ሃይማኖታዊ እና ሕዝባዊ በዓላት
ሃይማኖታዊ እና ሕዝባዊ በዓላት
አዲስ አመት
የዓመቱ የመጀመሪያ ቀን ጥር 1 ነው። የአዲስ ዓመት ቀን ብለን እንጠራዋለን። ሱቆች እና ትምህርት ቤቶች ዝግ ናቸው። አብዛኛው ሰው የእረፍት ቀን ኣለው።
የሳሚ ብሔራዊ ቀን
የካቲት 6፣ በፊንላንድ፣ በኖርዌይ፣ በሩሲያ እና በስዊድን የሚገኙ ሳሚ፡ የሳሚ ብሔራዊ ቀን ያከብራሉ። ባንዲራ የሚውለበለብበት ቀን ነው፡ ግን የሕዝብ በዓል አይደለም።
የሴቶች ቀን
ዓለም አቀፉ የሴቶች ቀን፡ መጋቢት 6፡ ይከበራል። ዓለም አቀፉ የሴቶች ቀን ለመጀመሪያ ጊዜ የተከበረው በ1915 ዓ.ም ነበር። በ1970ዎቹ ብዙ ሰዎች ለሴቶች እኩልነትና መብት መፋለም ጀመሩ፡ ከዚያም ከ1972 ዓ.ም ጀምሮ በኖርዌይ የዓለም አቀፉ የሴቶች ቀን መከበር ጀመረ። አንዳንድ ሰዎች፡ መጋቢት 8 በጎዳናዎች ላይ ሰልፍ ያደርጋሉ፡ መልእክቶችንም ለተለያዩ አካላት ያስተላልፋሉ። ሆኖም፡ መጋቢት 8 የሕዝብ በዓል አይደለም፡፡
ፋሲካ
የፋሲካ በዓል በየካቲት ወይም መጋቢት ወር ይከበራል። ትክክለኛው የማክበሪያ ቀኑ ከዓመት ዓመት ይለያያል፡፡ የፋሲካ በዓል የክርስቲያኖች በዓል ሲሆን፡ የኢየሱስ ክርስቶስን ሞትና ትንሳኤ በማሰብ የሚከበር በዓል ነው። ኖርዌይ ለሚኖሩ ብዙ ሰዎች፡ የፋሲካ በዓል ሃይማኖታዊ በዓል ሳይሆን፡ ከረጂም የክረምት ወራት በኋላ የሚገኝ፡ ጥቂት እረፍት የሚገኝበት ግዜ እንደሆነ ኣድረገው ይወስዱታል።
ጸሎተ ሐሙስ፣ ስቅለት (አርብ) እና (ትንሳኤ) የፋሲካ እሁድ እንዲሁም የፋሲካ ሰኞ የበዓል ቀናት ናቸው። በእነዚህ ቀናት ሱቆች ዝግ ናቸው፣ አብዛኛው ሰው ሥራ አይገባም። ተማሪዎችም በፋሲካ እረፍት ምክንያት ወደ ትምህርት ቤት አይሄዱም፣ እንዲሁም ብዙ ሰራተኞች ከሕዝባዊ ክብረበዓላት ውጪ፡ ተጨማሪ የበዓል እረፍት ይሰጣቸዋል፡፡
የእርገት እና የጰጤቆስጤ ቀን
የእርገትና የጰጤቆስጤ ቀን ሁለቱም የክርስቲያን ክብረ በዓላት ናቸው። የእርገት ቀን የሚከበረው ከትንሳኤ በዓል በኋላ በ40ኛው ቀን ሲሆን፡ የጰጤቆስጤ ቀን ደግሞ ከእርገት ቀን በኋላ በ10ኛው ቀን ይከበራል። የእርገትና የጰጤቆስጤ ቀኖች ሕዝባዊ በዓላት በመሆናቸው ሱቆች ዝግ ናቸው።
የሰራተኞች ቀን
ዓለም አቀፉ የሰራተኞች ቀን፡ ግንቦት 1 ይከበራል። በዚሁ ቀን፡ ብዙ ሰዎች የሚፈልጉዋቸውን ፓለቲካዊ ጉዳዮች ድጋፋቸውን ለመግለጥ፡ በጎዳናዎች ላይ ሰልፍ ያደርጋሉ። የሰራተኞች ቀን ሕዝባዊ በዓል በመሆኑ ሱቆች ዝግ ናቸው።
የሕገ መንግስት ቀን
የኖርዌይ ብሔራዊ ቀን ግንቦት 17 ነው። ግንቦት 17 ቀን 1814 የኖርዌይ ሕገ መንግሥት የተፈረመበት ቀን ኣስመልክቶ ይከበራል። የሕገ መንግሥት ቀን ከሁሉም በፊት የሕፃናት ቀን ነው። በዚህ ቀን፡ የመዋዕለ ሕፃናት እና የትምህርት ቤት ልጆች፡ ጥሩ ልብስ ለብሰው፡ የኖርዌይን ባንዲራ እያውለበለቡና እየዘፈኑ ሰልፍ ላይ ይሳተፋሉ። በቀለማት ያሸበረቀ የደንብ ልብስ የለበሱ የማርሽ ባንዶች ሰልፉን ይመራሉ። ብዙ ልጆች እንደዚህ ባሉ የማርሽ ባንዶች ውስጥ ይጫወታሉ።
