የጤና አገልግሎት
የጤና አገልግሎት
የማህበራዊ ደህንነት ስርዓት ግብ፡ በተቻለ መጠን ሕዝቡ ጥሩ ኑሮ እንዲኖር ማድረግ ነው።ይህም፡ ጥሩ የጤንነት ኣገልግሎት ጭምር እንዲኖር ነው። በኖርዌይ የመንግስት ጤና አገልግሎት አለ። ይህ ማለት፡ ሰዎች የሚያስፈልጋቸውን ህክምና እንዲያገኙ ሃላፊነት ይወስዳል። የግል የጤና ተቋማትም አሉ። በእነዚህ አገልግሎቶች የሚጠቀሙ ሰዎች ግን፡ ለሚያገኙት የህክምና ኣገልግሎት ራሳቸው ይከፍላሉ።
መደበኛ ጠቅላላ ዶክተር/ሓኪም
- ማንኛውም በኖርዌይ የሚኖር ሰው ኣጠቃላይ ሓኪም እንደ ቋሚ ሓኪሙ እንዲኖረው መብቱ ነው። ራስህ ወይም ከልጆችህ ህመም ሲሰማቸው፣ መጀመሪያ የምታናግሩት መደበኛ ሓኪማችሁን ነው።
- ኣስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ፡ ቋሚ ሓኪምህ ወደ ስፐሺያሊስት ሓኪም ሊያስተላልፍህ ይችላል።
- መደበኛ ሐኪምህን ማየት ከፈልግህ፡ ስልክ ደውለህ ቀጠሮ መያዝ አለብህ። ብዙ ጊዜ ቀጠሮ ለመውሰድ ጥቂት ቀናት መጠበቅ አለ፣ ነገር ግን፡ በአጠቃላይ የህመም ስሜት ከተሰማህ በዛ ቀን ቀጠሮ ልታገኝ ትችላለህ።
መደበኛ ጠቅላላ ሃኪምህን ራስህ ትመርጣለህ። መደበኛው ሓኪምህ ካልተማማህ መለወጥ ትችላለህ፡ ይህንን ማድረግ የምትችለው ግን፡ በአመት ሁለት ጊዜ ብቻ ነው።
በኢንተርነት (helsenorge.no) በኩል፡ መደበኛ ቋሚ ሓኪም ለምግኘት፡ ለመለወጥ እና ሌሎች ጠቃሚ የጤና መረጃዎችን ማግኘት ትችላለህ።
ኢንተርነት
ስፔሻሊስት ሓኪሞች
- ስፔሻሊስት (ልዩ) ሓኪም የሚባለው፣ ለምሳሌ የማህጸን ሓኪም፣የቆዳ ሓኪም፣ ከኣንገት በላይ (የጆሮ-አፍንጫ-ጉሮሮ) ሓኪም፡ እንዲሁም የልጆች ስፔሻሊስት ሕኪምን ማለት ነው፡፡
በኣጠቃላይ፡ ስፔሻሊስት ዶክተር ለማየት ከፈለግህ፡ ወደ ስፔሻሊስት ዶክተሩ ሊጽፍልህ የሚችለው የግል ሓኪምህ ነው።
ሆስፒታል መግባት
- ሆስፒታል መተኛት ያስፈልግ እንደሆነ ሐኪሙ ይወስናል። በመንግስት የሆስፒታል ቆይታ ከክፍያ ነፃ ነው። የመንግስት ባለስልጣናት ሁሉንም የህክምና፣ የምግብ እና የመጠለያ ወጪዎችን ይሸፍናሉ።
- ልጆች በሆስፒታል ውስጥ ሲሆኑ ከወላጆቻቸው አንዱ ከልጁ ጋር ብዙ ጊዜ ሆስፒታል ውስጥ ይቆያል።
ተመላላሽ የሆስፒታል ሕክምና
- ተመላላሽ ሕክምና ማለት አንድ ታማሚ በሆስፒታል አልጋ ሳይዝ እየተመላለሰ የሚታከምበት አሰራር ማለት ነው፡፡በተሰጠህን ቀጠሮ መሰረት ተገኝተህ ህክምናውን ከተደረገልህ ወደ ቤትህ ትመለሳለህ።
የድንገተኛ አገልግሎት
