ኖርዌይ ከ1814 እስከ 1905 እ.ኤ.አ
ኖርዌይ ከ1814 እስከ 1905 እ.ኤ.አ
ውህደቱት ማፍረስ እና ኣዲስ ሕብረት
በ19ኛው መቶ ክፍለዘመን መጀመሪያ አካባቢ ላይ በአውሮፓ የተለያዩ ስፍራዎች ጦርነቶች የነበሩበት ዘመን ነበር፣ በተለይ በአንድ በኩል በእንግሊዝ በአንድ በኩል በፈረንሳይ ይካሄድ የነበረው ጦርነት ሆኖ፡ “ናፖሊዮናዊ ጦርነት” በመባል ይታወቃል፡፡ የዴንማርክና ኖርዌይ ሕብረት ከፈረንሳይ ቆመው ስለነበር፡ ፈረንሳይ በጦርነቱ ስትሸነፍ፡ የዴንማመርክ ንጉሥ፡ ኖርዌይን ከእንግሊዝ ወገን ቆማ ለነበረችው ለስዊድን አሳልፎ ሰጣት፡፡
በ1814 ዓ.ም በኖርዌይና በዴንማርክ መካካል የነበረው ውሕደት ፈረሰ፡፡ ብዙ ኖርዌጅያውያንም አገሪቱ ራሷን የቻለች ነጻ አገር እንደምትሆን ተስፋ አድርገው ስለ ነበር፣ 112 ኃይለኛ ሰዎች በኣይድስቮል ስብሰባ አደረጉ። ካደረጓቸው ነገሮች መካከል፡ የነጻ ኖርዌይ ሕገመንግሥት ማርቀቃቸው ነበር፡፡ በግንቦት 17፡ 1814 ኖርዌይ የራሷ የሆነ ሕገ መንግሥት አረቀቀች፤ ለዚህም 1814 ዓ.ም ለኖርዌጅያውያን በጣም ወሳኝ አመት ነበር።
ይህ ቢሆንም፣ በሕዳር ወር 1814 ዓ.ም. ኖርዌይ ከስዊድን ጋር ሕብረት እንድፈጥር ተገድዳለች። ከስዊደን ጋር የነበረው ህብረት ከዴንማርክ ጋር ከነበረው በጣም የላላ ነበር። ኖርዌይም ባወጣችው ሕገመንግሥት ጥቂት ለውጥ ተደርጎበት፡ የውስጥ ጉዳይዋ ራሷን እንድታስተዳድር ተፈቀደላት። በዚሁም፡ በ1814 ዓ.ም የኖርወይ ፓርላማ (ስቶርቲንጌ) በ 1814 ዓ.ም. ተቁቋመ።
የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ በስዊድን ነበር የሚወሰነው፡ ንጉሱ ካርል ዮሃን የሚባል ስወድናዊ ነበር። የኦስሎ ዋና ጎዳናም በስሙ ተሰይሟል።
ብሔራዊ ሮማንቲሲዝም እና የኖርዌይ ብሄራዊ ማንነት
በ19ኛው ክፍለ ዘመን አጋማሽ ላይ በአውሮፓ ውስጥ የኪነጥበብ እና የባህል እንቅስቃሴ ተፈጠረ:: ይህ ብሄራዊ ሮማንቲሲዝም ይባል ነበር። በዚህ እንቅስቃሴ፡ ልዩ የሆኑ አገራዊ ባህሪያትን ለማጉላት እና ብዙውን ጊዜ ከእውነታው የተሻሉ እንዲሆኑ ለማድረግ አስፈላጊ ሆነ። በኖርዌይ ውስጥ፣ ልዩ ትኩረት የተሰጠው በኣገሪቱ ውብ ገጽታ ጐልቶ በማውጣት እና፡ የገጠር ገበሬ ማህበረሰቦች ደግሞ እውነተኛዋን ኖርዌይ ምሳሌ ሆነው ታይተዋል። ብሄራዊ ሮማንቲሲዝም በሥነ ጽሑፍ፣ ሥዕል እና ሙዚቃ ይገለጣል። ብዙ ሰዎች ኖርዌጂያውያን በመሆናቸዉ የበለጠ ኩራት ይሰማቸው ስለ ጀመረ፣ ኖርዌይ ነጻ ሀገር እንድትሆን ፈለጉ።