ልጆችም የቻሉትን ያህል ጣፋጭ ከረሜላዎችንና የተጠበሰ ስጋ ሳንድዊቶችን በነጻ መመገብ ይችላሉ። በኖርዌይ ያሉ ልጆች፡ ግንቦት 17 በጉጉት የሚጠብቁት ቀን ነው። የሕዝብ በዓል ስለሆነ ሱቆች በዚህ ቀን ዝግ ይሆናሉ።
የገና በዓል
አብዛኛዎቹ ኖርዌጃውያን በታሕሳስ ወር የገና በዓልን ያከብራሉ፡፡ የገና በዓል የክርስቲያኖች በዓል ሲሆን፡ የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት ቀን የሚከበርበት በዓል ነው። ለብዙ ሰዎች ገና እና የገና በዓል በጣም ኣስፈላጊ ልምድ ናቸው። የገና በዓል ግን በዋነኝነት የቤተሰብ በዓል ነው።
ታህሳስ 24 ቀን የገና ዋዜማ ብለን እንጠራዋለን። በገና ዋዜማ፡ ከኣንድ ቤተሰብ ጋር ተሰብስቦ ባህላዊ የገና እራት መብላት የተለመደ ነው። የተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች የተለያዩ ወጎች አሏቸው። ብዙ ሰዎች መጠበቅ አስፈላጊ እንደሆነ የሚሰማቸው የራሳቸው ወጎች አሏቸው። በገና ዋዜማ፡ እርስ በርስ ስጦታዎችን መለዋወጥ የተለመደ ነው።
የገና ቀን እና የማግስቱ ቀን የህዝብ በዓላት ናቸው። ሱቆች ዝግ ናቸው፣ አብዛኛው ሰዎች በእነዚህ ቀናት አይሰሩም። ተማሪዎች በገና በዓል ምክንያት ከትምህርት ነጻ ናቸው።ብዙ ሰራተኞች፡ ከህዝባዊ በዓላት በተጨማሪ የበዓል እረፍት ቀናት ይወስዳሉ።
የዘመን መለወጫ ዋዜማ
የዓመቱ የመጨረሻ ቀን ታህሳስ 31 ነው። ይህ ቀን የአዲስ ዓመት ዋዜማ ተብሎ ይጠራል። ብዙ ሰዎች ከቤተሰቦቻቸው እና ከጓደኞቻቸው ጋር ያከብሩታል። እኩለ ሌሊት ሲደርስ፡ ርችቶች ይለኮሳሉ በዚህም የሌሊት ሰማይ ያደምቁታል።የአዲስ ዓመት ዋዜማ የህዝብ በዓል አይደለም።
የቀን መቁጠሪያውን የማይከተሉ ወጎች እና የማይረሱ ቀናት፣ የተወለዱበት ቀን፡ ሰርግ፡ ጥምቀት፡ የእምነት ማጽኛ እና የቀብር ።
ኣብራችሁ ተወያዩ
- የትኞቹን የደስታ በዓል ቀናት ታውቋቸው ነበር? እነዚህንስ ቀኖች እንዴት ነበር የምታከብሯቸው?
- ሰዎች የተለያዩ የደስታ በዓላት የሚያከብሩት ለምንድነው?
- የትኛው የደስታ በዓል ቀን ነው ለእናንተ በጣም ኣስፈላጊ የሆነው? በኖርዌይ ሆናችሁ እነዚህን በዓላት ስታከብሩ ምን የተለየ ነገር ገጠማችሁ?
- ከኖርዌጃውያን የደስታ በዓላት ለእናንተ ኣስፈላጊ ይሆናሉ ብላችሁ የምታስቧቸውን ኣሉ ወይ?
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ
የሕዝብ በዓል ያልሆኑት የትኞቹ ቀኖች ናቸው?
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ
የኖርዌይ ብሔራዊ ቀን መቼ ነው?
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ
የአመቱ የመጨረሻ ቀን ምን በመባል ይታወቃል?
ትክክል ወይም ስህተት የሆነውን ይምረጡ
መግለጫዎቹን ያንብቡ። ትክክል የትኛው ነው? ስህተት የትኛው ነው?
ትክክል ወይም ስህተት የሆነውን ይምረጡ
መግለጫዎቹን ያንብቡ። ትክክል የትኛው ነው? ስህተት የትኛው ነው?
ትክክለኛውን ምስል ይምረጡ፡፡
በኖርዌይ የቀዩ ደብዳቤ (የስጦታ መለዋወጫ ) ቀን፡ ተብሎ የሚጠራው በዓል የትኛው ነው?