የሠራተኞች ማህበር።
የሠራተኞች ማህበር።
በኖርዌይ ውስጥ ያሉ ሰራተኞችም ሆኑ ቀጣሪዎች መብቶቻቸውን ለመጠበቅ እና አስፈላጊ በሆኑ ስምምነቶች ላይ የመተባበር እድላቸውን ለማስጠበቅ የሚፈልጉ የየራሳቸው ድርጅቶች አሏቸው። በግምት፡ 50% የሚሆኑ በኖርዌይ ከሚገኙ ሠራተኞች፡ የሠራተኛ ማህበር አባላት ናቸው።
የሠራተኛ ማኅበር ዋናው አስፈላጊ ሥራ፡ ከአሠሪዎች ጋር ስለ ደመወዝ እና ስለ ሌሎች መብቶች መደራደር ነው። እነዚህ መብቶች፡ የሥራ ሰዓቶች፡ የእረፍት ግዜ እና በሥራ ላይ ሥልጠና የማግኘት መብት ሊሆኑ ይችላሉ። ድርድሮች ሲጠናቀቁ፡ አሠሪዎች እና ሠራተኞች፡ የማክበር ግዴታ ያለባቸው ስምምነቶች ይፃፋሉ። ተዋዋይ ወገኖች ስምምነት ላይ ካልደረሱ፡ ሠራተኞቹ የሥራ ማቆም አድማ የማድረግ መብት አላቸው።
ጥሩ የሥራ ቦታ ሁኔታን ለመፍጠር፣ አሠሪዎች እና ሠራተኞች በተለያዩ ስምምነቶች ኣብረው መሥራት አለባቸው። ስለሆነም፡ የኖርዌይ የሥራ ሕይወት ውስጥ፡ ለጋራ ውሳኔ እና ለድርጅት ዴሞክራሲ በብዙ መንገዶች ያመቻቻል። እያንዳንዱ ሠራተኛ፡ የመደመጥ እና በራሱ የሥራ መስክ በመደራጀት የመሳተፍ መብት አለው። ሠራተኞች በሠራተኛ ማኅበሮቻቸው አማካይነት በውይይቶች ውስጥ ይሳተፋሉ፡ ስለ ድርጅቱም መረጃ ያገኛሉ።
ሁሉም አሠሪዎች፡ በሥራ ቦታ ጤናን፡ ደህንነት እና የአካባቢ እንክብካቤ (HSE) እንዲጠበቅ ግዴታ ኣለባቸው። ይህም ሥራ፡ በሁለቱም የሠራተኞች የደህንነት ተወካይ እና በድርጅቱ ተወካይ መደራጀትና መከታተል አለበት።
ኣብራችሁ ተወያዩ
- በአገርዎ ውስጥ የሠራተኛ ማኅበራት አስፈላጊነት ኣላቸው?
- የሥራ ማቆም አድማ መብትና ሊሠራበት በሚችልበት ሁኔታ ላይ ይወያዩ
- ብዙ ሰዎች ወደ ሠራተኛ ማኅበር የሚገቡበት ምክንያት ምን ይመስልዎታል?
- ከሠራተኞች መካከል ግማሽ ያህሉ ወደ ሠራተኛ ማኅበር ላለመቀላቀል የሚወስኑት ለምን ይመስልዎታል?
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ
በኖርዌይ ካሉ ሰራተኞች፡ ምን ያህል መቶኛ የሰራተኛ ማህበር ኣባላት ናቸው?
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ
የሠራተኛ ማህበር በጣም አስፈላጊው ሥራ ምንድነው?
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ
አሠሪዎች እና ሠራተኞች ስምምነት ላይ ካልደረሱ ሠራተኞች ምን ማድረግ ይችላሉ?
ትክክል ወይም ስህተት የሆነውን ይምረጡ
መግለጫዎቹን ያንብቡ:: ትክክል የትኛው ነው? ስህተት የትኛው ነው?
ትክክል ወይም ስህተት የሆነውን ይምረጡ
መግለጫዎቹን ያንብቡ:: ትክክል የትኛው ነው? ስህተት የትኛው ነው?