ደመወዝ እና ዓመታዊ ግብር
ደመወዝ እና ዓመታዊ ግብር
ደመወዝ
በኖርዌይ ስለ ደመወዝ/ክፍያ ሲወራ፡ ብዙውን ጊዜ የዓመት ደመወዝ ወይም የሰዓት ደመወዝ ያመለክታል። በኖርዌይ በአማካይ የዓመት ደመወዝ ፡ የሥራ ግብር ከመቀነሱ በፊት፡670,000 ክሮነር (በ 2023)ነው። ሴቶች በአማካይ፡ ከወንዶች ያነሰ ገቢ ያገኛሉ። ከብዙ ምክንያቶች፡ ኣንዱ ሴቶች ብዙውን ግዜ፡ በትርፍ ሰዓት የሚሰሩ በመሆናቸው እና ዝቅተኛ ደመወዝ በሚከፍሉ ሥራዎችን ስለሚመርጡ ነው።
የደመወዝ ድርድር ኣስፈላጊ ነው። ስለሆነም፡ ድርድሩ በቀጥታ በአሠሪ እና በሠራተኛ መካከል ወይም በአሠሪው ተወካዮች እና በሠራተኞች ተወካዮች መካከል ይካሔዳል። የሠራተኛ ማህበር አባላት ለሆኑት፡ ኣብዛኛውን ጊዜ፡ የሠራተኛ ማህበራቸው በአባላቱ ስም ይደራደራል።
ደመወዝ፡ በወር በአንድ የተወሰነ ቀን፡ በሠራተኛው ባንክ ሂሳብ ይገባል። ስለ ደመወዝ መጠን እና የግብር ቅነሳዎች በሚገባ ተዘርዝረው፡ በወረቀት ላይ ይሰፍራሉ፡ ለሠራተኛውም ይሰጣሉ።
ምንጭ - ስታቲስቲክስ ኖርዌይ
ግብር
የኖርዌይ ማህብረተሰብ የተገነባው ሙሉ በሙሉ ነዋሪዎቹ በሚከፍሉት ቀጥተኛ ግብር እና ሌሎች ክፍያዎች ላይ ነው። የማህበራዊ ደህንነት ሥርዓት፡ ከግብር እና በሌሎች ገቢዎች ይደገፋል። በኖርዌይ ውስጥ ያሉ ሁሉም ሠራተኞች ለሚኖሩበት ኣስተዳደር እና ለኖርዌይ መንግስት ግብር ይከፍላሉ። እንዲሁም፡ አሠሪዎች ለመንግስት እና ላሉበት ኣስተዳደር ግብር ይከፍላሉ።
በዓመት ከዝቅተኛ መጠን በላይ የሚያገኝ ሁሉ፡ ግብር መክፈል አለበት። ሁሉ ሰው እኩል የግብር መጠን አይከፍልም። ብዙ ገቢ ያላቸው በገቢያቸው መጠን ከፍ ያለ ግብር ሲከፍሉ፡ ኣነስተኛ ገቢ ያላቸው ደግሞ እንድ ገቢያቸው መጠን ያነሰ ግብር ይከፍላሉ። ይህ ሀሳብ የመጣው፡ ብዙ ገቢ ካላቸው ሰዎች፡ ለጋራ ጥቅም ብዙ ይመልሳሉ ከሚል አስተሳሰብ ነው።
ሥራ ሲጀምሩ፡ ቀጣሪዎ ምን ያህል ግብር እንደሚቀንስ ማወቅ አለበት። የኖርዌይ የኣገር ውስጥ ገቢ አስተዳደር ም/ቤት፡ ማንም ምን ያህል ግብር መክፈል እንዳለበት ያሰላል። የግብር አስተዳደሩ ስለእርስዎ ትክክለኛ መረጃ እንዲኖረው የማድረግ ኃላፊነት አለብዎት። ስለ እርስዎ፡ በግብር አስተዳደር ጽ/ቤት ኢንተርነት ውስጥ የተመዘገበውን መረጃ ማየት እና ኣስፈላጊ ለውጦችን ማድረግ ይችላሉ። ቀጣሪዎ የግብር ቅነሳ ካርድዎ ዲጂታል በሆነ መንገድ ያገኘዋል።
አሠሪው ደመወዝ ከመክፈሉ በፊት፡ ከሠራተኞቹ ጠቅላላ ክፍያ ግብርን የመቀነስ ግዴታ ኣለበት። አሠሪው፡ የግብር ቅነሳዎችን ለግብር ባለሥልጣናት ያስተላልፋል።
ዓመታዊ የገቢ እና የግብር መግለጫ ፣
የሚከፍሉት ግብር የሚሰላው፡ የኣገር ውስጥ ጽሕፈት ቤት፡ ስለ ሰዎቹ ባለው መረጃ ላይ ነው። በመጋቢት/ሚያዝያ ወር፡ እያንዳንዱ ሰው፡ ላለፈው ዓመት ገቢውን እና የመሳሰሉትን አጠቃላይ ዝርዝር ይቀበላል። ይህ አጠቃላይ ዝርዝር ዲጂታል ነው፡ ስለዚህ፡ አሃዞቹን ለመፈተሽ ወደ www.skattetaten.no መግባት ያስፈልጋል። በጣም ብዙ ግብር የከፈለ ተመላሽ ያገኛል። በጣም ትንሽ ግብር የከፈለ፡ ግን መክፈል ያለበትን በክፍያ መጠየቂያ ሰነድ ይቀበላል።