ከብዙ መቶ ዓመታት ከዴንማርክ ጋር ሕብረት ተከትሎ፡ በኖርዌይ በስራ የዋለው የጽሑፍ ቋንቋ የዴንማርክ/ዳንስክ/ ነበር። አሁን ቡክማል ተብሎ የሚታወቀው የኖርዌጂያን የጽሑፍ ቅጽ፡ ዳንስክ ወደ ኖርዌጂያን በመለወጥ ነበር። በብሔራዊ ሮማንቲሲዝም ዘመን፣ ብዙ ኖርዌጂያውያን በዳንስክ ላይ ያልተመሰረተ የራሳችን የጽሑፍ ቋንቋ ሊኖራቸው እንደሚገባ ይፈልጉ ነበር። ኢቫር ኦሰን የተባለ የቋንቋ ሊቅ፡ የተለያዩ የኖርዌይ ቋንቋ ኣባባልን በምሳሌነት በመሰብሰብ፡ ያከናወነው ሥራ መሰረት በማድረግ ነበር። በሰበሰባቸው ምሳሌዎች ላይ በመመስረት፡ ኒኖሽክ የተሰኘ የኖርወይ ቋንቋ ፈጠረ። ሁለቱም ኒኖሽክ እና ቡክሞልን ከ9ኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ በጣም የተለወጡ ቢሆኑም፡ ሁለቱም የኖርዌጂያን የጽሁፍ ቅጾች ናቸው። የሳምስክ ቋንቋም በኖርዌይ እንደ ብሔራዊ ቋንቋ ጥቅም ላይ ውሏል።
ከግብርና ወደ ኢንዱስትሪ
ኖርዌይ የገበሬ ማህበረሰብ ነበረች። በ19ኛው ክፍለ ዘመን አጋማሽ ላይ፡ 70 በመቶው የኖርዌይ ህዝብ በገጠር ውስጥ ይኖር ነበር። አብዛኛዎቹ ኑሮአቸውን የሚተዳደሩት በእርሻ እና በአሳ ማጥመድ ነበር። ይህ ለብዙ ሰዎች ከባድ ሕይወት ነበር። የሕዝቡ ቁጥር ስለ ጨመረ፣ ለሁሉም የሚሆን በቂ መሬትና ሥራ አልነበረም። በተመሳሳይ ጊዜ፡ በከተሞች ለውጦች እየታዩ ነበር። ፋብሪካዎች ተጀመሩ፣ ብዙ ሰዎች ሥራ ለማግኘት ከገጠር ወደ ትናንሽና ትልላቅ ከተሞች ይሄዱ ጀመር። የከተማ ሕይወት ግን ለብዙ የሰርቶ ኣደር ቤተሰቦች እጅግ ከባድ ነበር። የስራ ሰዓታት በጣም ረጅም፡ የኑሮ ሁኔታ ድማ ከባድ/ኣስቸጋሪ ነበር። ኣብዛኞቹ ቤተሰቦች ብዙ ልጆች ነበሯቸው፣ እና ለብዙ ቤተሰቦች አንድ ትንሽ አፓርታማ መካፈላቸው የተለመደ ነበር። ብዙ ልጆች ቤተሰቦቻቸው ለመርዳት በፋብሪካዎች ውስጥ ይሰሩ ነበር።
ከ1850 ዓ.ም በፊት 15 ከመቶ የሚሆነው ሕዝብ የሚኖረው በትልልቅና አነስተኛ ከተሞች ውስጥ ነበር፡፡ በ19ኛው ክፍለ ዘመን መጨረሻ አካባቢ ባለው ጊዜ ይህ መጠን ወደ 35 ከመቶ ጨምሯል። በ1900 ዓ.ም. 23 ከመቶ የሚሆነው ተቀጥረው የሚሰሩ በኢንዱስትሪዎች ዘርፍ ነበር። ከ1850 እስከ 1920 ዓ.ም ባለው ጊዜ ውስጥ፡ በግምት 800,000 ኖርዌጅያውያን ወደ አሜርካ ተሰደዋል፡፡
ነጻ እና ሉአላዊት አገር
