ማሕበራዊ መድረኮች
ማሕበራዊ መድረኮች
ማሕበራዊ መድረኮች ማለት ሰዎች የጋራ ጊዜ ለማሳለፍ የሚገናኙባቸው ስፍራዎች ማለት ነው። ብዙ ጊዜ ሰዎች በሕይወታቸው ውስጥ የተለያዩ ማሕበራዊ መድረኮች ይኖሯቸዋል። ቤተሰብ፡ ማለትም የራስ ቤተሰብ እንዲሁም ዘመድ ወዳጆች፡ እንደ አንድ መድረክ ሊወሰዱ ይችላሉ። የሥራ ቦታ እና ትምህርት ቤቶች ደግሞ ለብዙ ሰዎች ጠቃሚ መድረኮች ሊሆኑ ይችላሉ። ብዙ ሰዎች ጓደኞቻቸውን የሚያገኙት በእረፍት ቀናቸው ነው።በቡና ቤት ውስጥ እና የመሳሰሉት ቦታዎች ሊገናኙ ይችላሉ። አሊያም ደግሞ በየራሳቸው ቤት ውስጥ ሊገናኙ ይችላሉ። ብዙ አዋቂ ሰዎች በእረፍት ቀናቸው አንዳንድ ኮርሶችን አሊያም ተጨማሪ ትምህርቶችን ሊማሩ ይቸችላሉ። ብዙ ጎልማሶች በትርፍ ጊዜያቸው የተለያዩ ኮርሶች ወይም ተጨማሪ ትምህርት ይወስዳሉ። አንዳንድ ሰዎች በመዘምራን ቡድን ውስጥ ይዘምራሉ ወይም መሣሪያ ይጫወታሉ፣ ሌሎች ደግሞ በተለያዩ ድርጅቶች ውስጥ ይሳተፋሉ። እነዚህም ማህበራዊ መድረኮች ናቸው።
የተደራጁ የመዝናኛ እንቅስቃሴዎች
ብዙ ልጆች በተለያዩ የተደራጁ የመዝናኛ እንቅስቃሴዎች ይሳተፋሉ። በስፖርት ክበብ ውስጥ ሊሆኑ ወይም በሙዚቃ ባንድ ውስጥ ይጫወታሉ። አንዳንዶቹ ወደ ስካውት ወይም አስጎብኚዎች ይሄዳሉ፣ ሌሎች ደግሞ ወደ ፎቶግራፊ ቡድን ይሄዳሉ። ወላጆቹ በብዙዎች እንቅስቃሴዎች ውስጥ ይሳተፋሉ። በእነዚህ እንቅስቃሴዎች ምናልባት የአንድ ሰው እናት የእጅ ኳስ ቡድንን ታሠለጥናለች? ምናልባት ወላጆች ተራ በተራ ልጆችን ከተለያዩ የእንቅስቃሴ ቦታዎች ያመላልሷቸዋል። ይህ፡ በቅርብ ወደ ኖርዌይ ለመጡ ወይም ወደ አዲስ አካባቢ የተንቀሳቀሱ፡ ሰዎችን ለማወቅ ጥሩ ኣጋጣሚ ሊፈጥር ይችላል።
የበጎ ፈቃድ ሥራ
የበጎ ፈቃድ ሥራ ማለት በመደበኛ መንገድ ተቀጥራችሁ የማትሰሩት ሥራ ማለት ነው፡፡ ሥራው ክፍያ የለውም፡፡ የበጎ ፈቃድ ሥራ ለአጭር ጊዜ የሚሰራ እንጂ ማንም ሰው በሙሉ ጊዜው የሚሰራው አይደለም! የበጎ ፈቃድ ሥራ፡ ኣብዛኛውን ጊዜ ከሕዝብ አገለግሎት ጋር የተገናኙ ድርጅቶች ሥራዎች ናቸው፡፡ ለምሳሌ፣ ቀይመስቀል፡ የስፖርት ክለቦች፡ የባሕል ዝግጅቶች እና የመሳሰሉትን ያጠቃልላል፡፡
በስካንዲኔቪያን ሃገራት ብዙ ሰዎች በበጎ ፈቃድ አገልግሎት ሰጪ ድርጅቶች ውስጥ ተሳትፎ ያደርጋሉ። አዳዲስ ነገሮችን ለመማር እና አዳዲስ ጓደኞችን ለማፍራት ምቹ አጋጣሚዎችን ይፈጥራሉ። ከእነዚህ ድርጅቶች አብዛኛዎቹ ስለ ዲሞክራሲ እውቀት ያስጨብጣሉ። ተሳታፊዎቹም በስብሰባዎች የመሳተፍን፣በምርጫዎች ላይ በመሳተፍ፣ ድምጽ በመስጠት እንዲሁም በመሳሰሉት ነገሮች ላይ የዲሞክራሲ መመሪያዎችን ልምድ ያገኛሉ።ብዙ የበጎ ፈቃድ አገለግሎት ሰጪ ድርጅቶች በአካባቢያዊው ማህበረሰብ እንዲሁም በአገር አቀፍ ደረጃ ባለው ፖለቲካዊ ሂደቶች ላይ ተጽእኖ የማድረግ አቅም አላቸው።
በተለያዩ የበጎ ፈቃድ ድርጅቶች ውስጥ መሳተፍ፡ በምትኖርበት አካባቢ ከሚኖሩ ሰዎች ጋር የመተዋወቅ እና የምትኖሩበት አካባቢ ማሕበረሰብ የእናንተ እንደሆነ እንዲሰማችሁ ያደርጋችኋል። ከሥራችሁ፡ ከትምህርት እንዲሁም ከእለት ተአለት ሕይወታችሁ ጋር በተያያዘ ትልቅ ትስስር እንድትፈጥሩ ያደርጋችኋል።
