ዘላቂ እድገት
ፊልሙን ይመልከቱ
ዘላቂ እድገት
የተባበሩት መንግስታት የዘላቂ ልማት ግቦች (SDGs) በመላው አለም ዘላቂ ልማት ለማምጣት የጋራ እቅድ ነው። ግባቸው እ.ኤ.አ በ2030 ዓ.ም፡ ድሕነትን ማጥፋት፣ የእኩልነት ችግሮችን ማስወገድና፡ የአየር ንብረት ለውጥን ማስቆም ነው።
የአየር ንብረት ለውጥ
የአየር ጠባይ እና የአየር ንብረት አንድ አይነት አይደሉም። የአየር ጠባይ በየእለቱ ከቤት ውጭ ስንሆን ወይም በመስኮት ስንመለከት የምናየው ሲሆን፡ የአየር ንብረቱ ደግሞ ለረጅም ጊዜ የሚለካው አማካይ የአየር ሁኔታ ነው። ባለፉት 100 ዓመታት ውስጥ በምድር የአየር ንብረት ላይ ከፍተኛ ለውጦች ተመዝግቧል። አብዛኛዎቹ የአለም የአየር ንብረት ተመራማሪዎች፡ ከምናየው ፈጣን የአየር ንብረት ለውጥ ጀርባ የሰው ልጅ የካርቦን ዳዮክሳይድ (CO2) ልቀት እንደሆኑ ያምናሉ።
እያጋጠሙን ያሉት ለውጦች የሚከተሉትን ያካትታሉ:
- የምድር ሙቀት እየጨመረ ነው።
- የውቅያኖሱ መጠን እየጨመረ እና አሲድነቱ እየጨመረ ነው።
- በረዶው እየቀለጠ ነው።
- የበለጠ የተለያየ ዝናብ እና የበለጠ የከፋ የአየር ሁኔታ አለ።
ሊታደሱ የሚችሉ ሀብቶች
ታዳሽ ሃብቶች ማለት ራሳቸውን የሚያድሱ የተፈጥሮ ሃብቶችን ማለት ነው፡፡ ሰዎች እነዚህን ሃብቶች በጥንቃቄ ሊጠቀሟቸው ይችላሉ፣ በአግባቡ ከተጠቀሙባቸው አይጠፉም፡፡
የታዳሽ የተፈጥሮ ሃብቶች ምሳሌ፡
- እንስሳት፡ ዛፎች እና ተክሎች፡
- ዝናብ፡ ንፋስ እና ውሃ፡
- የፀሐይ ብርሃን፡
ኢታዳሽ የሆኑ ሃብቶች፡ ምሳሌ
- ዘይት
- ነዳጅ
- ጋዝ
- የድንጋይ ከሰል
በአካባቢው-የተመረተ ምግብ
በአገር ውስጥ የሚመረት ምግብ ከሸማቹ አጠገብ ይመረታል። በአገር ውስጥ ምግብ በሚመረትበት ጊዜ የትራንስፖርት ፍላጎት አነስተኛ ስለሆነ ብዙ የሙቀት አማቂ ጋዝ ልቀትን እንቆጠባለን። በአገር ውስጥ የሚመረቱ ምግቦችን መቆጣጠርም ቀላል ነው። ይህ የሰብል ርጭቶችን፣ በስጋ እና በአሳ ኢንዱስትሪ ውስጥ አንቲባዮቲክን መጠቀም እና የእንስሳት ደህንነት ሁኔታዎችን ሊመለከት ይችላል።
ኣብራችሁ ተወያዩ
- ስለ አየር ንብረት ለውጥ ተነጋገሩ፡፡ ይህ ጉዳይ የትውልድ ሃገራችሁን በምን መልኩ ጎድቷል? ኖርዌይንስ በምን መንገድ ጎድቷታል?
- ስለ ታዳሽ ሃብቶች ተነጋገሩ፡፡ ሰዎች እነዚህን ሃብቶች ተፈጥሮ ልታድስ ከምትችልበት ፍጥነት ባለፈ ሲጠቀሙባቸው ምን ሊፈጠር ይችላል?
- በአካባቢ ስለሚመረት ምግብ ጥቅምና ጉዳት ተነጋገሩ፡፡
- አንዲት አገር እራሷን የቻለች መሆኗ ጥቅም አለውን? አዎ ከሆነ ለምን? አይ ከሆነ ለምን?
- የተባበሩት መንግስታት የዘላቂ ልማት ግቦች ላይ ተነጋገሩ፡፡ ከእነሱ መካከል አንዳዶቹ ከሌሎች በተለየ መልኩ የበለጠ የሚጠቅሙ ይመስላችኋልን? ዓለም በሞላው በዚህ እቅድ የሚስማማ ይመስላችኋልን?
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ
የአየር ንብረት ምን ማለትነው?
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ
አብዛኞቹ የአየር ንብረት ተመራማሪዎች ዛሬ ከምናያቸው ፈጣንና ሰፊ ለውጦች በስተጀርባ ምን አለ ብለው ያምናሉ?
ትክክለኛውን መልስ ይምረጡ
ታዳሽ ሃብት ምን ማለት ነው?
ትክክል ወይም ስህተት የሆነውን ይምረጡ
መግለጫዎቹን ያንብቡ፡፡ ትክክል የትኛው ነው? ስህተት የትኛው ነው?
ትክክል ወይም ስህተት የሆነውን ይምረጡ
አረፍተ ነገሩን ያንብቡ፡፡ ትክክል የትኛው ነው? ስህተት የትኛው ነው?
ምስሉን ተጫኑት ፡፡
የትኛው ምስል ነው የማይታደስን የተፈጥሮ ሃብት የሚያሳየው?