ከስዊድን ንጉስ ጋር በተደርገው የፖለቲካ ስምምነትን ተከትሎ፣ የኖርዌይ ፓርላማ (ስቶርቲንግ)፡ ከሰኔ 7 ቀን 1905 ጀምሮ፡ የስዊድን ንጉስ የኖርዌይ ንጉስ እንዳልሆነ እና ኖርዌይ ከስዊድን ጋር የነበራትን ህብረት መፍረሱን አስታወቀ። ከስዊድን የመጣ ጠንካራ መልስ ስሜቶችን ስልስነሳ፡ ኖርዌይ እና ስዊድን ለጦርነት ተቃርበው ነበር። በዚያው አመት በተደረጉ ሁለት ህዝበ ውሳኔዎች ግን፡ ከስዊድን ጋር የነበረው ህብረት ፈርሶ፡ አዲሱ የኖርዌይ ኣገር፡ ንጉሳዊ አስተዳደር እንደሚኖራት ሆኖ ተወሰነ።
የስዊድን ንጉስ የእነዚህን ሪፈረንደም ውጤት ተቀበለ። የዴንማርክ ልዑል ካርል፡ አዲሱ የኖርዌይ ንጉስ ሆኖ ተመረጠ። የቀድሞ የኖርዌይ ነገሥታት ይጠቀሙበት የነበረውን ‘ሀኮን የሚል ስም ወሰደ። ንጉስ ሀኮን ሰባተኛ፡ ከ1905 ጀምሮ በ1957 እስከሞተበት ጊዜ ድረስ፡ የኖርዌይ ንጉስ ነበር።
ኣብራችሁ ተወያዩ
- በኖርዌይ ግንቦት 17ን ለምን እናክብራለን?
- ብሔራዊ ቀኖች በተለያዩ አገራት በተለያየ መንገድ ይከበራሉ። በትውልድ አገራችሁ ብሔራዊ ቀን እንዴት ነው የሚከበረው? ኖርዌጃኖችን ከሚያከብሩበት ኣግባብ ምን አይነት ተመሳሳይነትና ልዩነት አለው?
- ብዙ ኖርዌጃኖች በ19ኛው ክፍለ ዘመን ጠንካራ የሆነ የብሔራዊ ስሜት አዳብረዋል፡፡ ብሔራዊ ስሜት ምን ማለት ነው? እንዴትስ ይፈጠራል?
- ጠንካራ የሆነ ብሔራዊ የኩራት ስሜት አሉታዊ ጎኑ እንዲሁም አዎንታዊ ጎኑ ምንድነው?
- ኖርዌይ ከስዊድን ጋር በውህደት የኖረችባቸው ጊዜያት አሁን በሁለቱ አገራት መካከል ባለው ግንኙነት ላይ የፈጠረው ነገር ይኖር ይሆን?
- ከ1814 እስከ 1905 ዓ.ም. ስለነበረው የኖርዌይ ታሪክ ተምራችኋል፡፡ ከተማራችሁት ነገር፡ በተለይ ለዛሬዋ ኖርዌይ እድገት ጠቃሚ የሆነ ይመስልሃል?
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ
ኖርዌጅያውያን የራሳቸውን ሕገ መንግሥት ያረቀቁት መቼ ነበር?
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ
ኖርዌይ ከስዊድን ጋር የተዋሃደችው መቼ ነበር?
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ
ኢቫን አሰን ኒኖሽከን እንዴት አድርጎ ፈጠረው?
ትክክል ወይም ስህተት የሆነውን ይምረጡ
መግለጫዎቹን ያንብቡ። ትክክል የትኛው ነው? ስህተት የትኛው ነው?
ትክክል ወይም ስህተት የሆነውን ይምረጡ
መግለጫዎቹን ያንብቡ። ትክክል የትኛው ነው? ስህተት የትኛው ነው?
ምስሉን ተጫኑት
በዘመን ቅደም ተከተሉ መሰረት ትክክለኛውን ምሥል ተጫኑት ፡፡ ሃኩን ሰባተኛው መቼ ነበር የኖርዌይ ንጉሥ የነበረው?