በኖርዌይ ያሉ አናሳ እና ብዙሃን
በኖርዌይ ያሉ አናሳ እና ብዙሃን
ከጥንት ጀምረው፡ ሰዎች ከቦታ ቦታ ተጓግዟል። ለምሳሌ፡ ከ 1820 እስከ 1930 ባለው ጊዜ ብቻ፡ 30 ሚሊዮን የሚሆኑ አውሮፓውያን ወደ አሜሪካ ተሰደዋል። ከኖርዌይ ብቻ፡ ከ 800,000 በላይ ሰዎች ተሰደዋል።
በኖርዌይ የሚኖረው አብዛኛው ሰው የኖርዌይ ተወላጅ ነው። ባለፉት 60 አመታት ኖርዌይ ብዙ ስደተኞችን አስተናግዳለች። አንዳንዶች ጥገኝነት ፈልገው የመጡ ሲሆን ሌሎች ደግሞ ሥራ ፍለጋ የመጡ ናቸው። እነዚህ፡ ከአውሮፓ እንዲሁም ከተለያዩ አገራት የመጡ ናቸው።
በ2024 መጀመሪያ ላይ ኖርዌይ ውስጥ 5.5 ሚሊዮን ሰዎች ይኖራሉ። ከእነዚህ ውስጥ ከአንድ ሚሊዮን የሚበልጡ በውጭ አገር የተወለዱ ወይም በውጭ የተወለዱ ወላጆች አሏቸው። ይህ ከኖርዌይ የሕዝብ ብዛት በግምት ሃያ በመቶ ይደርሳል። በኖርዌይ ከሚገኙ ስደተኞች ግማሽ ያህሉ የኖርዌይ ዜግነት አላቸው። ትልቅ ቁጥር ያላቸው ስደተኞች (የውጭ ኣገር ዜጎች) የሚመጡት ከፖላንድ፣ ሊትዋኒያ፣ ዩክሬን፣ ስዊድን፣ ሶርያ ነው። በኖርዌይ ባሉ ከተሞች (ኮሙነዎች) ሁሉ ስደተኞች ይኖራሉ። ይሁን እንጂ ስደተኞች ከገጠር ይልቅ በብዛት በከተሞች ውስጥ መኖር ይመርጣሉ።
ኣናሳ ብሔሮች
በአገሪቱ ውስጥ ብዙ ክፍለ ዘመናትን ያስቆጠሩ ከአገሪቱ ጋር ግንኙነት ያላቸው የተለያዩ ብሔሮች ይኖራሉ፡፡ እነዚህን ቡድኖች አናሳ ብሔሮች ይባላሉ፡፡
- ሳሚ
- ኣይሁዶች
- ክቬነር
- ስኩግፊነር
- ሩመር
- ሩማኒ/ታተረ
ምንጭ፣ regjeringen.no
ኖርዌይ በ1999 የአናሳ ብሔረሰቦች መብት ስምምነትን አፅድቃለች። ይህ ስምምነት ማዕከላዊው መንግሥት አናሳ ብሔረሰቦች የሆኑ ሰዎች ሃይማኖትን፣ ቋንቋን፣ ወጎችን እና ባህላዊ ቅርሶችን ጨምሮ ባህላቸውን እንዲጠብቁ እና እንዲያሳድጉ የማስቻል ግዴታ እንዳለበት ይደነግጋል።
ውህደት
የኖርዌይ የፖለቲካ አላማ ብዙሃኑ እና አናሳዎች በደንብ አብረው የሚኖሩበት እና ሁላችንም የምንኖርበት ሀገር የባለቤትነት ስሜት የሚሰማቸው እና የመተሳሰብ ስሜት የሚሰማቸው ማህበረሰብ መሆን ነው። የውህደት ፖሊሲ ዋናው ግብ ስደተኞች እና ልጆቻቸውም መቻል ነው። ሀብታቸውን ተጠቅመው ከብዙሀኑ ህዝብ ጋር በመጣመር ለህብረተሰቡ አስተዋፅዖ ያደርጋሉ። ይህንን ለማረጋገጥ አንደኛው ቁልፍ በኖርዌይ ውስጥ የሚኖር ማንኛውም ሰው ጥሩ የኖርዌይ ቋንቋ (ኖሽክ) የመናገር ችሎታ መያዙ ነው።
ኣብራችሁ ተወያዩ
- የመጣችሁበት አገር፡ የሚመጡ ስደተኞች ወይስ ከአገር የሚወጡ ስደተኞ ይበዛሉ?
- ሰዎች ለምን ከትውልድ አገራቸው ይወጣሉ?
- ብዙ ስደተኞች ከገጠር ክፍል ይልቅ በከተማዎች ውስጥ መኖር የሚመርጡት ለምን ይመስላችኋል?
- ስደተኞች ብቻ የሚበዙባቸው አንዳንድ ክፍለ ከተማዎች አሉ። ይህ የሆነበት ምክንያት ምን ይመስላችኋል? ይህ ጥሩ (አዎንታዊ) ነገር ይመስላችኋል? መልሳችሁ አዎን ከሆነ ለምን? አይ ከሆነ ለምን?
- ስደተኞች የሚሰደዱበትን አገር ቋንቋ መማር አለባቸውን? መልሳችሁ አዎን ከሆነ ለምን? አይ ከሆነ ለምን?
- ስደተኞች መኖር ያለባቸው እንደተሰደዱበት አገር ሰዎች መሆን አለበት? አዎ ከሆነ ለምን? አይ ከሆነስ ለምን?
- በትውልድ አገራችሁ አናሳ የሆኑ ብሔሮች አሉን?
- ማዕከላዊው መንግሥት አናሳ ለሆኑ ብሔሮችን ባሕል ከመጠበቅ አንጻር ስላለበት ኃላፊነት ተነጋገሩ፡፡
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ
ከኖርዌይ ውጪ የተወለዱ አሊያም ከኖርዌይ ውጪ የተወለዱ ወላጆች ያሏቸው ምን ያህሉ የኖርዌይ ሕዝቦች ናቸው?
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ
አብዛኛዎቹ ስደተኞች የት አካባቢ ነው የሚኖሩት?
አረፍተ ነገሩን አሟሉ፡፡
ስደተኞች ያላቸውን ምጣኔ ሃብት ለመጠቀም ………. አስፈላጊ ነው፡፡
ትክክል ወይም ስህተት የሆነውን ይምረጡ
መግለጫዎቹን ያንብቡ። ትክክል የትኛው ነው? ስህተት የትኛው ነው?
ትክክል ወይም ስህተት የሆነውን ይምረጡ
መግለጫዎቹን ያንብቡ። ትክክል የትኛው ነው? ስህተት የትኛው ነው?