መኖርያ ቤቶች
ፊልሙን ይመልከቱ
መኖርያ ቤቶች
መኖርያ ቤቶች
በኖርዌይ፡ በ 2,7 እና 3 ሚሊዮን መካከል የሚሆኑ የመኖሪያ ቤቶች አሉ። ከእነዚህ ውስጥ ግማሽ ያህሉ ቪላ ቤቶች ናቸው። እንደ ኦስሎ ባሉ በትልልቅ ከተሞች ውስጥ ብዙዎቹ ቤቶች የአፓርትመንት ሕንፃዎች ናቸው። በትናንሽ ከተሞች፡ አብዛኛዎቹ ቤቶች ቪላ ቤቶች ናቸው። ወደ 82 ከመቶ ያሚያህሉ ቤተሰቦች የራሳቸው የሆነ መኖሪያ ቤት አላቸው፡ የቀሩት 18 ከሞቶ የሚያህሉ ግን ተከራይተው ይኖራሉ።
- በባለቤት የተያዘ መኖሪያ፡ የቤቱ ባለቤት ኣንተ ራስህ ነህ። ማንንም መጠየቅ ሳያስፈልግህ፡ ቤትህ ለማደስና ለማከራየት ትችላለህ። ከቤትህ ጋር በተያያዘ ሁሉንም ወጪዎች (የኣስተዳደር ግብር፡ የቤት መድን እና የጥገና ወጪዎችን) ራስህ ትከፍላለህ። ቤቱን ለምግዛት የሚያስፈልገውን ሁሉ በሙሉ ራስህ ትሸፍነዋለህ።
- የመኖሪያ ቤት ህብረት ስራ ማህበር፡ በቤቶች ህብረት ስራ ማህበር ውስጥ የራስህ የሆነ ድርሻ አለህ። ቤቱን የመጠቀም ልዩ መብት አለህ። የቤቶች ህብረት ስራ ማህበራት ሕጎችን እና ደንቦችን ማክበር አለብህ። አፓርትመንቱን ስትገዛ፡ ኣስቀድመህ መያጃ ገንዘብ ማስቀመጥ፡ ይህም በራስህ የገንዘብ ትሸፍነዋለህ። በየወሩ የቤት ኪራይ ትከፍላህ። ኪራዩ የመኖሪያ ቤት ህብረት ስራ ማህበር የጋራ ዕዳ፣ የኣስተዳደር ግብርን እና የቤት መድንን ድርሻህን ይሸፍናል።
የገንዘብ ድጋፍ
ቤት መግዛት ብዙ ገንዘብ ያስፈልጋል፣ ስለሆነም ብዙ ሰዎች ቤት ለመግዛት ከባንክ ይበደራሉ። ብድሩን ለመሸፈን፡ ለብዙ ዓመታት በየወሩ የተወሰነውን መክፈል የተለመደ ነው። ቤቱን ለመግዛት የሚያስፈልገውን ገንዘብ በሙሉ ከባንክ መበደር አትችልም። የራሳችን የተወሰነ ገንዘብ ሊኖረን ይገባል። ይህ ‘የራሱ ገንዘብ’ ተብሎ ይጠራል። በደንቡ መሰረት፡ ከጠቅላላው የግዢ መጠን፡ 15 በመቶውን ካከማቸነው መሆን ኣለበት። ከዚያም ቀሪውን 85 በመቶ የግዢ ዋጋ፡ ከባንክ መበደር ይቻላል። ይሁን እንጂ፡ ይህን ከባንክ ብድር ለማግኘት፡ ሰዎች መደበኛ ገቢ ወይም ሌላ የገንዘብ ዋስትና ሊኖራቸው ይገባል። ባንኩ፡ ተበዳሪዎቹ ክፍያዎችን እና ወለድን መክፈል እንደሚችሉ ማረጋገጥ አለበት።
ኣብራችሁ ተወያዩ
- ቤት በመግዛት ወይም በመከራየት ስላለው ጥቅምና ጉዳት ይናገሩ።
- ስለ በባለቤት የተያዘ መኖሪያ እና ፡ የመኖሪያ ቤት ህብረት ስራ ማህበር፡ ቤቶች ልዩነት ተወያዩ።
- ከባንክ ገንዘብ ስለመበደር ምን ታስባላችሁ? ምን ማካተት አለበት ብላችሁ ታስባላችሁ?
- ከ finn.no ወይንም ከሌላ ኢንተርነት፡ በመኖሪያ አካባቢያችሁ የሚገኙ ለሽያጭ የቀረቡ ንብረቶችን ማግኘት ትችላላችሁ። ምን አይነት ንብረት ተመለከታችሁ? ምን ያክል ያወጣሉ?
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ
በኖርዌይ ውስጥ ስንት ቤቶች አሉ?
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ
የትኛው አይነት ቤተ ነው በ………..ሊገለጽ የሚችለው፡፡
- ቤቱን ለመጠቀም የተለየ መብት ያለው ፡፡
- በሕግና በደረጃዎች
- አፓርትመንት (የጋራ መኖሪያ) ለመግዛት ውዝፉን መክፈል
- በየወሩ ኪራይ መክፈል
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ
ቤት ለመግዛት ስንፈልግ አስቀድመን የግዢውን ዋጋ ምን ያህል መጠን መቆጠብ ይኖርብናል?
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ
ባለቤቱ የሚኖርበት ቤት ምን ይመስላል?
ትክክል ወይም ስህተት የሆነውን ይምረጡ፡፡
መግለጫዎቹን ያንብቡ:: ትክክል የትኛው ነው? ስህተት የትኛው ነው ?