ጤና

  • ለእናንተ ጥሩ ጤና ምን ማለት ነው?
  • ለአገሪቱ ነዋሪዎች የጤና ኃላፊነት መውሰድ የሚገባው ማነው?
  • የራሳችንን ጤና ለመንከባከብ ምን ማድረግ እንችላለን?
  • ቀድሞ ትኖሩበት ከነበረው አገር ይልቅ፡ በኖርዌይ መኖር ከመጣችሁ ወዲህ፡ የራሳችሁን ጤና ከመንከባከብ ባሻገር ስለ ተጨማሪ ነገር ማሰብ ይኖርባችኋል ማለት ነው?
    ወደ ዶክተር ስትሄዱ ምን ትጠብቃላችሁ?
  • በየትኞቹ ሁኔታዎች ዶክተር ማየት አስፈላጊ ነው ብለው ያስባሉ?

ጥሩ ጤንነት - ከበሽታዎች አለመኖር የበለጠ?

አንዳንድ ሰዎች ጥሩ ጤና ማለት አለመታመም ማለት ነው ይላሉ። አንዳንዶች ደግሞ ጥሩ ጤና ማለት ምቾትና በሕይወት ደስተኛ መሆን ማለት ነው ይላሉ። ጥሩ ጤናን በተመለከተ ሁለቱም ፍቺዎች ትክክል ናቸው። የመጀመርያው ትርጉም ምናልባት ከባድ በሽታ እና ድህነት በተስፋፋባቸው ማህበረሰቦች ውስጥ የበላይ ይሆናል። በሌሎች ማህበረሰቦች፣ ለአብዛኛዎቹ በሽታዎች መድሀኒት ሲገኝ እና አስፈላጊው የህክምና እርዳታ ለሁሉም በተሟሉባቸው ኣከባቢዎች፡ ጥሩ ጤንነት ማለት በአካል እና በአእምሮ ጤናማ ከመሆን የበለጠ እንደሆነ ይሰማቸዋል።

ለጤናችን ኃላፊነቱን የሚወስደው ማነው?

ቀደም ብሎ፡ ለሕመምተኞች ጤንነት ኋላፊነት ያለበት የጤና አገልግሎቱ እንደሆነ ያስቡ ነበር። ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ግን፡ ለጤንነታችን ትልቅ ኃላፊነት እንዳለብን ማሰብ የተለመደ ሆኗል። ህይወታችንን ለመኖር የምንመርጥበት መንገድ በጤናችን ላይ ተጽእኖ ይኖረዋል። የጤና አገልግሎት ምክር እና መመሪያ የመስጠት ሃላፊነት አለበት፡ ነገር ግን ምክሩን መከተል የኛ ሃላፊነት ነው። በሽታዎችን ለመከላከል እና ለማከም በኢንተርኔት፣ በዶክተር ወይም በፋርማሲ ውስጥ መረጃ ማግኘት ይቻላል።

አይጉል፡ አፍንጫዬ ተደፍኗል እንዲሁም ራሴንም እያመመኝ ነው።
ዶክተሩ፡ እሺ ምናልባት ጉንፋን ሳይዝህ አይቀርም። ጉሮሮህንም ሕመም ይሰማሃል?
አይጉል፡ በእውነቱ ጉሮሮዬን አላመመኝም ነገር ግን ጥቂት ያስለኛል።
ዶክተሩ፡ በሳምንት ውስጥ ይሻልሃል። እስከዚህ ሳምንት መጨረሻ የማይሻልህ ከሆነ ሌላ ቀጠሮ ማስያዝ ትችላለህ።
አይጉል ፡ ምንም አይነት መድሃኒት አታዝልኝም እንዴ?

በብዙ ሃገራት፡ ሕመምተኞች የእነርሱን የሕክምና ጉዳይ የመወሰን ስልጣን ያለው ዶክተሩ እንደሆነ አድርገው ያስባሉ። እንዲሁም፡ አንዳንድ ሕመምተኞች ዶክተሩን የሆነ መድኃኒት ካላዘዘላቸው አይለቁትም። በኖርዌይ ዶክተሮች ከሕመምተኞቻቸው ጋር የተለያዩ የሕክምና ዘዴዎችን እና የክትትል መንገዶችን ላይ ውይይት ማድረግ የተለመደ ነው።

Tips til undervisningen

Snakk sammen

Stikkord til diskusjonen: ha energi og overskudd, ikke være syk, føle velvære, fysisk kontra psykisk helse, bruk av medisiner, kroniske sykdommer, forebygging, livsstil, kosthold, trening, alkoholvaner, tobakk, informasjon, tannhelse, smittevern, økonomiens betydning for valgmulighetene, påkledning, forkjølelse

Snakk sammen om deltakernes forventninger til legebesøk, hva de er vant til fra tidligere og hva de kan forvente i Norge.

Snakk om kunstverket

Maleri. Mor ved sengen til sin syke datter.
Foto: Nasjonalmuseet/Børre Høstland «Det syke barn» malt av Edvard Munch (1885–1886).

Tips til undervisninga

Snakk saman

Stikkord til diskusjonen: ha energi og overskot, ikkje vere sjuk, kjenne velvære, fysisk kontra psykisk helse, medisinbruk, kroniske sjukdomar, førebygging, livsstil, kosthald, trening, alkoholvanar, tobakk, informasjon, tannhelse, smittevern, kva økonomi har å seie for ein person sine valmoglegheiter, påklednad, forkjøling

Snakk saman om kva deltakarane ventar seg av eit legebesøk, kva dei er vane med frå før og kva dei kan vente i Noreg.

Snakk om kunstverket

Maleri. Mor ved sengen til sin syke datter.
Foto: Nasjonalmuseet/Børre Høstland «Det syke barn» malt av Edvard Munch (1885–1886).