውስጥ ያሉ ሁሉም ልጆች የትምህርት እኩል መብት አላቸው። ተጨማሪ እርዳታ የሚፈልጉ ተማሪዎች እርዳታ ይቀበላሉ። ተማሪዎች በሚኖሩበት፣ በቤተሰባቸው ዳራ ወይም በጾታ ምክንያት በተለየ መንገድ መታየት የለባቸውም። በኖርዌይ ጥቂት ልዩ ትምህርት ቤቶች አሉ። አብዛኛዎቹ ልጆች በሚኖሩበት ትምህርት ቤትውስጥ የሚፈልጉትን እርዳታ ያገኛሉ።

ኣብራችሁ ተወያዩ

  • ኖርዌይ ውስጥ ያለው የትምህርት ሥርዓት ከዚህ በፊት ከምታውቁት የትምህርት ቤት ሥርዓት ጋር ተመሳሳይ / የሚለየው እንዴት ነው?
  • በትምህርት ቤቱ መሰረታዊ እሴቶች ስለ ተቀመጡ ስነምግባራዊ ክብሮች ምን ያስባሉ?
  • በትምህርት ቤት ውስጥ ያሉትን ደረጃዎች ይወያዩ።
  • በትምህርት ቤት የደንብ ልብስ አጠቃቀም ላይ ተወያዩ።
Seks barn sitter i klasserom bak skrivebord. Alle rekker ei hånd opp i lufta. Foto.
Tre gutter sitter bak hvert sitt skrivebord i et klasserom. De har på seg skoleuniform. En av dem smiler mot kamera. Foto.
AdobeStock

ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ

ልጆች ትምህርት የሚጀምሩት መቼ ነው?

ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ

በኖርዌይ፡ ወደ የግል ትምህርት ቤት የሚሄዱት ልጆች፡ ከመቶ ምን ያህል ነው?

ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ

ተማሪዎች በመለስተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ውስጥ ስነ ምግባርና እና ስነ ስርዓት ውጤት ይሰጣቸዋል። ስንት የውጤት ደረጃዎች ሊያገኙ ይችላሉ?

ትክክል ወይም ስህተት የሆነውን ይምረጡ

መግለጫዎቹን ያንብቡ:: ትክክል የትኛው ነው? ስህተት የትኛው ነው?

የአንደኛ ደረጃ እና መለስተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት መማር፡ ግዴታ እና ከማንናውም ክፍያ ነፃ ነው።
የአንደኛ ደረጃ እና የመለስተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት፡ ለ 13 ዓመታት ይወስዳል።
የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ከ 1ኛ ክፍል እስከ 6ኛ ክፍል ነው።
በመለስተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ያሉ ተማሪዎች ውጤት ይሰጣቸዋል። የክፍል ደረጃው 1-6 ነው ፣ ከፍተኛው የውጤት ደረጃ 6 ነው።
በኖርዌይ፡ በትምህርት ቤትም ሆነ በቤት ውስጥ፡ አካላዊ ቅጣት የተከለከለ ነው።

ትክክል ወይም ስህተት የሆነውን ይምረጡ

መግለጫዎቹን ያንብቡ:: ትክክል የትኛው ነው? ስህተት የትኛው ነው?

በየትኛው የኖርዌይ ኣስተዳደር ቦታ ቢኖሩም፡ ልጆች ተመሳሳይ ትምህርት ያገኛሉ።
በኖርዌይ በሚገኙ ትምህርት ቤቶች ያሉ ተማሪዎች እምብዛም በቡድንም ሆነ በፕሮጀክቶች ላይ አይሰሩም።
በኖርዌይ በአንደኛ እና በመለስተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የሚገኙ ልጆች፡ የትምህርት መብት አላቸው።
ብሔራዊ የትምህርት ሥርዓተ፡ በስቶርቲንግ ተቀባይነት አግኝቷል።
በአንደኛ እና መለስተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የሚገኙ ተማሪዎች፡ በሚኖሩበት ኣከባቢ፡ በቤተሰባቸው የኑሮ ሁኔታ እንዲሁም በጾታ፡ በማስመልከት በልዩነት መታየት የለባቸውም።