የአዕምሮ ጤንነት
የአዕምሮ ጤንነት
ዮሃንስ፣ አሁን ድረስ ሆዴን እያመመኝ ነው። በዚህም ምክንያት ጥሩ እንቅልፍ አልተኛሁም፡፡
ዶክተር፡ አስፈላጊዎቹን ምርመራዎች በሙሉ አድርገናል እናም በሆድህ ውስጥ ምንም አይነት ችግር አልተገኘም ፡፡
ዮሃንስ፣ ኣልገባኝም።
ዶክተር፡ ኣልህ? እስቲ ሌላ የሚሰማህን ነገር ንገረኝ ? አሁንም ሃዘን እና ብቸኝነት ይሰማሃል?
ዮሃንስ፣ ይህን ጥያቄ ለምን ጠየከኝ? ያመመኝ ሆዴ ነው፡ ችግሬ እሱ ነው?
- ዶክተር ለምን ዮሃንስ ሀዘን እና ብቸኝነት እየተሰማው እንደሆነ ጠየቀው?
- ይህ ዮሃንስን የሚያናድደው ለምንድን ነው?
- በኣዕምሮ እና በአካላዊ ጤንነት መካከል ስላለው ግንኙነት ተወያዩ።
- በአገርዎ እና በኖርዌይ ስላሉት የአዕምሮ ጤና ችግሮች ሰዎች ምን ያስባሉ?
- ዮሃንስን ማን ሊረዳው ይችላል?
ከጥቂት ሳምንታት በኋላ፡
ዶክተር፡ እንደምን አለህ ጆን! በድጋሚ ስለተገናኘን ደስ ብሎኛል። ምን ልርዳህ?
ዮሃንስ፣ ባለፈው እዚህ በነበርኩበት ጊዜ ስለ ተነጋገርነው ነገር እያሰብኩ ነበር። አንዳንድ እርዳታ የሚያስፈልገኝ ይመስለኛል። ህይወት ፈታኝ እና አስቸጋሪ እንደሆነ ይሰማኛል። ደስተኛ አይመስለኝም፡ እና ሁልጊዜም ይደክመኛል። አንዳንድ ጊዜ ያለ ምክንያት እቆጣለሁ። እንዲሁም ጥሩ እንቅልፍ የለኝም እና በአገሬ ስላጋጠሙኝ ነገሮች ቅዠት አለኝ።
ዶክተር፣ ወደ ስነልቦና ባለሞያ ብጽፍልህ እንደሚሻል አስባለሁ።
ዮሃንስ፣ የስነልቦና ባሙያ ነው ያልከኝ? እኔ እኮ ጭንቅላቴ ላይ ምንም ችግር የለብኝም።
ዶክተር፣ አይ፡ አንዳንድ ጊዜ ስለችግርህ ከባለሙያ ጋር መነጋገር ሊረዳህ ይችላል። የሥነ ልቦና ባለሙያዎች የምስጢርነት ግዴታ እንዳለባቸው እና ከኣንተ ጋር የተናገሩትን ማንኛውንም ነገር ለማንም ሊነግሩ እንደምይችሉ ኣስታውስ። አንድ ጊዜ እሱን ለማየት ሄደህ ከጠቀመህ ሞክረው።
ዮሃንስ፣ ደህና፡ ኣሁን ካለሁበት የባሰ ሊሆን ኣይችልም። ስለዚህ፡ እሞክረዋለሁ።
- ስለ ዶክተሩ አስተያየት ምን ታስባለህ?
- ስለ ዮሃንስ ምላሽ ምን ታስባለህ?
ብዙ ሰዎች በህይወት ዘመናቸው በተለያዩ የአእምሮ ጤና ችግሮች ይሰቃያሉ። ሰዎች የኣዕምሮ ጤና ችግር የሚፈጥሩባቸው ብዙ ምክንያቶች አሉ።ኣንዳንድ ግዜ፡ ከአስቸጋሪ የህይወት ሁኔታዎች፣ እንደ የቤተሰብ ችግሮች ወይም አስቸጋሪ የስራ ሁኔታ ሊሆን ይችላል። አንዳንድ ሰዎች ከችግር፣ ከሞት ወይም ከአደጋ በኋላ ወይም ከጦርነት በኋላ የኣዕምሮ ችግር ያጋጥማቸዋል። አንዳንድ ሰዎች ደግሞ የአዕምሮ መታወክን በዘር የሚተላለፍ ቅድመ-ዝንባሌ ሊኖራቸው ይችላል፣ ስለዚህ ጭንቀት እንደ መነሻ ሆኖ ሊያገለግል ይችላል።
በምንቸገርበት ጊዜ፡ ከአንድ ሰው ጋር መነጋገር ሊያስፈልገን ይችላል። አንዳንድ ጊዜ ከቤተሰብ ወይም ከጓደኞች ጋር መነጋገር በቂ ነው። በሌላ ጊዜ ደግሞ የባለሙያ እርዳታ ልንፈልግ እንችላለን። የሥነ ልቦና ባለሙያ ወይም ሌላ ባለሙያ ለችግሮቻችን መፍትሔ ለማግኘት ብዙ ጊዜ ሊረዱን ይችላሉ። ኣስፈላጊ ከሆነ፡ መደበኛ ቋሚ ሓኪማችን ወደ የሥነ ልቦና ባለሙያ ሊልኩን ይችላሉ።
የማህበረሰብ እይታ የአዕምሮ ጤና ተለውጧል። ዛሬ፣ አብዛኛው የኖርዌይ ህዝብ ለአዕምሮ ህመም ክፍት ኣመለካከትና ግንዛቤ አለው። ብዙ ሰዎች የአዕምሮ ህሙማን የአካል ችግር ካለባቸው ሰዎች ጋር በተመሳሳይ መልኩ፡ በጤና አገልግሎቱ ህክምና እና እርዳታ ሊደረግላቸው ይገባል ብለው ያምናሉ። ከአዕምሮ ሕመም መዳን እንደሚቻልም ያምናሉ።
ኣብራችሁ ተወያዩ
- በተለያየ ጊዜ እና በተለያዩ ማሕበረሰቦች ዘንድ የአዕምሮ ሕመምን በተመለከተ ያሉትን አመለካከቶች ላይ ተመካከሩ፡፡
- መልካም የአዕምሮ ጤንነት እንዲኖረን ምን ማድረግ እንችላለን?
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ
በኖርዌይ ውስጥ ብዙ ሰዎች ስለ አእምሮ ሕመም ያላቸው አሳብ ምንድነው?
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ
የአዕምሮ ችግር የሚገጥመው ማነው?
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ
በጤናችሁ ዙሪያ አንድን ሰው ማናገር ብትፈልጉ የግል ሃኪማችሁ ምን ሊያደርግላችሁ ይችላል?
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ
ደካማ የሆነ የአእምሮ ጤንነት እንዴት ሊጎዳን ይችላል?
ትክክል ወይም ስህተት ይምረጡ
መግለጫዎቹን ያንብቡ:: ትክክል የትኛው ነው? ስህተት የትኛው ነው