- የቋሚ ሓኪም ጽሕፈት ቤት ከተዘጋ በኋላ፡ እራስህ ወይም ከቤተሰብህ ኣንዱ ብትታመሙ ወይም ኣደጋ ቢደርስባችሁ፡ በቴለፎን ቁጥር 116 117 የኣስቸኳይ ሕክምና (ሌገቫክት) ተገናኙ።
- አንድ ሰው በጠና ከታመመ ወይም ከባድ ጉዳት ካጋጠመው እና አፋጣኝ እርዳታ የሚያስፈልገው ከሆነ፣ ወደ ድንገተኛ አደጋ ቁጥር 113 መደወል አለብዎት።
- ተረጋግታችሁ መረጃውን በሚከተለው ቅደም ተከተል ያቅርቡ፡ ማን እንደሆኑ፣ምን ችግር እንዳጋጠመ እና የት እንዳሉ/ያሉበትን ኣድራሻዎ/።
መደኃኒት ቤቶች
- አብዛኞቹ መድሃኒቶች መግዛት የሚቻለው ከፋርማሲዎች ብቻ ነው።
- አንዳንድ የመድኃኒት ዓይነቶች፣ ለምሳሌ ቀላል የህመም ማስታገሻዎች፡ ከግሮሰሪ ሱቆች/ሱፐርማርኬቶች ወይም ከነዳጅ ማደያዎች ሊገዙ ይችላሉ።
- በፋርማሲዎች ውስጥ የሚሰሩ ሰዎች መድሃኒትን በመምረጥ እና ኣጠቃቀሙ ላይ መምርያ ሊሰጡህ ይችላሉ።
- መድሃኒት ለመግዛት ብዙ ጊዜ የሃኪም ማዘዣ ያስፈልግሃል። በመድሃኒት ማዘዣው፡ የመድሃኒት ስም እና እንዴት ጥቅም ላይ እንደሚውል ይገልጻል።
- የመድሃኒት ማዘዣዎች ብዙውን ጊዜ ኤሌክትሮኒክ፡ አንዳንዴም በወረቀት ላይ ናቸው። ሁሉም ፋርማሲዎች የዲጂታል ማዘዣዎችን ማግኘት ይችላሉ።
- የታዘዘለህን መድሃኒት ለመውሰድ ስትሄድ፡ በፋርማሲው፡ (በባንክ ካርድ፡ የመንጃ ፍቃድ፡ ፓስፖርት ወይም መታወቂያ ካርድ) ማንነትህን መለየት ኣለብህ።
- ከባድ እና ሥር የሰደደ ሕመም ካለብህ፡ በሰማያዊው የመድሃኒት ማዘዣ፡ መድሃኒት፣ ምግብ እና የህክምና አቅርቦቶች ማግኘት ትችላለህ። ለዚህ አገልግሎትም የምትከፍለው መጠን በጣም ትንሽ ነው።
ምስጢር የመጠበቅ ግዴታ
- በጤና አገልገሎት ውስጥ የሚሳተፉ ባለሙያዎች ምሥጢር የመጠበቅ ግዴታ አለባቸው፡፡ይህ ማለት፡ ያለኣንተ ፈቃድ፡ መረጃህን ለሌላ አካል ማስተላለፍ አይችሉም ማለት ነው። ስለዚህ፡ ለሓኪምህ ችግርህን ነጻ ሆነህ መንገር ትችላለህ። የገዛ ቤተሰብ ጨምሮ፡ ሌላ ሰው የተናገርከውን ነገር ይሰማብኛል ብለህ ስጋት ሊሰማህ አይገባም።
- ሓኪሙ፡ በሕክምና ማሕደርህ ውስጥ፡ ስለኣንተ የ ተጻፈውን ማንኛውም ነገር የማወቅ መብት አለህ።
- ያነጋገርከው ሰው ስራውን ቢቀይርም የምስጢርነት ግዴታ ተግባራዊ ይሆናል።
- ምስጢር መጠበቅ ግዴታ አስተርጓሚዎችም ይመለከታል።
- ከ16 አመት በላይ የሆናቸው ልጆች፡ ወላጆቻቸው የጤና መረጃቸውን ማየት ይችሉ ዘንድ መወሰን ይችላሉ።
የታካሚ ክፍያ