አንድ ላይ መሆን
በሁሉም ሕብረተሰብ ዘንድ በጽሑፍ የሰፈሩም ያልሰፈሩም ደንቦች አሉ። ደግሞም ሁሉም ሰው የሚያውቃቸው ነገር ግን በጽሑፍ ያልሰፈሩ ደንቦች አሉ። እነኚህ ደንቦች እንደየባህሉ ይለያያሉ። ለዚህ ምሳሌ ሊሆነን የሚችለው አንዱ የሰላምታ ልውውጥ ነው። በኖርዌይ እጅ በመጨባበጥ ሰላምታ መስጠት በወንዶችም በሴቶችም ዘንድ የተለመደ ነው። በምንሰነባትበትም ጊዜ ደህና ሁን ለማለት እጅ መጨባበጥ የተለመደ ነው። ጓደኛማቾችም ሲገናኙ “ሃይ” በማለት፣ ተቃቅፈው ትከሻቸውን መታመታ እየተደራረጉ ሰላምታን ይለዋወጣሉ። የተለመደው የሰላምታ መግቢያ “ሃይ፣እንዴት ነህ/ነሽ?” የሚለው ሲሆን ለዚህ ሰላምታ የተለመደው ምላሽ ደግሞ “አመሰግናለሁ ደሕና ነኝ፣ አንተስ/አንቺ?” የሚል ነው።
ስደተኛ፦ አንድ ቀን ልትጎበኘኝ ትችላለህን?
ኖርዌጅያዊ፦ አዎን በጣም ጥሩ ሃሳብ ነው።
ከአንድ ወር በኋላ፦
ስደተኛ፦ ለምንድነው ያልጎበኘኸኝ?
ኖርዌጅያዊ፦ አልጋበዝከኝም እኮ።
ምንድነው የተፈጠረው? ግባዣ የተለየ ቀን እና ሰአት ሊወሰንለት ይገባል። ኖርዌጃኖች አስቀድመው ሳያሳውቁ ጉብኝት የሚያደርጉት አንዳንድ ጊዜ ብቻ ነው።
ኣብራችሁ ተወያዩ
- ልጆች በተደራጀ የመዝናኛ እንቅስቃሴዎች ላይ ተሳትፎ ያደርጉ ዘንድ ወላጆች ቀዳሚ ሆነው ሊገኙ ይገባልን? ምን ማድረግ አለባቸው? ምን ማድረግ የለባቸውም?
- በምትኖሩት አካባቢ የበጎ ፈቃድ ድርጅቶች መኖር አለመኖራቸውን ታውቃላችሁን?
- “ያለ በጎ ፈቃድ ሰራተኞች ኖርዌይ ሁሉ ነገሯ ይቆማል"። በሚለው ሃሳብ ተወያዩበት።
- የበጎ ፈቃድ ስራ መልካም ጎኖቹ ምንድናቸው?
- ኖርዌይ ከመምጣታችሁ በፊት፡ ታውቋቸው የነበሩ፡ ምሳሌ ሊሆኑ የሚችሉ በጽሁፍ ያልሰፈሩ ደንቦችን ፈልጉ።
- በኖርዌይ ውስጥ ያሉ የምታውቋቸው በጽሑፍ ያልሰፈሩ ደንቦችን ግለጹ።
- የተለያዩ ባህሎች እንግዶችን እንዴት እንደሚያከብሩ፣ ሰዎች ሲያድሩ፣ ጉብኝቱን ከሚያስተናግደው ሰው ምን እንደሚጠበቅ፣ ጉብኝት ለምን ያህል ጊዜ ሊቆይ እንደሚችል ወዘተ በተመለከተ ትልቅ ልዩነቶች አሉ። በእነዚህ ልዩነቶች ላይ ተወያዩ።
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ
ማሕበራዊ መድረኮች ምንድናቸው?
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ
የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ምንድነው?
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ
በኖርዌይ ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ ያገኛችሁትን ሰው ሰለምታ የምትለዋወጡበት የተለመደው አይነት ሰላምታ የትኛው አይነት ነው?
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ
በጎ ፈቃደኛ ሆኖ የማገልገል ጥቅሙ ምንድነው?
ትክክል ወይንም ስህተት የሆነውን ይምረጡ
መግለጫዎቹን ያንብቡ:: ትክክል የትኛው ነው? ስህተት የትኛው ነው?