ኢንተርነት
የቅጥር ውል
በአንድ ቦታ ተቀጥሮ የሚሠራ ሁሉ፡ በጽሑፍ የሥራ ውል የማግኘት መብት አለው። ሠራተኛውም ሆነ አሠሪው ስምምነቱ ላይ መፈረም አለባቸው። የሥራ አካባቢ ሕግ፡ የሥራ ስምሪት ውሉ ምን መያዝ እንዳለበት ይገልጻል። እንዲሁም፡ የሥራ ቦታን፡ የደመወዝ እና የሥራ ሰዓት መግልጫን ያካተተ ነው።
በውል ያልተደገፈ ሥራ
በውል ያልተደገፈ ሥራ ማለት፡ ያለኮንትራት እና ግብር ሳይከፍሉ፡ መሥራት ማለት ነው። ስለሆነም፡ አሠሪው ለሠራተኛው የአሠሪውን የብሔራዊ መድን መዋጮ ወይም ሌላ ተመሳሳይ ክፍያ አያደርግም። በውል ያልተደገፈ ሥራ፡ ሕገ-ወጥ ነው፣ ስለሆነም፡ እንደ ኢኮኖሚያዊ የወንጀል ዓይነት ተደርጎ ይወሰዳል። አሠሪዎችም ሆኑ ሠራተኞች፡ በውል ባልተገለፀ ሥራ ምክንያት ሊቀጡ ይችላሉ።
በውል ያልተደገፈ ሥራ፡ ሥነ ምግባር የጎደለው ነው። ግብር የማይከፍሉ ሠራተኞች ፣ ለማህበረሰቡ የሚፈለግባቸውን አስተዋፅኦ አያደርጉም። በዚህ ረገድ፡ የኖርዌይ መንግሥት፡ በየዓመቱ በሚሊዮን የሚቆጠር ክሮነር ክግብር ገቢዎች፣ አሠሪው መክፈል የነበረብትን የብሔራዊ መድን መዋጮዎች እና በሠራተኛው የብሔራዊ መድን መዋጮ፡ ምክንያት ያጣል። ይህም ለማህበራዊ ደህንነት ሥርዓት፡ ለመክፈል ይረዳ የነበረበት ገንዘብ ነው።
በውል ያልተደገፈ ሥራ፡ ሕገ-ወጥ እና ሥነ ምግባር የጎደለው ከመሆኑ በተጨማሪ፡ ለሠራተኛውም ከፍተኛ መዘዝ ሊያስከትል ይችላል፡-
- የሕመም ክፍያ የለም፣
- የዕረፍት ጊዜ ክፍያ የለም፣
- የጡረታ መዋጮ የለም፣
- የሥራ አጥነት ጥቅም መብት የለም፣
- በሥራ ላይ ለሚደርስ አደጋ መድን የለም፣
- ከባንክ ብድር የማግኘት ዕድል የለም፣
- የሥራ ውል የለም፡ ማጣቀሻ የለም፡ የሥራ ልምድ ሰነድ የለም፡ ስለሆነም፡ ሌላ ሥራ ማግኘት አስቸጋሪ ይሆናል::
ኣብራችሁ ተወያዩ
- በአገርዎ ውስጥ የግብር ሥርዓቱ ምን ይመስላል?
- ነዋሪዎች ግብር ባይከፍሉ፡ በኖርዌይ የማሕበራዊ ደህንነት ሥርዓት ላይ ምን ችግሮች ሊያስከትል ይችላል?
- የጽሑፍ የሥራ ውል መኖር፡ ለምን አስፈላጊ ሆነ?
- በውል ባልተደገፈ ሥራ መስራት፡ ለግለሰቡም ሆነ ለኅብረተሰቡ ስለሚያስከትለው ችግር ላይ ተወያዩ።
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ
ጠቅላላ ደመወዝ ምንድነው?
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ
ክፍያን የሚያመለክት የወረቀት ማስታወሻ ምንድነው?
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ
በውል ያልተደገፈ ሥራ ምንድነው?
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ
መግለጫዎቹን ያንብቡ። ትክክል ምንድን ነው? ስህተት ምንድን ነው?
ትክክል ወይም ስህተት የሆነውን ይምረጡ
መግለጫዎቹን ያንብቡ። ትክክል የትኛው ነው? ስህተት የትኛው ነው?