- በሽተኛው የታካሚ ክፍያ ይከፍላል፣ መንግስት ደግሞ ቀሪውን የሕክምና ወጪዎችን ይሸፍናል።
- ታካሚዎች ለፋሻ፣ ለሲሪንጅ፣ ለመድሃኒት፣ ለምርመራዎች ወዘተ. ራሳቸው መክፈል አለባቸው። ይህ ታካሚው ከሚያደርገው ክፍያ በተጨማሪ ነው።
- እድሜያቸው ከ16 አመት በታች የሆኑ ልጆች የታካሚ ክፍያ አይከፍሉም፡፡
- የወሊድ ምርመራዎች ከክፍያ ነጻ ነው፡፡
- ለመደበኛ የግል ሃኪማችሁ ቀጠሮ ለማስያዝ የምታደርጉት ክፍያ፡ ኣብዛኛውን ጊዜ፡ ከ150 እስከ 300 የኖርዌይ ክሩነር ነው፡፡
- ሥር የሰደደ ሕመም ካለብህ፣ ለታካሚው ክፍያው እንዲመለስለት ሆኖ በተዘጋጀው ሰነድ ላይ ትከፍላለህ።
- በአንድ አመት ውስጥ የተወሰነ የታካሚ ክፍያዎች መጠን ካደረግህ በኋላ፣ የነፃ ሕክምና ካርድ የማግኘት መብት ኣለህ። የተወሰነ የታካሚ መጠን ክፍያዎችን ከከፈልህ፣ የጤና ቁጠባ አስተዳደር (HELFO) ከክፍያ ነጻ የሆነ ካርድ ይልክልሃል ወይም በ helsenorge.no የነፃ ታካሚዎች ካርድ የመውጣት ትችላለህ። ወደ ሐኪም ስትሄድ ወይም ክፍያን የሚመለስ የመድሃኒት ማዘዣ ስትገዛ፡ ይህንን ካርድ ማቅረብ አለብህ። ይህ ማለት፡ በቀሪው የአመት፡ የታካሚ ክፍያ መክፈል የለብህም ማለት ነው።
አስተርጓሚ መጠቀም
ኣንተና መደበና ሓኪምህ፡ በቋንቋ ምክንያት ልትግባቡ ካልቻላችሁ፡ ወደ ሓኪም በምትሄድበት ግዜ፡ ኣስተርጓሚ ይዘህ የመሄድ መብት ኣለህ። ለዚህም ምንም ዓይነት ክፍያ ኣትጠየቅም።
ኣብራችሁ ተወያዩ
- በምታውቃቸው አገሮች የጤና አገልግሎት እንዴት ነው የሚሰራው?
- ለበሽተኛው የሚደረግ ህክምና ከክፍያ ነጻ ሲሆን፡ መንግስት ወጪዎቹን ይሸፍናል። መንግስት ገንዘቡን የሚያገኘው ከየት ነው?
- ቋሚ መደበኛ ሃኪም መኖሩ ጥቅሞቹ ምንድናችው?
- ላንተ ቅርብ የሆነ፡ የአደጋ እና የድንገተኛ ሕክምና (ሌገቫክት) የት ይገኛል?
ትክክለኛውን መልስ ምረጡ
የመንግስት የጤና አገልግሎት ማለት ምን ማለት ነው?
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ
ሐኪም ማየት ከፈለጉ መጀመሪያ ማንን ማነጋገር አለብዎት?
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ
በኖርዌይ ውስጥ አንድ ሰው ሆስፒታል ሲተኛ ሊከፍል የሚገባው የትኛውን ክፍያ ነው?
ትክክል ወይም ስሕተት የሆነውን ምረጡ
መግለጫዎቹን ያንብቡ:: ትክክል የትኛው ነው? ስህተት የትኛው ነው?
ትክክል ወይም ስህተት የሆነውን ይምረጡ
መግለጫዎቹን ያንብቡ:: ትክክል የትኛው ነው? ስህተት የትኛው ነው?