በቤት እና በትምህርት ቤት መካከል ትብብር
በቤት እና በትምህርት ቤት መካከል ትብብር
ሴት ልጅ - ይህ ደብዳቤ ከአስተማሪዬ የተላከ ነው፣ እንኩ። በሚቀጥለው ሳምንት፡ ስለ እድገትና ኣስተዳደግ ያለውን ውይይት መሄድ አለብዎት።
ኣያት - መምህሩ ለምን ደብዳቤውን ጻፈ? የሆነ ስህተት ሰርተሻል?
ሴት ልጅ - አይ ፣ ከአስተማሪው ለሁሉም ተማሪዎች የተሰጠ ደብዳቤ ነው።
ኣያት - እርግጠኛ ነሽ ምንም ስህተት አልሰራሽም? እኔ ትምህርት ቤት ስማር፡ ወላጆች ኣስተማሪዎችን የሚያናግሩት ተማሪ ስህተት ሲሰሩ ብቻ ነበር።
እናት - በኣሁኑ ግዜ እንደሱ።እኔም ስለ ትምህርት ከኣስተማሪው ጋር መነጋገር እፈልጋለሁ። እንዲሁም ስለ የቤት ሥራዎች ኣንዳንድ ጥያቄዎች አሉኝ።
ወላጆች ለልጆቻቸው ዋና ኃላፊነት አለባቸው። ሆኖም ፣ ወላጆች ከመዋዕለ ሕጻናት እና ከትምህርት ቤት ጋር በአስተዳደጋቸው እና በትምህርታቸው ቢተባበሩ ለልጆቹ እና ለወጣቶች ጥሩ ነው።
ወላጆች እና ትምህርት ቤቱ ከልጅዎ ጋር በመሆን፡ ተማሪው የሚፈልገውን/የምትፈልገውን ትምህርት እንደሚማር/እንደምትማር ማረጋገጥ አለባቸው። ተማሪው፡ ወላጆች እና አስተማሪው ስለ ልጁ የትምህርት እድገት፡ እና በትምህርት ቤት እንዴት እንደሚሠራ ፡ ቢያንስ በዓመት ሁለት ጊዜ በጋራ መነጋገር አለባቸው።
ወላጆች ከትምህርት ቤቱ የተጻፉትን የጽሑፍ መረጃዎች ሁሉ አንብበው እንዲያውቁት አስፈላጊ ነው። ማንኛውም ጥያቄ ካላቸው፡ ወላጆች መምህሩን ወይም ሌላውን የት / ቤት ሠራተኛ ማነጋገር ይችላሉ።
ኣብራችሁ ተወያዩ
- ትምህርት ቤቱ ለሁሉም ጥሩ ቦታ መሆን አለበት ማለት ምን ማለት ነው?
- የጋራ ውሳኔ እና የጋራ ኃላፊነት ማለት ምን ማለት ነው?
መተባበሩ፡ ኣብዛኛውን ጊዜ፡ እንደፈለግነው አይሰራም። አስፈላጊ እና ትክክለኛ ስለሆኑ ነገሮች፡ ወላጆች እና ትምህርት ቤቱ: የተለያዩ አስተያየቶች ሊኖሯቸው ይችላል። ሌላው ችግር ትምህርት ቤቱ እና ወላጆች፡ በየበኩላቸው የሚጠብቋቸው ነገሮች የተለያዩ ሊሆኑ ይችላሉ። አንዳንድ መምህራን የሚከተሉትን ሁኔታዎች ሪፖርት ያቀርባሉ፣
- ወላጆች በወላጆች ስብሰባዎች ወይም የእድገት ንግግሮች ላይ አይገኙም።
- ወላጆች በበጋ ዕረፍት ወቅት ልጆችን ወደ አገራቸው ይወስዳሉ፡ እና ትምህርት በነሐሴ ወር ሲጀምር አይመለሱም። ልጆቹ ከጥቂት ሳምንታት ወይም ወራት በኋላ በትምህርት ቤት ይታያሉ።
- በኖርዌይ የተወለዱ ልጆች ትምህርት ሲጀምሩ ደካማ የኖርዌይ ቋንቋ ችሎታ አላቸው።
- ወላጆች፡ ተማሪዎች ከትምህርት ቤት ውጭ በሚደረግ፣ የማስተማር እንቅስቃሴዎች ውስጥ፡ ለምሳሌ በትምህርት ቤት ካምፕ እንዲሳተፉ አይፈልጉም።
- ተማሪዎች የኣካል እንቅስቃሴ በጂም ወይም መዋኛ ትምህርቶች እንዲሳተፉ አይፈቀዱላቸውም።
- አንዳንድ ወላጆች ለምን እንደዚህ ዓይነት ምርጫ ይወስዳሉ?
- ለልጆቹ የሚያስከትለው መዘዝ ምን ሊሆን ይችላል?
- ለእነዚህ ችግሮች መፍትሔ ሊሆኑ ስለሚችሉ ሃሳቦች ላይ ተነጋገሩ።
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ
በየስንቱ ጊዜ፡ አስተማሪው፣ ተማሪው እና ወላጆቹን ያካተተ፡ ተማሪው ትምህርት ቤቱን ስለመውደድና የልጁ የትምህርት እድገት ይነጋገራሉ?
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ
ከመምህሩ ጋር በሚደረገው ስብሰባ ላይ ምን ይብራራል?
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ
ትብብሩ ሁልጊዜ እንደምንፈልገው አይሰራልንም። ችግሩ ምን ሊሆን ይችላል? ከአንድ በላይ መልስ መምረጥ ይችላሉ።
ትክክል ወይም ስህተት የሆነውን ይምረጡ
መግለጫዎቹን ያንብቡ:: ትክክል የትኛው ነው? ስህተት የትኛው ነው?
ትክክል ወይም ስህተት የሆነውን ይምረጡ
መግለጫዎቹን ያንብቡ:: ትክክል የትኛው ነው? ስህተት የትኛው ነው?